የቱለማ ኦሮሞና የሸዋ ስያሜ: (ሸዋ የሚለው) የኦሮሞ ቃልም ሆነ ፍቺ የሌለውና የሰፋሪ ሐይሎች ስም መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

የቱለማ ኦሮሞና የሸዋ ስያሜ: (ሸዋ የሚለው) የኦሮሞ ቃልም ሆነ ፍቺ የሌለውና የሰፋሪ ሐይሎች ስም መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

የቱለማ ኦሮሞና የሸዋ ስያሜ

ኦሮሞ ከኩሽ ህዝቦች ሁሉ አብላጫና በሰፊ መልክዓ ምድራዊ ይዞታ ላይ ተስፋፍቶ የሚኖር ሕዝብ ነው። እንደ ስፋቱና ትልቅነቱ መጠን ደግሞ ኦሮሞ የተለያዩ ጎሣዎች አሉት። እነርሱም ቱለማ :መጫ :ጉጂ :ቦረና :ገብራ :አርሲ :ኢቱ :ሁምበና: ራያ: የጁ: ከረዩ ሊበን-ወዘተ በመባል ይታወቃሉ። ከነዚህ ዉስጥ የቱለማ ጎሣ አንደኛው ነው። የቱለማ ኦሮሞ በኢትዮጽያ እምብርት ሰፊ የሆነ አካባቢና እንዲሁም ከጥንት[ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ4000 B.C] ጀምሮ የኩሽ ህዝቦች እንደ አንድ ቋንቋ(ኩሽ)ተናጋሪ ህዝብ ሲኖሩበት በነበረ ሥፍራ ላይ እንደ ኦሮሞነቱ ብሎም እንደ ኩሽነቱ ተንሰራፍቶና ሰፍሮ የነበረና ዛሬም በመኖር ላይ ያለ የኦሮሞ አብይ ጎሳ ነው። ከአንዳንድ የኦሮሞ ትዉፊቶች መረዳት እንደሚቻለው ይህ የኦሮሞ ጎሣ በመሃል ኦሮሚያ የሰፈረና ከጊዜ በኋላ ግን ከዚሁ ማዕከል በመነሣት በሁሉም አቅጣጫዎች ለተሰራጩ ኦሮሞዎች ዋና ግንድና መሠረት እንደ ነበሩ ይገለጻል። ለምሳሌ የመጫና ቱለማን የትውልድ ቦታን እንደ አንድ አባት ልጆች በመውሰድ በአሁኑ ጊዜ መናገሻ ወይም ከኮሎቦ የሚገኘው የአጌዱ ጋራ ላይ እንደነበረና በኋላ እንደ ተራራቁ የኦሮሞ አዛውንቶች ይገልጻሉ።

የተለያዩ የታሪክ ፀሐፍት በተለያዩ ጊዜያት በመራጃ በማስደገፍ እንዳረጋገጡት ዛሬ የቱለማ ኦሮሞ(የሸዋ ኦሮሞ)ና የሸዋ አምሃራ የሚኖርበት አካባቢ ቀድሞም የኦሮሞ እምብርትና የጥንት የገዳ አስተዳደር የተጀመረበት ከመሆኑም በላይ ኦሮሞ እንደ አንድ ሕዝብ ከሌሎች የኩሽ ወገኖቹ በመገንጠል ራሱን ችሎ የወጣበት አካባቢም እንደሆነ የረጅም ዘመን ታሪካቸውን በመጥቀስ ያወሳሉ። በመኻከለኛው ክፍለ ዘመን የኦሮሞ ከፊሉ ሕዝብ በክርስቲያኑ መንግሥት ተገፍቶ ከኖረበት የሰሜን ሸዋ ክልል ማዕከሉ ወደ ደቡብ ከመገፋቱ በፊት የቱለማ ኦሮሞ ይዞታ የአባ ሙዳ (ቃሉ) የኦሮሞ ሐይማኖትና ፖለቲካ ማዕከል ሆኖ ሲያገለግል እንደቆየና ዋና ዋና የሙዳ ሥፍራዎችም በዚሁ ሸዋ ዉስጥ እንደነበር ይነገራል። ነገር ግን የግዥ መደብ ታሪክ ጸሐፊዎች በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተካሄደው ተሐድሶና የኦሮሞ ህዝብን እንቅስቃሴ እንደ መጤና እንግዳ በመቁጠር [የኦሮሞ] ፍልሰት ወይም ወረራ ሲሉ ሲዘግቡ ቆይተዋል ነገር ግን የነበረው እንቅስቃሴ የገዥ መደብ ጸሐፊዎች ስደት ይበሉት እንጂ በዘመኑ የነበረው ሕዝቡ ወደነባር ቀኤው የመመለስ ሂደት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

