የሲዳማ ብሄር ክልል መሆን በሌሎች አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የማይደገፍበት ምክንያት:-

የሲዳማ_ብሄር_ክልል_መሆን_በሌሎች_አማርኛ_ቋንቋ_ተናጋሪዎች_የማይደገፍበት_ምክንያት:-

#1 ቋንቋ

የሲዳማ ብሄር ክልል ሆኖ ሲዋቀር የክልሉ የስራ ቋንቋ Sidaamu-Afoo እንደሚሆን ግልጽ ነው። ላለፉት 27 ዓመታት ሲዳማ በደቡብ ክልል ስር በነበረበት ውቅት የዞኑ የስራ ቋንቋ ሲዳምኛ ቢሆንም በአጠቃላይ የክልሉ ቋንቋ ግን አማርኛ ነበር።በዚህም ምክንያት ነበር ከፍተኛ የስራ አጥ ፍልሰት ከሌላ ክልሎች (አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች) ወደ ደቡብ ክልል ሲተም የነበረው።ከሀዋሳ ከተማ ህዝብ 30% የሚሆነው በዚህ የስራ ፍለጋ ምክንያት የመጣ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።አሁን ሲዳማ ክልል ሆኖ ሲወጣ ግን በሀዋሳ ከተማ እና በሌሎቹ የሲዳማ ክልል ውስጥ የሚገኙ የስራ እድሎች ወደ ሲዳምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሚያደላ በመሆኑ ወደ ሲዳማ የመጡ እና ሊመጡ ያሰቡ ወይም ወገኖቻቸው በሲዳማ ያሉ ሁሉ ከእራሳቸው ጥቅም አንጻር አይተውት የሲዳማን የክልል ጥያቄ አምርረው እንዲቃወሙ ዋነኛ ምክንያት ሆናቸው፡፡

#2 ዘረኝነት

ታዋቂው የoxford መዝገበቃላት ዘረኝነት የሚለውን ቃል ሲተረጉመው “እራስን ከሌላው የበላይ አድርጎ ማሰብ እና ሌላውን የበታች አድርጎ ማሰብ ሲሆን የእራስን ማንነት በሌላው ላይ ለመጫን መሞከርም ነው” ይላል። እንግዲ ሲዳማ ክልል ሆኖ ሲዋቀር ማንነቱን፥ባህሉ፥ቋንቋውን፥ሀብቱን፥ታሪኩን እና አቅሙን አጎልብቶ እራሱን በእራሱ ያስተዳድራል። ሲዳማ ይህን በማድረጉ ከሌሎች(ቀደምት ክልሎች) እኩል ይሆናል እንጂ የበላይ አይሆንም።ግን ዘረኝነት የተጠናወተውን እኩል እንሁን ስትለው የበታች የሆነ ስለሚመስለው ይቃወምሀል።በእኩልነት የምታምን ከሆንክ እና ዲሞክራስያዊ መብቶችን የማክበር አቅም ካልህ የማንንም ነጻነት አትቃወምም፡፡ ስለዚህ የሲዳማን ብሄር ክልል መሆን የሚቃወሙበት ሌላኛው ምክንያት ሲዳማ እራሱን በእራሱ ማስተዳደር ሲጀምር ማንነቱን በግልጽ ስለሚያሳይ የተጫነበትን ማንነት አውልቆ ይጥለዋል የሚል ስጋት ነው።

“የሲዳማን ክልል መሆን አለመደገፍ መብት ይሆናል መቃወም ግን ዘረኝነት ነው!!”

#በማሳንቱ

Sidama page