የተመጣጣኝ ሀይል ፖለቲካ መባቻ እና መፈራገጦች!! ከሀዋሳ ፣ ሸገር እሰከ ነዜርላንድ ..አምስተርዳም የተዘረጋ ወጥመድ!!

የተመጣጣኝ ሀይል ፖለቲካ መባቻ እና መፈራገጦች!!
ከሀዋሳ ፣ሸገር እሰከ ነዜርላንድ….አምስተርዳም የተዘረጋ ወጥመድ!!
====================
በታሪኩ ለማ
ክፍል 1
…..ደቡብ ክልል ተመጣጣኝ ሀይል ወይስ ክልላዊ መንግስት ክልሉ ከመመስረቱ በፊት የራሳቸው መሪ ድርጅት ያላቸው 5 ክልሎች ነበሩ፡፡ ህወሀት ደቡብ ክልልን ለኦሮሞ እና አማራ ተመጣጣኝ ሀይል እንፍጠር በሚል ስሌት የተፈጠረ የብሄር ብሄረሰቦች እጎራ እንደነበር ይታወቃል። ሁሉም በክልሉ የሚኖሩ ህዝቦች ስርዓቱን እያመለኩ ያ ስርዓት ካልተመለሰ የብሄሮች እኩልነት ጉዳይ ገደል እንደሚገባ በማሳመን ክልሉንና መሪ ድርጅቱን የህውሃት 2ኛ ካምፕ አድርጎ ለማስጠበቅ ከፍተኛ ትግል ሲደረግ ነበር። ይህ ሲሆን ሁሉም ምልምል ካድሬዎች 56ቱንም ብሄር ጠፍንገው እንድዪዙ ተልኮ ተሰቷቸው በደህዴን ጓንት የህወሃት እጅ ሆነው ሲያገለግሉ ነበር ። ይህን እውነታ ለማስተዋል ከአብይ በፊት የነበረውን የክልሉን ፖለቲካዊ አስተላለፍ መረዳት በቂ ይመስለኛል። ህወሃት በደኢህዴን እና ደቀ መዝሙሮቶቹ ትልቅ እምነት ነበረው። ለዚህም በተለይ በለውጡ ዋዜማ እና ከዛ በፊት በነበሩ ጊዜያት የደህዴን አመራሮች በፌደራል ስልጣን እንዲይዙ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ስያደርግ ቆይቷል። ለዚህም ከሁሉም ብሄሮች የተወጣጡ አመራሮች እርስ በእርስ እንዲጠራጠሩ በማድረግ ስየጣላ እና ስያስታርቅ በሸምጋይነት እና አቅጣጫ ሰጭነት በመሀል ሲተውን ነበር(ወያኔ)፡፡ ይህ ሲሆን ለከፍተኛ ስልጣን ስያጫቸው የነበሩ አመራሮች በነርሱ አጠራር የክልሉን አንድነት ለማስጠበቅ ከፍተኛ ሚና ተጫወቱ ያላቸውን አመራሮች እንደነበር ማስታወስ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ በ1994 አሁን ያለው አከላለል ፍትሃዊ እንዳልሆነ በማስረዳት በተለይም ሲዳማ ክልል እንዲሆን ሲታገሉ የነበሩ ወጣቶችን በመሪ ተወናይነት ያስጨፈጨፈውን ሀይለማርያምን የክልሉን አንድነት ጠብቋል(ተመጣጣኝ ሀይል ፈጥሯል) በሚል ግምገማ ወደ ፌደራል በከፍተኛ አምጥቶ የሞት ስንቁን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ማዳረሱ አይዘነጋም፡፡በተመሳሳይ 1998 እና 2004 ዳግም ያገረሸውን የክልል ጥያቄ አኮላሽቷል በሚል የጀግና ስም በሲዳማ ጥያቄ expense ሽፈራውን በከፍተኛ ሹመት ወደ ፌደራል አመጡት፡፡ ከዚህ በተቃራን ‘’ህዝቦች ለየትኛውም ድርጅት መጠቀምያ መሆን የለባቸውም ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር አለባቸው’’ ብለው የሚያምኑ አመራሮችን ልክ ፌደራል ላይ የኦህዴድ ጠንካራ የለውጥ አመራሮች ይፈረጁ እንደነበር ሁሉ ‘’ጠባቦች ተገንጣዮች’’ እየተባሉ ከሀገር እንዲሰደዱ  ይደረግ ነበር፡፡ የተቀሩት በተለይም በህዝብ ዘንድ መጠነኛ ፍቅር እና እምነት ያላቸውን አመራሮች እንዳይወጡ ትንሽዬ የስራ ሹመት በመስጠት እንዳይወስኖ የፓርቲ ስልጣን በመከልከል በግዞት አቆይተዋቸዋል፡፡ ለዚህ እንደምሳሌየሚጠቀሱት አቶ ደሴ ዳልኬ ናቸው፡