የቱለማ ኦሮሞ ይዞታ የዳበረና ለሰውና እንስሳትም ተስማሚ በመሆኑ የኦሮሞ ጎሣዎችም ሆኑ ሌሎች ወገኖች በተለያዩ ጊዜያት ቀደምት መኖሪያ ሥፍራቸውን በመተው ወደዚህ ክልል ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ታሪክ ያስገነዝባል። ከጊዜ ወደ ጊዜ ከሚካሄዱት ፍልሰት የተነሣ የቱለማ ኦሮሞ አጎራባች ሕዝቦችና እንዲሁም ከሩቅ ቦታዎች ፈልሰው የመጡት በዚሁ ጎሣ ይዞታዎች ላይ ሲሰፍሩ እንደነበረም እሙን ነው። ስለዚህ ይህ የ”ሸዋ” ስያሜ አመጣጥ ከእነዚህ የተለያዩ ወገኖች የተገኘ ስያሜ እንደሆነ ይነገራል። ሆኖም ግን ሸዋ የሚለው ስም በማንና መቼ እንደ ተሰየመ የተለያዩ መላምቶች(ሃሣቦች) መኖራቸው አልቀረም።

ካሉት ሃሣቦች ውስጥ አንደኛው ከደቡብ አረቢያ ወገን በመሃከለኛው ዘመን (ከ10ኛው እስከ 14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ባለው ጊዜ ውስጥ) ፈልሰው ከመጡ ህዝቦች ጋር የተያያዘ ነው። የታሪክ ሰነዶች እንደሚያብራሩት ለመጀመሪያ ጊዜ በቱለማ ምድርና መሃበረሰብ ውስጥ የሠፈሩ የውጭ ሰዎች ከመሃከለኛው ምሥራቅ የመጡ አረቦች እንደሆኑ ይነገራል። እነርሱም ለንግድ ሥራና የ እስልምና ሃይማኖትን ለማስፋፋት የመጡ ነጋዴዎች በተለይም አረበ-ገባ እና ወረሼ የተባሉ ወገኖች እንደሆኑ ይነገራል። ከዚህም በመነሳት ወረ ሼ ከሚለው ስም “ሸዬ” የሚለው ስም በጊዜ ብዛት “ሸዋ” ወደሚለው ስያሜ እንደተቀየረና ለዚህም ለማስረጃም ያህል የአያሌ አካባቢ ስሞች ወደ ዓረቦችና አይሁዶች ስምና ቃል እየተቀየረ እንደነበረ ይታወቃሉ። ከነዚህም መኻከል ወደ ሰሜን ሸዋ (ቱለማ) ያሉትን አያሌ የመንደር ስሞች መጥቀስ ይቻላል። ለምሳሌ ያህል ዳንያ ; ኢፋት (ይፋት) ; ኤፌሶን ; ኤፍራታ ; ማመዶች; ወረሼክ ; ማክሱማይት : ደብረሲና :ማፉድ: አንፆኪያና የመሳሰሉትን መጥቀስ ይበቃል። በይበልጥ ግን ከቱለማ ኦሮሞ አካባቢዎች ሸዋ ወዳ ተባለው ስያሜ (ስም) የተቀየሩት በይፋት አካባቢ የሚገኙ ውስን የ ዓረብ ሰፈሪ መንደሮች እንደሆኑ ተጠቅሷል። ይህም ከዓረቦች ስያሜና ሰፈራ ጋር የተያያዘ መሆኑ ይነገራል።

