የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው አስክሬን ላሊበላ ገባ

የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው አስክሬን ላሊበላ ገባ

(bbcamharic)–የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌን አስክሬን ላሊበላ አየር ማረፊያ እንደደረሰ በስፍራው የሚገኙት የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ማንደፍሮ ታደሰ ለቢቢሲ ገለፁ።

• ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ መገደላቸው ተገለጸ

• ስለ’መፈንቅለ መንግሥት’ ሙከራው እስካሁን የማናውቃቸው ነገሮች

ትናንት የብ/ጄነራል አሳምነው መገደል ከተሰማ በኋላ ቤተሰቦቻቸው አስክሬናቸው በክብር እንዲሰጣቸው ለወረዳው ጥያቄ በማቅረባቸው ጥያቄያቸውን መንግሥት ተቀብሎ አስክሬናቸውን እንደሸኘ አቶ ማንደፍሮ ተናግረዋል።

ዛሬ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት አካባቢ የብ/ጀኔራሉ አስክሬን ከባህር ዳር ወደ ትውልድ ቀያቸው እንደሚላክ በስልክ እንደተነገራቸው የገለፁት ምክትል ከንቲባው አስክሬናቸውን በክብር ለመቀበል በአየር ማረፊያ እንደተገኙ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የጄነራሉ ቤተሰቦች፣ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የአካባቢው የመንግሥት አመራር አካላት፣ የፀጥታ ኃይሎችና የቤተክርስቲያን ቀሳውስት በአውሮፕላን ማረፊያው ተገኝተዋል።

ከቤተሰቦቻቸው ጋር ገና ስላልተነጋገሩ የብ/ጄነራሉ የቀብር ሥነ ሥርዓት የትና መቼ እንደሚፈፀም በእርግጠኝነት መግለፅ እንደማይችሉ የገለፁልን ምክትል ከንቲባው፤ ሕብረተሰቡ ኃዘኑን የሚገልፅበት በከተማ አደባባይ ትልቅ ድንኳን የተዘጋጀ መሆኑንና አስክሬናቸውም በዚሁ ድንኳን ውስጥ እንደሚያርፍ አስረድተዋል።

በዚያው ሥፍራ ሌሊቱን የፀሎተ ፍትሃት ሥነ ሥርዓት እየተደረገ እንደሚያድር መረጃ እንዳላቸው ገልፀውልናል።

ምክትል ከንቲባው ብ/ጄነራል አሳምነው ለአገር ያበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው በደማቅ ሁኔታ ለመፈፀም ኮሚቴ መዋቀሩን አክለዋል።

በዚህም መሠረት የቀብር ሥነ ሥርዓቱን በዲስፕሊንና በፕሮቶኮል ለመምራት የክብር ተመላሽ ጄነራሎች በአካባቢው ላይ በመኖራቸው በእነርሱ ይመራል ብለዋል።

በሌላ በኩልም የፀጥታ ሂደቱን የሚመራ ቡድን፣ የወጣቱ ሰላምና ደህንነት የሚከታተል ሌላ በወጣቶች የሚመራ ቡድን እንዲሁም የሃይማኖት ሥነ ሥርዓቱን የሚመራ ኮሚቴም ተዋቅሯል።

• ራሱን አጥፍቷል የተባለው የጄነራል ሰዓረ ጠባቂ ሆስፒታል እንደሚገኝ ተገለፀ

አቶ ማንደፍሮ እንደገለፁልን ትናንት ብ/ጄነራሉ መገደላቸውን ከተሰማ አንስቶ በሕብረተሰቡ ዘንድ የተዘበራራቀ ስሜት እንደሚታይ እንዲሁም በክልሉ አመራሮች ሞት ምክንያት ድንጋጤ ውስጥ መሆናቸውን ነግረውናል።

የአገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግሥት አመራርና የፀጥታ አካላት ከህዝቡ ጎን በመሆን ቤተሰባቸውን በማፅናናትና ህዝቡንም በማረጋጋት ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሆነ አስረድተዋል።ESAT Special Eletawi Part 1 Tue 25 Jun 2019

ESAT Special Eletawi Part 2 Tue 25 Jun 2019


የሰሀረ አስክሬን ከህዝብ ጋር በምሽት ተቀላቀለ Ethiopia Abiy Ahmed


These  Stupid TPLF’s cadres are spitting venom day and night no job, they are just lumpen!!


Ethiopia: ሰበር ዜና – ዶ/ር አብይ አህመድ ዝምታቸውን ሰበሩ (የአሁን) – PM Abiy Ahmed’s Latest Statement

Ethiopia: ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና | Zehabesha Daily News June 25, 2019