ሁሉም የክልል ርዕሰ መስተዳደሮች ልባል በሚችል ደረጃ ሲሆን ሊቀንበር ካልሆነም ብያንስ የፓርቲ ም/ሊቀንበርነት ማዕረግ በመያዝ የፓርቲና የመንግስት ስልጣን ይዘው ክልሎችን ሲመሩ ደሴ ዳልኬ ግን ከአጀንዳ ተቀባይነት በቀር ምንም አይነት የመወሰን ስልጣን እንዳይኖረው ከፓርቲ ስልጣን የተገለለበት ሁኔታ ነበር፡፡ አቶ ሚልዮን ህዝብ ይወደዋል ተብሎ ስለተሰጋ ከህዝብ እና ከፓርቲ ተገሎ ህዝቡን በተፈለገው መልኩ ልያገለግል እንዳይችል ተድረጓል፡፡ በተመሳሳይ የሌሎች ጭቁን ብሄሮች እና ህዝቦች ውግንና ያላቸው አመራሮች የውሳኔ ሰዎች አልነበሩም፡፡ እነዚህ የተገለሉ ቡድኖች ሀገራዊ ለውጡን ከሩቅ እና ከቅርብ ሆነው እየተከታተሉ እንደነበር ብዙ የወታወቃል፡፡ይህ በንዲህ እያለ ሀገራዊ ለውጥ ይመጣል፡፡ አብይ ወደ ስልጣን እንዲመጣ ከኦህዴድ እና ብአዴን በተጨማሪ 50+ ድምጽ ማግኘት ነበረበት። ስለዚህ አንድ የደኢህዴን ቡድን ከህውሃት ጋር የነበረውን ዘላለማዊ ቃልኪዳን አጋጣሚውን በመጠቀም ማፍረስ ነበረበት፡፡

ይህን ማድረግ ደኢህዴን ከቆመለት አላማ አንጻር ምን ያህል ዋጋ ልያስከፍል እንደሚችል ማወቅ ከባድ አይደለም። በመሆኑም የዶ/ር አብይ ምርጫ በይፋ ደኢህዴን ከተልኮው እና ከአላማ አንጻር ለ2 እንደከፈለ ማወቅ ይቻላል። ስለዚህ ከዚህ ሃገራዊ ለውጥ ጀርባ አንድ ያልተነገረለት ታላቅ ጀብድ ስለ መኖሩ ግልጽ ነው። በወቅቱ እጄቶች በኦሮምያ እና
አምሀራ የነበረውን ለውጥ ወደ ደቡብ ለማምጣት ከፍተኛ ሀገራዊ ተልዕኮ አንግበው የሞት ሽረት ትግል ጀመሩ።ደኢህዴን ውስጥ የነበሩ የለውጥ ሀይሎች አፍነው ያቆዩትን የለውጥ አጋጣሚ በቸልታ ያዩ አይመስልም፡፡ በተለይም አቶ ሚልዮን ማቲዎስ እና ደሴ ዳልኬ አሁን የመጣው ሃገራዊ ለወጥ እውን እንዲሆን ህዝብ አንቅሮ የተፋውን የራሳቸውን ልጅ(ሽፈራውን በመካድ ለዶ/ር አብይ ድምጽ በማሸባሰብ ከፍተኛ ጀብድ ፈጽመዋል። (ይህን ለመረዳት የትኛውንም በጊዜው የነበረ የኦህዴድ አመራር መጠየቅ ይቻላል)፡፡ ይህን ለማድረግ ደኢህዴን እንደ ድርጅት ይዞት ከነበረው ጠንካራ አቋም ማፈንገጥ ነበረባቸው፡፡ በርግጥ ይህን ያደረጉት ለሀገራዊ ለውጥ ካላቸው ጽኑ ፍላጎት ብቻ ብለው ላይሆን ይችላል፡፡ በተለይ በሲዳማ ህዝብ ውስጥከግዜ ወደ ጊዜ  እየከረረ የመጣባቸውን ክልል የመሆን ጥያቄ እና ህዝባዊ ግፊት ለማስተናገድ ከፓርቲው ተልዕኮ ጋር ህጋዊ ፍቺ ማድረግ

ነበረባቸው፡፡ ለዚህ ተግባር ደግሞ ከዚሀ የተሻለ አጋጣሚ አልነበረም፡፡ ደኢህዴን ዴሞክራስያዊ ማዕከላዊነት ብሎ የሚዘምርለትን የወንብድና እና የታዛዥነት ማሽግ እነዚህ አመራሮች ባያፈርሱት ዛሬ የምናየው ሀግራዊ ለውጥ ባልመጣ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች የአንድነትን በማፍረስ እውነተኛ ሀገራዊ አንድነትን ለመገንባት ከቶርች መደረግ እና ወህኒ ጋር ተወራርደዋል።ስለዚህ አሁን ደቡብ ውስጥ እየተደረገ ያለው ፍቺ ዴሞክራሳዊ ፍቺ መሆኑን ከዚ መረዳት ይቻላል። አሁን የቀደሞው ሀይል መንሰራራት ከፈለገ ሊንሰራራ ከሚችልባቸው አማራጮች አንዱ ክልሉን እንደቀደመው በማጠናከር ተመጣጣኝ ደቡባዊ ሀይል መመስረት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ለዚህም ሰሞኑን ለማስኬድ እየተሞከረ ያለው ኖርማላይዜሽን እንቅስቃሴ የዚህ ጉዞ ማሳያ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ለእነ አብይ ትግል እንጨት ሲያቀብሉ የነበሩትን አመራሮች በዚሁ ሰበብ ማስወገድ ሌላኛው እርምጃ ሊሆን እንደሚችል ግልጽ ነው። ለዚሁ ተግባር በሶስት ቡድን የተደራጀ በከፍተኛ ገንዘብ የምክንቀሳቀስ ማፍያ ቡድን አደራጅተዋል የቡዱኑን ዝርዝር
ተግባር
በቀጣይ ይዘን እንቀርባለን

Via: Ejjeetto tube