ከጊዜ በኋላ የሸዋ ነገሥታት ነን ብለው ራሳቸውን በመሠየም በተለይም እንደነ ስብስቴ ነጋሢና ተከታታይ ተወላጆቹ በሐይል የወረሱትና የግላቸው ያደረጉት አካባቢዎችን ሁሉ ቀደም ሲል የከረዩ ; ጂሌ ; አርጡማ ; ቆሪ ; ፉርሴ ; ሊበን ኦሮሞዎች ጥንት ሐገርና እርስት መሆኑ ይታወቃል። እነዚህ ወገኖች የኦሮሞን ይዞታ በኋይል በመቆጣጠር ጠንካራ ኋይልና የሀብት ይዞታ ፈጥረው የሕዝቡን እምነትና (ሃይማኖት) ባህል በማስተው በዘዴና በሐይል ከራሳቸው በመቀላቀል በተለይም እንደነ መንዝ (የላሎና ማማ ምድር : ግቼ ; ቂያ: ሞላሌ: ዱሙጋ: ባሶና ወራናን) የመሳሰሉ ሰፊ መሬት ቀደምት የሸዋ መሪዎች እነ ስብስቴ ነጋሤ :ሣህለ ሥላሴና እንደነ ኋይለ መለኮት እንዲሁም ምኒሊክ 2ኛ ያሉ በአውሮፓ መሳርያ በመታገዝ በተከታታይ ኦሮሞን ከአባት ሀገሩ በመንቀል ሀገር ማቅናት በሚል ስም ዘርፈውታል። ከዚህም በመነሳት በተለይም ከአፄ ምኒሊክ 2ኛ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ቱለማ የሚለው ስም “ሸዋ” በሚለው እየተተካ መምጣቱን የተለያዩ ፀሐፍት ይመሰክራሉ። የሸዋ ስም መስፋፋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣና ከሰሜን ምሥራቅ የቱለማ ሀገር ተነሥቶ እስከ ደቡብና ደቡብ ምዕራብ እስከ መኻከለኛ የመጫ ኦሮሞ ይዞታን ጨምሮ ይጠራበት እንደነበረ ይታወቀል።

ሌላው ሸዋንና ስያሜውን አስመልክቶ ያለው ሠነድ የአለቃ ወልድ ክፍሌን የአማርኛ መዝገበ ቃላት ጠቅሶ ደስታ ተ/ወልድ የፃፈው ነው። እርሱም እንደሚከተለው ገልፆት ነበር።

“ሺዋ /ሺሕዋ/ የሴት ስም የግሼ ባላባት : የወሎ ባላባት የሴት ልጅ ምስ ብዙ ልጆች ስለወለደች አባቷ ልጄ ሽኋዋ አሏት። በዚህ ምክኒያት የልጆቿ ሀገር ሸዋ ተብሎ ተጠራ ይባላል። ሸዋ ከግሼ ጀምሮ ወንጭት በመለስ እስከ አዋሽ ነው።”

የሸዋ ግዛት ከጊዜ በኋላ ግሼን መጨመሩ (የስሙ ከዚያ ሀገር ጋር መተሳሰር ሲገልጽ) ይህ ስም ከዚያ ሀገር ግንኙነት ሊኖረው ይችላል ወደሚለው እንድምታ ያደርሰናል። ሆኖም ግን ይህንን የሚያረጋግጥ አጥጋቢ መረጃ አልተገኘም።

