የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባወጣው መግለጫ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትግራይን ህዝብ በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ “በጥብቅ” አሳስቧል።

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባወጣው መግለጫ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትግራይን ህዝብ በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ “በጥብቅ” አሳስቧል።

ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ

የትግራይ ክልል መንግስትና ህዝብ ሰላሙን አስጠብቆ የክልሉን ውስጣዊ ችግሮች ለመፍታት ሌትና ቀን በሚረባረብበት ወቅትየአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዛሬው ዕለት (ጥቅምት 13 ቀን 2011ዓ.ም) ባወጣው መግለጫ “ የአማራ ብሔራዊ ክልል ከትግራይ ብሔራዊ ክልል ጋር በሚያዋሰኑት የወልቃይትና የራያ አላማጣ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች የሰላም መታወክ እየገጠመ ይገኛል። •••.አያይዞም ሁኔታው “ለክልላችን ትልቅ የፀጥታ ስጋት ሆኗል” ብሏል። የትግራይ ክልል ከመግለጫው በተቃራኒ የሁሉም ብሄር ብሄረሰብ ተወላጆች ሕገ መንግስታዊ መብታቸውና ነፃነታቸው ተከብሮ በሰላምና በክብር የሚኖሩባት ክልል ሆና እያለች ዜጎች በማንነታቸው የሚፈናቀሉባትና የአማራ ክልል ሰላም ችግር ፈጣሪ መባሏ አሳዛኝና ከትንኮሳ የማይተናነስ ጠባጫሪ አቋም ነው። በዚህ አጋጣሚ የትግራይ ክልል መንግስትና ህዝብ ለአማራ ህዝቦች ማረጋገጥ የምንፈልገው ለሰላማቸው መረጋገጥ እንጂ በማንኛውም ጊዜ ለፀጥታቸው መደፍረስ ምክንያት ሊሆኑ እንደማይችሉ ነው።

መግለጫው በመቀጠልም “የተከሰተው ግጭት መነሻው የራያ አካባቢ ህዝብ የማንነት ጥያቄ ሲሆን ይህንን ጥያቄ ከህዝቡ ጋር በመነጋገር ሕገ መንግስታዊ ምላሽ መስጠት እንደሚገባ በአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርትም ሆነ በኢህአዴግ ጉባኤዎች አቅጣጫ መቀመጡን ይታወሳል” በማለት ሕገ መንግስቱ በማንነት ጉዳይ ላይ ያስቀመጠውን ስርዓት በመጣስ በሌላ ክልል የውስጥ ጉዳይ ጠልቃ መግባቱ የሚያረጋግጥ መግለጫ ነው። በመግለጫው በግልፅ እንደተቀመጠውም በራያም ሆነ በወልቃይት አካባቢዎች ለተፈጠሩ ችግሮችንም የአማራ ክልል መንግስት ኃላፊነቱን መውሰድ ይኖርበታል።

በአጠቃላይ የአማራ ክልል መንግስት ያወጣው መግለጫ መሰረታዊ የሆነ ሕገ መንግስታዊ ጥሰት ያለበትና በሁለቱ ክልል ህዝቦች መካከል ለዘመናት የኖረው አብሮነት የሚጎዳ አደገኛ አካሄድ በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲታረም እና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትም ለትግራይ ህዝብ በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና የትግራይ ህዝብ በጥብቅ እናሳስባለን።

የትግራይ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ
ጥቅምት 13 ቀን 2011ዓ.ም
መቐለ


አረ ተውት😕😕
የሁለት ሀገሮች መንግስታት መግለጫ ነው እንዴ?