የስልጣን ርክክብ አለመፈፀም እና የምሁራን ኤጄቶች እስራት በሲዳማ ህዝብ ዘንድ ቁጣ እየቀሰቀሰ የሚገኝ ጉዳይ ነዉ” አቶ ዱካለ ላሚሶ

የስልጣን ርክክብ አለመፈፀም እና የምሁራን ኤጄቶች እስራት በሲዳማ ህዝብ ዘንድ ቁጣ እየቀሰቀሰ የሚገኝ ጉዳይ ነዉ” አቶ ዱካለ ላሚሶ

ሀዋሳ 14/06/2012ዓ.ም (SMN) ሀዋሳ፣ሲዳማ

የስልጣን ርክክብ አለመፈፀም እና የምሁራን ኤጄቶች እስራት በሲዳማ ህዝብ ዘንድ ቁጣ እየቀሰቀሰ እንደሚገኝ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ሊ/መንበር አቶ ዱካለ ላሚሶ ተናገሩ።

አቶ ዱካለ ይህንን የተናገሩት ሲአን ዛሬ እያካሄደ ባለው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ነው።

እነዚህ ጉዳዮች በአፋጣኝ እልባት እንድያገኙ ለጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት ደብዳቤ ከመፃፍ ጀምሮ በርካታ ስራዎች መስራታቸውን በሪፖርታቸው ገልጸዋል ።

አቶ ዱካሌ ላሚሶ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት ደርግ ከፈጸመው በደል ያልተናነሰ የማይረሳ ጠባሳ በሲዳማ ህዝብ ላይ በዚህ በገዥው መንግስትም የተለያዩ በደሎች ተፈፅሟል ብለዋል።

ግንቦት 16/1994 ዓ.ም የተፈፀመው የሎቄ ጭፍጨፋ ለዚህ ማሳያ መሆኑን አንስተው
ዛሬም በፖሊቲካ አሻጥር ንጹሃን የሲዳማ ተወላጆች ያለጥፋታቸው በተለያዩ እስር ቤቶች እየተሰቃዩ ይገኛሉ ብሏል።

አክለውም አቶ ዱካሌ የስልጣን ርክክብ አለመፈፀም እና የምሁራን ኤጄቶች እስራት በሲዳማ ህዝብ ዘንድ ቁጣ እየቀሰቀሰ የሚገኘዉና በግዜ እልባት የሚያስፈልገው ጉዳይ እንደሆነም ጠቅሶዋል።

በሰብሰባዉ ላይ ፕ/ር መራራ ጉዲናን ጨምሮ የተለያዩ የመድረክ አጋር ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።

Sidama Media Network-SMN