እንግዲህ ከተለያዩ ምንጮች ከቀረቡ ገለጻዎች በመነሳት ለቃሉ ምንጭነት የትኛዉ ትክክለኛ እንደሆነ ማነጻጸር ተገቢ ይሆናል። ከዚህ ውጭም ቱለማ የሚለው ስም ሸዋ ከሚለው ስም ቀደምትነት እንዳለው መገንዘብ አያዳግትም። ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ወደፊት ጥልቅ ጥናት መደረግ አለበት: ሆኖም ግን ወደ እውነት የተቃረበ ነው ወይም ሚዛን ደፍቷል ሊባል የሚችለው ከዓረብ ሀገር ከመጡ ሰፋሪዎች ጋር ተያይዞ የቀረበው ጭብጥ ነው። ከዚህም በመነሣት ይህ ሸዋ የተባለው ስም ከትንሽ ቦታ ተነሥቶ በመስፋፋት ወደ ሌሎች አካባቢዎችም ያደገና መነሻው የቱለማ ኦሮሞ ጥንተ ሀገር መሆኑን እንረዳለን። ቢሆንም ቅሉ ስሙ (ሸዋ የሚለው) የኦሮሞ ቃልም ሆነ ፍቺ የሌለውና የሰፋሪ ሐይሎች ስም መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።


‹የኦሮሞ ጥያቄ› ምንድ ነው?” የሚለው ጥያቄ ቀላል የሚመስል ነገር ግን ከባድ ጥያቄ ነው፤ ተደጋግሞ ሲነሳም ይደመጣል። በዚህ ሳምንት ይህንኑ ጥያቄ በመያዝ ከደርዘን የበለጡ የኦሮሞ ሕዝብ ማኅበረ-ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን የሚያነሱ ወይም ለመልሶቻቸው የሚሟገቱ ሰዎችን አነጋግሬያለሁ።

“‹የኦሮሞ ጥያቄ› ምንድ ነው?” የሚለው ጥያቄ ቀላል የሚመስል ነገር ግን ከባድ ጥያቄ ነው፤ ተደጋግሞ ሲነሳም ይደመጣል። በዚህ ሳምንት ይህንኑ ጥያቄ በመያዝ ከደርዘን የበለጡ የኦሮሞ ሕዝብ ማኅበረ-ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን የሚያነሱ ወይም ለመልሶቻቸው የሚሟገቱ ሰዎችን አነጋግሬያለሁ። በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች ጨምቄ የማቀርባቸው ጥያቄዎች ያነጋገርኳቸው ሰዎች “የኦሮሞ ጥያቄ” እነዚህ ናቸው በሚል በተደጋጋሚ ከነገሩኝ መካከል አራቱ ዋነኞቹ ናቸው። ለእያንዳንዱ ጥያቄ የማስቀምጠው ማብራሪያም በተጠያቂዎቹ የተሰጡኝን ማብራሪያዎች ለዚህ ጽሑፍ በተመቸ መልኩ አሳጥሬው ነው። የጽሑፉ ዓላማ በፖለቲካ ተዋስዖው ውስጥ የሚነሱትን ጥያቄዎች እና ውይይቶች ሊያግዝ የሚችል ፍሬ ሐሳብ ለማበርከት ነው።

