“የብሄር ፖለቲካ በሕግ ቢታገድ እንኳን ሕጉን እንፈርሰዋለን”(ኢሳት አዲስ አበባ

“የብሄር ፖለቲካ በሕግ ቢታገድ እንኳን ሕጉን እንፈርሰዋለን”(ኢሳት አዲስ አበባ-ሚያዚያ 15 2011)
የብሄር ፖለቲካ በኢትዮጵያ እንዲቀር የሚደረገውን ጥረት ሕወሃት እንደማይቀበለውና እንደሚታገለው የሕወሃት ከፍተኛ አመራር አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ፣የብሄር ፖለቲካን ለማስቀረት የሚደረገውን ጥረት የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ይታገሉታል ሲሉም አሳስበዋል።

በብሄር ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ በሕግ ቢታገድ እንኳን ሕጉን እናፈርሰዋለን በማለት የዛቱት የሕወሃት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ለሚቀጥሉት 30 እና 40 ዓመታት የብሄር ፖለቲካ ይቀራል ብለው የሚያምኑ ካሉ ሞኞች ናቸው ሲሉም ተናግረዋል።

“ የብሄር ፖለቲካ በኢትዮጵያ ይቀጥላል አማራጭ የለውም” ሲሉም በሕወሃት ማህበራዊ ገጽ ላይ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።ኢሕአዴግ ወደ አንድ ሃገራዊ ፓርቲ ይዋሃዳል ማለት የብሄር ፖለቲካን ማስቀረት እንዳልሆነም ገልጸዋል። የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ ከኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ጋር የነበረው የዓላማ አንድነት እንደተበረዘ ገልጾ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ውህደት የማይታሰብ መሆኑንም እንዳመለከተ ይታወሳል።

ኢትዮጵያውያን አክቲቪስቶች በኢትዮጵያ ለቀጠለው ቀውስ መንስኤው የብሄር ፖለቲካ ነው በማለት እንዲታገድ ዘመቻ መጀመራቸው ይታወቃል። 


ለመሆኑ ገለልተኛ የታሪክ ፀሀፍት ምኒልክ የኦሮሞ እና ሌሎች ወንድም ህዝቦች ላይ ስለፈፀሙት በደል ምን ፅፈዋል የሚለውን በከፊል ስናይ፦

* በአፄ ምንሊክ መተዳደርያ ደንባቸው ላይ የሰፈረው የመጀመሪያው አንቀፅ ለኦሮሞ ህዝብ ያላቸውን ጥላቻና ንቀት በጉልህ ያሳየ ነበር፡፡አንቀፁ እንዲህ ይላል “የሰው ልጅ ክቡር ነው አይገደልም ፡፡ ጋላም ቢሆን” ይላል። የምንሊክ ዘረኝነት በዚህም ብቻ አላበቃም።

* ቡላቶቪች የተባለው ራሺያዊ በ1900 ከሚኒሊክ ጦር ጋር ዘምቶ የነበረ ሲሆን “Ethiopia Through Russian eyes” በተሰኘው መጽሀፉ የሚኒሊክ ወረራ የኦሮሞን ህዝብ ቁጥር በግማሽ ያሳነሰ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

* ማርቲን ዴ ሳልቫክ የተባለ ፈረንሳዊ የካቶሊክ ሚሺነሪ (1900) “The Oromo: An Ancient Africa Nation” በተባለው መጸሀፋቸው በዚህ ወረራ የኦሮሞ ህዝብ ቁጥር በግምት ከአስር ሚሊየን ወደ አምስት ሚሊየን መውረዱን ገምቷል፡፡

* August 18, 1895 እ.አ.አ የታተመው የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ፣ አፄ ሚኒሊክ በኦሮሞ ላይ ዘመቻ በመክፈት ወንዶቹን በመፍጀት ሕፃናት እና ሴቶችን በባሪያነት መውሰድ በሰፊው ይተገበሩ እንደነበር ፅፏል፡፡

* February 26, 1895 እ.አ.አ የታተመው የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ አሰቃቂው የሚኒሊክ ዘመቻ በሚል ርዕስ ስር ሰሞኑን ንጉስ ሚኒሊክ በኦሮሞ ህዝብ ላይ በደቡብ አቢሲኒያ የከፈቱት ዘመቻ 70,000 ሰዎችን በመግደል 15,000 መማረካቸውን ገልፀዋል፡፡

* August 2,1874 እ.አ.አ የታተመው የኒውወርክ ታይምስ ጋዜጣ የአቢሲንያ ባሪያዎች በሚል አርስት ስር በየዓመቱ ከ80,000 እስከ 90,000 የሚሆኑ ባሪያዎች በምፅዋ ወደብ በኩል ወደ ውጪ የሚሽጡ መሆኑን ጠቅሶ የባሪያ ነጋዴዎቹ ባሪያዎችን የሚገዙት ከነፍጠኞቹ ሲሆን ንጉሰ ነገስቱም የቀረጡ ተቋዳሽ መሆኑን ያትታል፡፡ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጽያዊያኖችን በባርነት ሸጠዋል (መኩሪያ ቡልቻ)::

* አኖሌ ላይ የሦስት ሺህ ኦሮሞዎች እጅ እና ጡት ከማስቆረጣቸው በተጨማሪ በአደዋ ጦርነት የተማረኩ 800 የኤርትራ አስካሪዎችን ቀኝ እጅ እና ቀኝ እግር አስቆርጠዋል፡፡

