የታሰሩት የONN ጋዜጠኞች::

የታሰሩት የONN ጋዜጠኞች::
1. ሰቦንቱ አህመድ
2. ባህሉ ነጮ
3. ደሱ ዱላ
4. ኤቢሴ ነጋሽ
5. ሲምቦ ደጀኔ
6. ዋዳ ዲሮ
7. ሶራ ጅርማ
8. ጌቱ
9. ቢንያም

10. ባይሳ


ይቅርታ የሚል ቀልድ

በኦሮሚያ ከአስራ አምስት ሺህ ወጣት በላይ መንግስትን ባለመደገፉ በእስር ቤት ታጉሯል።
ብዙ ቦታ እስር ቤቶች ሞልተው ትምህርት ቤቶች ወደ እስር ቤትነት ተቀይረዋል። ሴቶችና ህፃናት በመንግስት የፀጥታ ሃይሎች በየቀኑ ይገደላሉ።
 
ፖለቲከኞች የሀሰት ክስ ተፈብርኮባቸው እስር ቤት ተወርውረዋል። ከድጡ ወደ ማጡ ብለሃል ፤ የሽግግር መንግስት ሃሳብ አቅርበሃል በሚል አስቂኝ ክስ የታሰረም አለ።
ይህ ሁሉ በሚሆንበት ሀገር የይቅርታ ቀን በሚል ቀልድ ጷግሜን ጀምረናል። የይቅርታ ቀን የሚለው ሃሳብ የመጣው ከአዴ አዳነች ቢሮ መሆኑን ማየትም ይገርማል። ከሁለት ወራት በፊት የኦሮሞ ፖለቲከኞችንና ሌሎችንም ፍፁም ሃሰት በሆነ ክስ ወደ እስር ቤት እንዲጋዙ በማድረግዎ መጀመሪያ እርሶ ይቅርታ ይጠይቁና እኛ እንከተላለን።
ዛሬ በተደረገው ዝግጅት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ መንግስት ላይ “ማመፅና ህገ መንግስቱን መጣስ” ሀጢአት ነው ብለዋል።
 
አምባገነናዊ መንግስት ላይ ማመፅ ሀጢአት ሆኖ አያውቅም ወደፊትም አይሆንም።
በአንድ ግለሰብ ፈላጭ ቆራጭነት ላይ የተመሰረተ አምባገነናዊ ስርአት ይህን ሁሉ ጥፋት ሲፈፅም ታላላቅ የእምነት አባቶች መኮነን ሲገባቸው ከመንግስት ጎን ሆነው ህገ መንግስት መጣስ ሃጢአት ነው ሲሉ መስማትም አሳዛኝ ነው።
ህገ መንግስቱንም ቢሆን ከመንግስት በላይ ደጋግሞ የጣሰ የለም። ለማንኛውም ይህ ሁሉ የሚዲያ ትእይንት በሚካሄድበት ወቅት በኦሮሚያ አራተኛ ዙር የእምቢተኝነት እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው። በሚዲያ ሸናኒጋንስ የሚሸወድ ህዝብ የለም።
ሀገር እንዲረጋጋ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው አንድ ክፍለ ዘመን ዘግይቶ ወደዚች ምድር የመጣውን ንጉሰ ነገስት አብይ አስቀድሞ አደብ ያስገዛ።


በጠራራ ጸሀይ የንጹሃንን ህይወት እየቀጠፈ ፣በግፍ እያሰረ፣ሴት እህቶቻችንን እየደፈረ ፣የሀይማኖት አባቶችን እየገደለ ባለ ኃይል የታወጀውን “የይቅርታ ቀን” እንደታወጀ የማይቆጠር፣ በምድርም ሆነ በሰማይ ቤት ተቀባይነት የሌለው፣ የማይጸና እና ትርጉም አልባ ነው!