መንደርደሪያ
ብዙዎቹ የጥያቄዬ መላሾች እያንዳንዱ ጥያቄ ያለ ጥቅል ዐውዱ ትርጉም እንደማይሰጥ ይናገራሉ። የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት (ኦሮሚያ) እና የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት (ኢትዮጵያ) መካከል ያለው ግንኙነት ታሪካዊ ጉዞን በጥቂቱ ምሥል የሚሰጥ ዐውድ ለጥያቄዎቹ ግልጽነት የግድ አስፈላጊ ነው። የአንድ አስተያየት ሰጪ ገለጻ የሁሉንም ሐሳብ ይጠቀልለዋል። የኦሮሞ ጥያቄ የሚመነጨው አንድም ከአገረ መንግሥቱ የቅቡልነት ደረጃ፣ አንድም ደግሞ ከዴሞክራሲያዊነት ደረጃ ነው። የአገረ መንግሥቱ ቅቡልነት ቀውስ የሚመነጨው “አገሩ እኛን የሚወክል እሴት፣ ትዕምርት እና ትርክት የለውም” ከሚል ሲሆን፣ ‘የዚህ መልሱ ዴሞክራሲያዊ አይደለም’ ይላሉ። የፌዴራላዊ መዋቅሩ የተፈጠረውም ይህንን የቅቡልነት ችግር ለመቅረፍ ሲባል ነበር። የዴሞክራሲያዊነት ቀውሱ የሚመነጨው ደግሞ የተለወጠው መዋቅር የታለመለትን ግብ እንዲመታ ለማድረግ ሲባል ነው። እንደ አስተያየት ሰጪው የአገረ መንግሥቱ ቅቡልነት ቀውስ ሲጎለብት ሉዓላዊ አገር መመሥረት እንደ ጥያቄና የመፍትሔ ሐሳብ እየጎላ ይቀርባል። የኢትዮጵያ አገረ መንግሥት የቅቡልነት ቀውስ እየቀነሰ ሲመጣ ደግሞ የዴሞክራሲያዊነት ጥያቄ ይጎላል።
ጥያቄዎቹ በዴሞክራሲ እና በአገረ መንግሥቱ መሠረታውያን ላይ ወዲያ እና ወዲህ ከማለታቸውም ባሻገር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለወጡ መምጣታቸውንም አስተያየት ሰጪዎቹ ይናገራሉ። በ1950ዎቹ የተነሱ ጥያቄዎች እና ዛሬ ያሉት አንድ አይደሉም፤ ለዚህም ነው ጥያቄዎቹን ደጋግሞ ማንሳት እና መለየት የሚያስፈልገው።
በዚህ መሠረት የኦሮሞ ዛሬያዊ ጥያቄዎች ከታች የተዘረዘሩት ናቸው። በዝርዝሩ ውስጥ ቀድመው የመጡት መልስ በሰጡኝ ሰዎች ባነሷቸው ጥያቄዎች ድግግሞሽ ልክ ነው። የጥያቄዎቹ መነሻ ታሪካዊ እና ወቅታዊ ዐውዶች አንድ ዓይነት በመሆናቸው አራቱን ጥያቄዎች እርስ በርስ የሚያመሳስሏቸው ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ገለጻው እና ማደራጀቱ የእኔ ቢሆንም፣ ሐሳቡ ግን የኦሮሞ ሕዝብ ጥቅም ተሟጋቾቹ ነው።

ጥያቄ አንድ፦ የትርክት እና ትዕምርት ጥያቄ

የኦሮሞ ጥያቄዎች በአብዛኛው የሚመነጩት በምሥለ ኢትዮጵያ ውስጥ የኦሮሞ ሕዝብ ራሱን አያገኝም ከሚል ይመነጫሉ። የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ትርክቶችም ይሁኑ ትዕምርታዊ መገለጫዎች ኦሮሞን ወይ ይገድፋሉ አልያም በአሉታዊ መንገድ ይገልጻሉ። እነዚህ ትርክቶች ከታሪክ መጽሐፍት ገጾች እስከ ትምህርት ስርዓቱ፣ ከቤተ መንግሥት እስከ ቀበሌ፣ ከሰንደቅ ዓላማ እስከ አደባባይ ሐውልቶች ድረስ ይዘልቃሉ። ትርክቶቹ እና ትዕምርቶቹ የኦሮሞን ገጽታ አካታች እና በአግባቡ ገላጭ ተደርገው መስተካከላቸው ወይም መካተታቸው ለብዙዎቹ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።
የትርክት እና ትዕምርት ጥያቄው ቀድሞ የነበሩትን ታሪካዊ ትርክቶች መከለስ እና የኦሮሞ ሕዝብ ትውፊታዊ እሴቶችንና ትዕምርታዊ መገለጫዎችን ማካተት ላይ ብቻ ላይ እንደማይወሰን ተሟጋቾቹ ይናገራሉ። የኦሮሞ ታጋዮች እነዚህን ጥያቄዎች ይዘው ትግል ማድረግ ከጀመሩ ወዲህ በርካታ ሰብኣዊ እና ሥነ ልቦናዊ መስዋዕትነቶች ተከፍለዋል፣ በርካታ ጀግኖችም ተፈጥረዋል። እነዚህ ትግሎች፣ መስዋዕትነቶች እና ጀግኖች በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ዕውቅና ማግኘት አለባቸው።

