የሲዳማ ታጋዮችን ለማሰር የወጣው ትዕዛዝ በተወሰኑ አመራሮች አለመግባባት ተቀልብሷል!!

#የሲዳማ_ታጋዮችን_ለማሰር_የወጣው_ትዕዛዝ_በተወሰኑ_አመራሮች_አለመግባባት_ተቀልብሷ!!

በአዳማው የብልጽግና ፓርቲ ስብሰባ ላይ የተገኙ የሲዳማ አመራሮች፡- የሲዳማ አክቲቪስቶችን እና አንዳንድ የኤጄቲማ ፌደራሊስት ፓርቲ ግዜያዊ አስተባባሪዎችን ለማሰር የወጣው የእስር ትዕዛዝ በአመራሮቹ እርስ በእርስ አለመግባባት ምክንያት ቀርቷል።

ላለፉት 7 ወራት በግፍ የታሰሩ የሲዳማ ሙህራኖች ከእስር አለመለቀቃቸውን ተከትሎ የህዝቡ ቁጣ ወደ ረብሻ ያመራል በሚል ስጋት 60 የሚጠጉ ኤጄቶችንና የኤፈፓ ፓርቲ አመራሮችን ለማሰር የወጣው ዕቅድ ሌላ ከባድ ብጥብጥ ይፈጠራል በሚል ስጋት የቀረ ቢሆንም ጠርተናቸው የቃል ማስጠንቀቂያ እንስጣቸው በሚል አማራጭ ሃሳብ የሲዳማ አስተዳደር ጸጥታ ሀላፊው አቶ አለማየሁ ጥሞቲዎስ እና የሀዋሳ ከተማ ጸጥታ ቢሮ ሀላፊው ኮሎኔል ሮዳሞ ጠርተዋቸው እያስፈሯሯቸው እንደዋሉ መረጃ ደርሶናል።

ኮሎኔል ሮዳሞ ዛሬ ከሰዓት 10 ሰዓት የኤፌፓ አስተባባሪዎችን ከቀጠሩ በኃላ ከቢሮ እንደተሰወሩና ከተወካይ ጋር እንዲወያዩ የተነገራቸው ኤፌፓዎች ከተወካይ ጋር አንነጋገርም ብለው ጥለው መውጣታቸውን አረጋግጠናል። አቶ አለማየሁ በበኩሉ ህዝቡን ለማስፈራራት መከላከያ ወደ ከተማ ያስገባ ሲሆን ልጆችን ስልክ እየደወለ ድርጊታችሁ ሁሉንም በቪዲዮና በድምጽ ቀድተናል፣ ደህንነት ሁሉንም መረጃ ሰቶኛል፣ ቢሮዬ ውስጥ የቴሌ መገናኛ ሰርቨር አለ ሲል ታጋዮችን ለማሸበር ሲሞክር መዋሉን አረጋግጠናል።

ታጋይ ሙህራኖች ከእስር አለመለቀቃቸውን ተከትሎ ልጆቹ መፈታት አለባቸው በሚሉ እና ልጆቹ መፈታት የለባቸውም እንደውም ህዝቡ እንዲጠላቸው የስም ማጥፋት ዘመቻ እንጀምር በሚሉ የሲዳማ አመራሮች መካከል አለመግባባት መፈጠሩ ተረጋግጧል። በተለይ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር እና የሲዳማ አስተዳደሪዎች ልጆቹ መፈታት የለባቸውም በህልውናችን ላይ ነው የመጡት ሲሉ ቢከራከሩም በሌላ በኩል ደግሞ ልጆቹ ካልተፈቱ ስልጣናችንን እንለቃለን እስከማለት የደረሱ አመራሮች መኖራቸውን ታማኝ ምንጫችን ከአዳማ መረጃውን አቀብሎናል።

“የሲዳማ ታጋዮችን በማስፈራራት የህዝቡን ጥያቄ ማፈን አይቻልም!!”

#በማሳንቱ