“የታላቁ ሩጫ ሚሥጢራዊ መረጃ: የአዲስ አበባ ወጣት ታላቁን ሩጫ

“የታላቁ ሩጫ ሚሥጢራዊ መረጃ: የአዲስ አበባ ወጣት ታላቁን ሩጫ አልሮጠም እንድሩጡም አልተፈቀደላቸውም ይልቁን የሮጡት ሚሥጢራዊ መረጃ ይሄው ከታች በዝርዝር አስቀምጨለሀለው ለህዝብ አሳውቅ በደህንነት የተሰራውን ደባ
1. 15% ለሩጫው በደህንነት የተመደቡ ካድሬወች
2. 25% ፌደራል ፖሊሶች
3. 17.5% የአዲስ አበባ ፖሊስ ( አዲስ አበባ የሚሰራ አንድም የከተማዋ ነዋሪ ፖሊስነት አይመደብም)
4. 21% ከትግራይ መተው አዲስ አበባ የሰፈሩ ትግሬወች
5. 20% 5 ለ1 ተደራጅተው ያሉ በሊስትሮ እና አዟሪነት የሚሰሩ ከሃድያ እና ወላይታ መተው አዲስ አበባን የወረሩ ወጣቶች
6. 1.5% የወያኔን ምንነት የማያውቁ ዘገምተኛ የአዲስ አበባ ነዋሪወች
እውነት ነው፡፡ የአዲስ አበባ ወጣት ከሚኖርበትን ሰፈር ተፈናቅሎ በየጥሻው ነው፡፡ የአዲስ አበባ ወጣት ስራ አጥ ነው፡፡ በየቀበሌው እና ወረዳው በሀላፊነት እየሰራ ያለው የትግሬ እና የደቡብ ሰው ነው፡፡ የአዲስ አበባ ወጣት ሰፈሩን እንኳ ማስተዳደር አልቻለም፡፡ ለቲሸርት መግዣ ከሚያወጣ አብዛኛው ወጣት ጫት ገዝቶ እራሱን እያደነዘዘ ውላል፡፡”

Via: Eshete Kassa Zewudie


(ኢሳት ዜና–ሕዳር 18/2010)

ከሁለት ወራት በላይ የዘለቀው የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤትን ወይዘሮ አዜብ መስፍንን አገደ። ማዕከላዊ ኮሚቴው የፓርቲውን ሊቀመንበር አቶ አባይ ወልዱና ሌላ አንድ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዝቅ ማድረጉን የትግራይ ክልል ቴሌቪዥን አስታውቋል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን ተከትሎ የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሊቀመንበርነትን ላለፉት አምስት አመታት የያዙት አቶ አባይ ወልዱ ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ዝቅ እንዲሉ በመደረጋቸው ሊቀመንበርነቱንም ለሌላ ግለሰብ ማስረከብ ግዴታቸው ይሆናል።

በዚህ መሰረት ሕወሃት በቀጣዮቹ ቀናት ሌላ የፓርቲ ሊቀመንበር እንደሚመርጥ ይጠበቃል። የአሁኑ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የመሪነቱን ስፍራ ሊይዙ ይችላሉ ሲሉ አንዳንዶች ግምታቸውን ሰጥተዋል። በብዙዎቹ የህወሃት አባላት ዘንድ በፖለቲካ ንቃታቸውና በሕዝብ የማሳመን ችሎታቸው ጥያቄ ስለሚነሳባቸው ከርሳቸው ይልቅ ሌላ ግለሰብ እንደሚመረጥ ይጠበቃል። የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ሕወሃት/ማዕከላዊ ኮሚቴ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወይዘሮ አዜብ መስፍንን ከፓርቲው ስራ አስፈጻሚነት እንዲሁም ከማዕከላዊ ኮሚቴ ማገዱን ተከትሎ ከኢፈርት ዋና ስራ አስፈጻሚነት እንደሚያነሳቸውም ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሀብት የተከማቸበት በሚል የሚጠቀሰው ኢፈርት በቢሊየን ብሮች የሚንቀሳቀስ ሲሆን በዚህ ላይ የሚደረጉ ተጨማሪ ምርመራዎች እንደሚኖሩ ምንጮች ይገልጻሉ። ወይዘሮ አዜብ መስፍን ሌሎች ተጨማሪ ርምጃዎችም ሊገጥማቸው እንደሚችል ተመልክቷል። አቶ አባይ ወልዱም ከሕወሃት ሊቀመንበርነቱ ባሻገር የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንትነቱንም ሊያጡ እንደሚችል በመገለጽ ላይ ነው። አንዳንድ ምንጮች ዶክተር አርከበ እቁባይ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት እንደሚሆኑ በመግለጽ ላይ ናቸው። ሆኖም አቶ አርከበ እቁባይ የትግራይ ክልል ምክር ቤት አባል ባለመሆናቸው በሕጋዊ አጋባብ ከሄዱ መንገዱ ዝግ እንደሚሆንም መረዳት ተችሏል።

የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ይፋ ባደረገው አንድ ገጽ መግለጫ ከአቶ አባይ ወልዱና ከወይዘሮ አዜብ መስፍን በተጨማሪ አቶ በየነ ምክሩ የተባሉ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ከስራ አስፈጻሚነታቸው ተወግደዋል። ሌሎች ስማቸው ያልተጠቀሰ ሁለት አባላት ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸውም ከመግለጫው መረዳት ተችሏል። የሕወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ዘጠኝ ሲሆኑ ሶስቱ ዝቅ ብለውና ታግደው ሁለቱ ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው ጥያቄ ያልተነሳባቸው አራት ብቻ ናቸው። ከነዚህ ውስጥ አንዱ የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ሆነው የሄዱት ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በመሆናቸው ጥያቄ ያልተነሳባቸው ሶስት ብቻ እንደሆኑም መረዳት ይቻላል። የማዕከላዊ ኮሚቴው ሂስና ግለሂስ መድረክ መቀጠሉም የተገለጸ ሲሆን ሒደቱ ሳያልቅ መግለጫው የወጣበት ምክንያት

ግን ግልጽ አልሆነም።

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 18/2010)
በኦሮሚያና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እንደገና ባገረሸው ግጭት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተሳታፊ መሆናቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ንጹሃን ሰላማዊ ሰዎችን ሲገድሉ በነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይም ርምጃ መወሰዱ ታውቋል። በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ እንደገና ግጭት ማገርሸቱን መንግስት በሳምንቱ መጨረሻ ማረጋገጫ ሰጥቷል። በኦሮሚያና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አዲስ ባገረሸው ግጭት ባለፈው ሳምንት ብቻ 20 ሰዎች መገደላቸውን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ሲገልጹ የኢሳት ምንጮች በግጭቱ የሞቱት ቁጥር ወደ 70 ማሻቀቡን አመልክተዋል።
በተለይ በሞያሌ ወረዳ በነበረው ግጭት 2 የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሆኑ ኮማንዶዎች መገደል በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከፍተኛ የአጸፋ ጥቃት ማስከተሉም ተመልክቷል። ቅዳሜ ህዳር 16/2010 ቦርቦር በተባለው አካባቢ በነበረው ግጭት ደግሞ የሶማሌ ልዩ ሃይል መለዮን የለበሱ ፖሊሶች በብዛት ሲገደሉ ሶስት የመከላከያ ሰራዊት አባላትም መገደላቸው ታውቋል። በሰሞኑ ግጭት በአጠቃላይ 5 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰው ዕልቂት ወደ 70 ማሻቀቡን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
በመከላከያ ሰራዊቱ አባላትና በሶማሌ ልዩ ሃይል ላይ እያደፈጠ ጥቃት የሚሰነዝረው ሃይል ማን እንደሆነ ለጊዜው አልታወቀም። ይህ ቡድን የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይልና የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ለሚያደርሱት ጥቃት አጸፋ በመስጠት ላይ መሆኑም ተመልክቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለም በሳምንቱ መጨረሻ አሬሮ አካባቢ በአንድ ስፍራ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ በድንገት በተከፈተ ተኩስ ሁለት ሕጻናትን ጨምሮ 7 ሰዎች መገደላቸውን የኢሳት ምንጮች ከስፍራው ገልጸዋል። አምና ሚያዚያ ላይ የተባባሰው የኦሮሚያና ሶማሌ ክልል ግጭት እንደገና መስከረም ላይ ማገርሸቱ ይታወሳል። መፍትሄ አገኘ ከተባለ በኋላ እንደገና በሳምንቱ መጨረሻ የተቀሰቀሰበት ምክንያት አልታወቀም። በቀደመው ግጭት ተሳታፊ የሆኑ 98 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ሲታሰሩ 5 ሰዎች ደግሞ ከሶማሌ ክልል መታሰራቸውን የመንግስት ቃል አቀባይ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ በሳምንቱ መጨረሻ ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።