ጥያቄ ሁለት፦ የቋንቋ ጥያቄ

የቋንቋ ጥያቄ በኦሮሞ ሕዝብ ጥቅም ተሟጋቾች ዘንድ እንደ እኩል አድራጊ (equalizer) ነው የሚቆጠረው። ኦሮምኛን የፌዴራል መንግሥቱ አንድ የሥራ ቋንቋ ማድረግ ከባሕል ጋር ተያይዘው የሚመጡትን ጥያቄዎችንም የመመለስ አቅም አለው። ብዙዎቹ የኢትዮጵያ ከተሞች መግባቢያ ቋንቋቸው አማርኛ ነው። ይህም የተለመደው የከተሞች መሥፋፋት በሚከሰትበት ጊዜ በዙሪያው ያሉ ባሕላዊ ልማዶች እና ወጎች በከተሜው ልማድ ይዋጣሉ። በኦሮሚያ ደግሞ ከተሞቹ ዙሪያ ያሉት የኦሮምኛ ተናጋሪ ገበሬዎች በመሆናቸው ቋንቋውም ባሕሉም አብሮ የመዋጥ አደጋ ይጋረጥበታል። ኦሮምኛ የፌዴራሉ የሥራ ቋንቋ መሆኑ ከተሞችን ሁለት ቋንቋ ተናጋሪ (Bi-lingual) በማድረግ ችግሮቹን በመጠኑ ይቀንሳል።
የቋንቋ ጉዳይ የኢኮኖሚ ጥያቄን ይመልሳል ብለው ተሟጋቾቹ ያምናሉ። የፌዴራል ተቋማት እና የግል ዘርፉ የተሠማራባቸው ከተሞች የመግባቢያ ቋንቋ አማርኛ መሆኑ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች በነዚህ ቦታዎች የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማግኘት አማርኛ ተናጋሪ መሆን አለባቸው። ይህ ተግዳሮት ኦሮምኛ የሥራ ቋንቋ ቢሆን የሚቀረፍ ነው።

ጥያቄ ሦስት፦ የአገር ባለቤትነት ጥያቄ

የኦሮሞ ሕዝብ የገዛ አገሩ ባለቤት አይደለም፤ መጀመሪያ ይህንን ማረጋገጥ አለበት የሚለው ጥያቄ አንዱ ነው። አሁን ባለው ሁኔታ የኢትዮጵያ አገረ መንግሥት የኦሮሚያ አገረ መንግሥትን ዕጣ ፈንታ ይወስናል እንጂ፣ ኦሮሚያ (እንደ አንድ ክልላዊ መንግሥት) የሥልጣን ባለቤት ሆና የኢትዮጵያን ዕጣ ፈንታ በሚገባት መጠን እየወሰነች አይደለም። የፌዴራል መዋቅሩ የተፈጠረው አባል መንግሥታቱ (ኦሮሚያን ጨምሮ) የኢትዮጵያን መንግሥት አካሔድ እንዲወስኑ ቢሆንም እየሆነ ያለው ተቃራኒው ነው የሚል ነው።
ይህ በፖለቲካ ኢትዮጵያ ኦሮሚያን ቅኝ ገዝታለች ከሚል ትርክት የሚመጣ ሲሆን፥ ምላሹም ነጻ መውጣት፣ ወይም ሉዓላዊ አገር መመሥረት ነው የሚለው ነው። ይህ የሉዓላዊነት ጥያቄ የኦሮሞ ሕዝብ ያሉትን በአገር በቀል ስርዓት የመተዳደር ጥያቄ ጀምሮ፣ የመሬት ባለቤትነትን የመሳሰሉ የኢኮኖሚ ጥያቄዎች፣ ባሕልን የማሳደግ ጥያቄ፣ የአዲስ አበባ ባለቤትነት ጥያቄ እና የመሳሰሉትን መልስ ያስገኙለታል ተብሎ ይታመናል። በዚህ ረገድ የኦሮሞ ሕዝብ ኦሮሚያ ሉዓላዊ አገር ብትሆን የሚያገኘውን ነጻነት እና ጥቅም በፌዴራል መዋቅርም ይሁን በሌላ መንገድ ከኢትዮጵያ ማግኘት አለበት የሚል ጥያቄ ነው።

