የቄሮን ጥሪ አስመልክቶ ከኤጄቶ የተሰጠ የአጋርነት መልዕክት

የቄሮን ጥሪ አስመልክቶ ከኤጄቶ የተሰጠ የአጋርነት መልዕክት

“Qeerroon Oromoo abbaa galata keenyaati. Kaleessa gaafa rakkoo nu waliin dhaabatan. Har´a gaafa rakkoo waliin dhaabachuuf dirqama qabna” jedha Ejjettoon SIDAAMAA.

የብሄር ብሄረሰቦችን መብት ረገጣ በማውገዝ ላለፉት ዓመታት

ሲደረግ የነበረውን የቄሮ ትግል እንደ ተሞክሮ በመውሰድ ከዚህ ቀደም የሲዳማ ጀግኖች ባልተደራጀ መልኩ ሲጠይቁ እና ሲታገሉለት የነበረው የሲዳማ ክልል ጥያቄ እውን እንዲሆን ከ2010 ዓም ጀምሮ የሲዳማ ወጣቶች ኤጄቶ በሚል ስያሜ መራራ ትግል በማድረግ እና ብዙ መስዋትነትን በመክፈል ትግላችን ፍሬ እንዲያፈራ አድርጓል።ለዚህ ድል እንድንበቃ የኦሮሞ ቄሮ ድጋፍ ከጅምሩ እስከ ስኬቱ ድረስ ያልተለየን ከመሆኑም በላይ ያለ ኦሮሞ ፖለቲከኞች ድጋፍ ባጭር ጊዜ ውስጥ ለድል ባልበቃን ነበር።ለዚህ ታሪካዊ አጋርነታችሁም የሲዳማ ህዝብ ሁሌም ያመሰግናችኋል።

ከ1956 ጀምሮ በሲዳማ አርነት ንቅናቄ(ሲዓን) እና በኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር ከፍተኛ አመራሮች የተጀመረው የሁለቱ ብሄሮች የትግል አጋርነት ዛሬም ድረስ ያለ እና ወደ ፊትም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን እናረጋግጣለን።በተለይ በሀገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች መብት ላይ እና በፌደራሊዝሙ ላይ የሚቃጡ ትንኮሳዎችን ለመመከት የሲዳማ ኤጄቶ ሁሌም ዝግጁ መሆኑን እየገለጽን አሁን ላይ በኦሮሞ ወንድሞቻችን ላይ እንደ ህዝብ እየደረሰ ያለውን አምባገነናዊ የመንግስት እርምጃ አምርረን እናወግዛለን።የኦሮሞ ህዝብ መብቱን ለማስከበር በሚወስደው የትኛውም ሰላማዊ ትግል የሲዳማ ኤጄቶ ከጎኑ መሆኑን እና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን እንገልጻለን።

ድል ለጭቁን ህዝቦች!!

ሀዋሳ ሲዳማ ኢትዮጵያ
ኤጄቶ

Via: Ejjeetto tube


Shirri keessaa fi alaa hangamuu hammaatu, kaayyoon qabsoo Oromoo xaliilawaan abadan hin boorawu! Oromoon galma isaa irraa hin hanqatu!