* November 7, 1909 እ.አ.አ የታተመው የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በአርስቱ የአቢሲኒያው ንጉስ ሚኒሊክ በአሜሪካው የባቡር ሃዲድ ስራ ተቋራጭ ከፍተኛ የአክሲዮን ባለቤት ናቸው በማለት ወደ ዝርዝሩ ውስጥ ስንገባ ይህ የባቡር ሃዲድ አክሲዮን ከሃያ አምስት ሚሊዮን ዶላር በላይ መሆኑ እና ከዚህ በተጨማሪ በቤልጅየም እና እስካንዲኒቭያ ከተሞች የወርቅ አምራች ኩባንያ ውስጥ አክሲዮን እንዳላቸው ዘርዝረዋል፡፡

* ይህ ሁሉ ንብረት ከዬት መጣ ብለን ብንጠይቅ ከተወረሩ ብሄር ብሄረሰቦች የተዘረፈ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት የሚኒሊክ ወታደሮች ከአርሲ 66,000 የቀንድ ከብት (ፕሮፌሰር መኩሪያ ቡልቻ)፤ ከወላይታ 18,000 (ተሻለ) ከደቡብ ኦሞ 40,000 ከጂጂጋ 50,000 (ጆን ማርካኪስ) ወዘተ… የተዘረፈ ነው፡፡

በዚህ አጋጣሚ ዛሬም እንደ ድሮው በምኒልክ ጨፍጫፊነት ምክንያት የዚህ ዘመን የአማራ ህዝብ የሚያወራርደው ምንም አይነት የታሪክ ዕዳ የለም ብለን እናምናለን፡፡ ነገር ግን ይህን ሰው በላ ግለሰብ ከማሞካሸት በመቆጠብ እና ሀውልቶቹን በማፍረስ ለወንድም ህዝቦች ያለውን አጋርነት እንዲያሳይ እንጠብቃለን፡፡

Haweni Dhabessa

እዚሁ ፌስቡክ ጓደኞቼ መሀል አብሮኝ ፊንፊኔ ዩኒቨርሲቲ Economics የተማረ ለPrivacy ስል ስሙን የማልጠቅሰው አንድ የአርሲ ልጅ ጓደኛ አለኝ፡፡ ይህ ጓደኛዬ ሴት አያቱ በ110 አመትዋ ካቻምና 2009 ላይ ነው ያረፈችው፡፡ የእኝህን አዛውንት የእናታቸውን ጡት የምኒልክ ወታደሮች ቆርጠውታል፡፡ የአባታቸውን ደግሞ እጅና እግር በመቁረጥ ለአካለ ስንኩልነት ዳርገዋቸዋል፡፡ በዘመኑ የሞተውን ደግሞ ቤቱ ይቁጠረው፡፡
———
አርሲ እና አካባቢው ላይ በምኒልክ እና በወታደሮቹ የግፍ በትር ያልተንኳኳ ቤት የለም፡፡ ሁሉም ከትውልድ የተረከበውን ይህን እውነታ ይናገራል፡፡ እርግጥ ነው አፋን ኦሮሞ መፃፊያ ፊደላት ስላልነበረው በፅሁፍ የተወረሰ ነገር ባይኖረውም፣ ኦሮሞ ለልጆቹ የተፈፀመውን እውነታጠአንዳች ሳይቀር ነው የሚዘግበው፡፡ በታሪክ ጥናት ውስጥ Primary እና Secondary Source ተብለው ይቀመጡ እንጂ በፅሁፍ ያለም ሆነ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፈ ኩነቶች በታሪክ ጥናት ውስጥ እንደምንጭነት ያገለግላሉ፡፡ በመሆኑም የተፃፈ ነገር ስለሌለ ይህ ታሪክ ተቀባይነት የለውም የሚለው የምኒልካውያን ሙግት በታሪክ ጥናት ላይ ተቀባይነት የለውም፡፡
———-
ኦሮሞ ምኒልክ ስለፈፀመው ግፍ የዚህ ዘመን አማራ የሚያወራርደው የታሪክ ዕዳ አለ ብሎ አያምንም፡፡ ተጠያቂም አያደርገውም፡፡ ነገር ግን ጀርመናዊያን ሂትለር እና የናዚ ጦር በአይሁዳውያን እና ጂፕሲዎች ላይ የፈፀመውን ጭፍጨፋ አምነው፣ እንዲህ አይነት ድርጊት ዳግም እንዳይፈፀም ማንኛውም የሂትለር ብሎም የናዚ ምልክቶች በህዝብ ፊት እንዳይቆሙ እና በኩራት ማወደስን ወንጀል እንዳደረጉ ሁሉ አማራ ወንድሞቻችንም በምኒልክ እና በስርዓቱ ላይ ተመሳሳይ አቋም እንዲያራምዱ እና ለዘላቂ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ሲባል ሀውልቱን ጨምሮ ማንኛውም ምልክቶቹን ከመሀላችን እንዲያስወግዱ እንፈልጋለን፡፡


ESAT Eletawi Wed 24 Apr 2019

1 Comment

  1. Jewish people do have built a museum that tells the story of Hitlers’s inhuman acts to remind the world that such brutal genocide want repeat itself. Yes we do not see Hitler’s statue so we do not want to see Minelik’s or Haile Sealses statues but like Jewish memorial museum Anole should be kept us a memorial to those thousands men and women who died at Anole. Let get rid of all the statues of Minelke and those like him and erect the statues of Qeerro and Qaree as well as General Tadesse Biru and other Oromo and Ethiopian heroes.

Comments are closed.