ጥያቄ አራት፦ የሰላምና ፍትሕ ጥያቄ

የኦሮሞ ሕዝብ ጥንትም ሆነ ዛሬ የሚያስቀድመው ጥያቄ የሰላም ጥያቄ ነው። ‘ነጋ’ ማለት ‘ሰላም’ ማለት ሲሆን፥ የማኅበራዊ ሕይወቱም አስኳል የሆነ ቃል ነው። ከዕለታዊ ሠላምታ ጀምሮ እስከ አረጋውያን ምርቃት ድረስ የሚጠይቀው እና የሚመኘው ሰላም ነው። ሰላምታው በግል ደኅንነት ጀምሮ እስከ ሀብት ንብረትና አካባቢ የሚዘልቅ ነው። ሃይማኖታዊ ትውፊቶቹ ውስጥም የሚንፀባረቁት የሰላም ጥያቄዎቹ ናቸው። ነገር ግን ይህ የኦሮሞ ሕዝብ የሰላም ጥያቄው በፖለቲከኞች በቅጡ ግንዛቤ አላገኘም፤ ስለሆነም የሚፈልገውን ሰላም ማግኘት አልቻለም።
በሌላ በኩል ለመብት ተሟጋቾቹ ፍትሕ ሰላም ለማምጣት ወሳኝ የኦሮሞ ጥያቄ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ በአስተዳደራዊ በደሎች ምክንያት መድልዖ ሲፈፀምበት የነበረ እንደመሆኑ እነዚያ መድልዖዎች እና በደሎች ፍትሕ ካላገኙ በስተቀር የሚመኘውን ሰላም አያገኝም።

መዝጊያ

ይህንን ጥያቄ ያቀረብኩላቸው የኦሮሞ ሕዝብ ጥቅም ተከራካሪዎች የተናገሯቸው ብዙ ቢሆኑም በኔ አረዳድ ሲጨመቁ ከላይ የተዘረዘሩት አራቱ ዋና ጥያቄዎች ሆነው ይወጣሉ። ከነዚህ በተጨማሪ ‘የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጥያቄዎች ናቸው’ ብለው የሚያነሷቸው የነጻነት፣ የዴሞክራሲ፣ የፍትሕ፣ የኢኮኖሚ እና ሌሎችም ጥያቄዎች አሉ። በተለይ የኦሮሞ ሕዝብ ብቻ ብለው የነገሩኝን ለመለየት ሞክሬያለሁ። በተጨማሪም ጥያቄዎቹ መልስ ማግኘት ይችላሉ በሚለው ላይ ሰፊ ልዩነት አላቸው፤ ነገር ግን በኢትዮጵያ ማዕቀፍ ውስጥ እና ከኢትዮጵያ በመነጠል በሚል በሁለት ሊከፈሉ ይችላሉ። ብዙዎቹ መልሶች የኦሮሞ ጥያቄዎች በኢትዮጵያ ማዕቀፍ ይመለሳሉ በሚል የተሰጡኝ ናቸው።

በፈቃዱ ኃይሉ
በዚህ አምድ የቀረበው አስተያየት የጸሐፊውን እንጂ የዶይቸ ቬለን «DW» አቋም አያንጸባርቅም።


አርቲስት ዳዲ ገላንን የበላው አውሬ ማን ነው?

