የሶማሌ ልዩ ኃይል ከኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች ጋር የነበረውን ግጭት

የሶማሌ ልዩ ኃይል ከኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች ጋር የነበረውን ግጭት አባብሷል መባሉን የክልሉ ፕሬዚዳንት አስተባበሉ

የሶማሌ ልዩ ኃይል ከኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች ጋር የነበረውን ግጭት አባብሷል መባሉን የክልሉ ፕሬዚዳንት አስተባበሉ

የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች ነዋሪዎች መካከል የነበረውን ግጭት ለማረጋጋት የሁለቱም ክልሎች የፀጥታ ኃይሎች ሚና ከፍተኛ ነበር አሉ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ዛሬ እሁድ ታህሳስ 15 ቀን 2010 ዓ.ም. በጅግጅጋ ከተማ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በተለይ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ችግሩን ከመፍታት አኳያ ያደረገው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር ብለዋል፡፡ የፀጥታ ኃይሎች የተከሰተውን ችግር አባብሰዋል ማለት አግባብ አይደለም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ የክልሉ ልዩ ኃይል ለኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ገልጸዋል፡፡

የሶማሌ ክልል በተለይ የአልሸባብ፣ የኦብነግና የኦነግ መተላለፊያ ሆኖ እንደነበር ያስታወሱት ፕሬዚዳንቱ፣ በልዩ ኃይሉ መስዋዕትነት ክልሉ ከእነዚህ ኃይሎች ነፃ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ምክንያት የተሰዉ የልዩ ኃይል አባላት ልጆች የሆኑ ስድስት ሺሕ ወላጅ አልባ ልጆችን የክልሉ መንግሥት እያሳደገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶሕዴፓ) እና በኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) መካከል ልዩነቶች እንደሌሉ ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን በተለያዩ ጊዜያት ሲታዩ የነበሩ መወቃቀሶች በድርጅቶቹ መካከል ክፍተት መኖሩን አያሳይም ብለዋል፡፡

ሆኖም ሲታዩ የነበሩ መወነጃጀሎችን በውይይት ለመፍታት በድርጅቶቹ መካከል እየተሠራ እንደሆነምም አቶ አብዲ ተናግረዋል፡

Source: ethiopianreporter


Basaastota wayyaaanee Jijjigaatti Abdi Illen afeeramanii dokumantarii sobaa Oromoon Somaalee Ajjeese Jedhanii gabaasa kijibaa warreeen hojjechuuf deemaniidha.

This are the TPLF cadres!!

Miidhaksaa Abbishuu