የአዜብ መስፍን ከህውሓት መታገድ፣

አንደኛ: የመለስ ራዕይ ወደ ሥላሴ መቃብር ይወርዳል። HD ከዚህ በኋላ ” ታላቁ መሪያችን” ብሎ እንዳይናገር ከአርከበ ትእዛዝ ይደርሰዋል።

ሁለተኛ: አዜብ መስፍን የስዬ አብርሃ እጣ ፈንታ ሊደርሳት ይችላል። እርግጥ ዘብጥያ ማውረዱ ዞሮ ዞሮ የኤፈርት ዝርፊያ እና ሌብነት ላይ ስለሚሽከረከር ለስብሃት በጣም ከባድ ይሆንበታል። አርከበም ቢሆን በሌብነት ከሴትየዋ የሚስተካከል በመሆኑ እስሩን ላይደግፈው ይችላል።

ሶስት: የሕውሓት ካድሬዎች ለሁለት ሊሰነጠቁ ይችላሉ። በተለይ ከሌብነቱ በላይ “የባድመ ጉዳይ” በልዩነት ጐልቶ መውጣት ከቻለ አባይ ወልዱ፣አዜብ እና ሳሞራ የኑስ በካድሬው ዘንድ ተቀባይነት ሊኖራቸው ይችላል ። ለስብሓት ነጋ የባድመ ጉዳይ ከባድ ፈተና ይሆንበታል።

አራት: በረከት ስምኦን ዳግም የመልቀቂያ መልቀቂያ ያስገባል። አርከበ እና ደብረፂዮን በትግርኛ ይስቁበታል። ስብሃት ነጋ ሥላሴ ቤተክርስቲያን ( ከአምላኩ አጠገብ) መቃብር ይምስለታል። በረኸት እንደተለመደው አፍንጫውን እየጐተተ ” ቀድሞ ወደ መቃብር ማን እንደሚሄድ እንተያያለን!!” በማለት ይዝታል ።

አምስት: አርከበ እቁባይ ወይም ወንድሙ አሊያም በስብሃት ነጋ እና በአርከበ ኔትወርክ ውስጥ ያሉ የሕውሐት ባለሥልጣናት ኤፈርትን ይቆጣጠሩታል። ደብረፂዮን በፌዴራል ደረጃ ቁልፍ ሥልጣኑን መልቀቁ ለህውሓት አደጋ ስለሚሆን የድርጅቱን ም/ሊቀመንበርነት መያዙ በቂው ሊሆን ይችላል።

ስድስት: የአዜብ መስፍን፣ አባይ ወልዱ፣ የበረከት እና ሳሞራ የኑስን ቆሽጤ ለማሳረር ተጋዳሊት ፈትለወርቅ “ሞንጆሪኖ” ( የአባይ ፀሐዬ የቀድሞ ሚስት) በፊት መስመር የመምጣት እድል ይኖራታል። ሳሞራ በአስቸኳይ በጡረታ ሊገለል ይችላል። በርካታ ጄኔራሎችም ሊባረሩ ይችላሉ።

Via: Ermias Legesse Wakjira