አርቲስት ዳዲ ገላንን የበላው አውሬ ሀጫሉን የበላው አውሬው በንጉስነት ቅዠት ውስጥ ያለው አብይ አህመድ ነው። ለማስረጃነት ያሉትን እውነታዎች እንደርድር
• የአርቲስት ዳዲ ገላን የአርት ስራዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ፀረ ነፍጠኛ እና የነፍጠኛው ስርአት መስራች እና ቁንጮ በነበረው አጤ ሚንሊክ ላይ ያነጣጠሩ ናቸው።፡ይህ አይነት ስራ ደግሞ በአብይ ለመታሰርም ለመገደል ከበቂ በላይ ምክንያት ነው
• አርቲስት ዳዲ ገላን የተገደለው አንድ ሆቴል በምረቅ ላይ ሳለ መድረክ ላይ እየተጫወተ እያለ በተተኮሰበት ጥይት ነው። ይህ ግድያ የተቀነባበረ ግድያ መሆኑን አመላካች ነው።
• አርቲስት ገላንን ገደለው የተባለው ተጠርጣሪ “መንግስት” በቁጥጥር ስር አዋልኩት ከማለት በቀር ምንም አይነት የፍርድ ሂደት ሲካሄድ አልሰማንም አላየንም።
• ከሁሉም በላይ የአርቲስት ዳdhi ገዳይ በገንዘብ ተገዝቶ እና ተልኮ ስለመሆኑ የዳdhi አባትን ንግግር ማስታወሱ በቂ ይመስለኛል። አባቱ እንደተናገሩት ዳdhiም ሆነ እሳቸው ገዳይ ከተባለው ሰው ጋር ምንም አይነት ግጭት እና ጥላቻ እንደሌላቸው ገልፀዋል። በገንዘብ ተገዝቶ ሊሆን እንደሚችልም ተንግረው ነበር።

ስለዝህ ዳዲ ገላን የገደለው የነፍጠኛው መንግስት አብይ አህመድ ነው።
እዝህ ጋር አስምሬበት ማለፍ የምፈልገው ለአብይ አህመድ ሰውን መግደል እና ማስገደል የሚቸግረውም ያሚያሳስበው አይደለም። ይልቁኑ መደበኛ ተግባሩ ነው። ወደ ኋላ ዞር ብለን ታሪኩን ስናይ አብይ ሰዎችን መግደል እና ማስገደል የጀመረው ገና የ17/18 አመት ወጣት እንደነበር ነው። 1992 በአጋሮ እና በበሻሻ ብዙ ሰዎችን አስገድሏል። ቀጥሎም ወደ ወለጋ በማምራት ብዙ ኦሮሞዎችን ኦነግ ናቸው በማለት ገድሏል አስገድሏል። በ2004/2005 በበሻሻ ውስጥ በቤተክርስቲያን ላይ ደባ በማድባት ቤተክሪስቲያን እንዲቃጠል አድርጎ የብዙ ሰዎች ህይወት እንዲጠፋ አስደርጓል። በአጠቃላይ ለአብይ ሰዎችን መግደል እና ማስገደል ያደገበት መደበኛ ተግባሩ ነው።
ከአርቲስት ዳዲ ገላን፡ስራዎች አንዱ የሆነው እናድምጠው።
justice for oromo people
#HaacaaluuHundeessaa
#FreejawarMohammed
#FreeBakeleGerba #FreeAllPoliticalprisoners
#stopKillingOromos
#FreeOromia
#AbiyMustGo
#OromoProtests
#OromoRevolution
#FREE_OMN_JOURNALISTS


ሸሸመኔ
“ሻሸመኔ ተክለኃይማኖት የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሙሉ ግቢዉን በልመጡ ባንዲራ ግጥግጥ አድርጎ ሞልቶታል፤ይህን ሚና የሚጫወተዉ በአሁን ሰዓት የተሾመዉ የቀድሞዉ የወያኔ ዘመን የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ የነበረዉ ስንታየሁ የሚባል ሰዉ ሲሆን በወያኔ ዘመን ብዙ ቄሮ ያስፈጀ ሰዉ ነዉ፥አሁንም ብዙ የጦርነት አጫሪነት ሥራዎችን ጀምሯል፤ሻሸመኔ ላይ በጀዋር አቀባበል ቀንም በደኅንነቶች በተሰቀለዉ ሰዉ ላይ የእርሱ እጅም አለበት፡በዕለቱ የተቃጠለችዋንም መኪና የያዘዉ ይኸዉ አሁን የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ተደርጎ የተሾመዉ የቀድሞዉ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ የነበረዉ አቶ ስንታየሁ ነዉ”።