የሲዳማ ህዝብ ሰላማዊ ትግሉን ማን ቀለበሰው¿¿

Above Single Post

የሲዳማ ህዝብ ሰላማዊ ትግሉን ማን ቀለበሰው¿¿

አመቱን ሙሉ በተደጋጋሚ ጊዜ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ በአደባባይ ወጥተው ድምፃችን ይሰማ ሲሉ ጆሮ ዳባ ብሎ

ኃላፊነት እንዳለው እንደ ሃገር መሪ ሀሣቡን እንኳን ሳይሰጥ የቆየው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሲዳማ ክልል ጉዳይ በተመለከተ የመጀመርያ ንግግሩ በህዝብ ተወካዮች ፊት ቀርበው ሱማሊያን እንዳደረጉት አደርጋችኋለሁ የሚለው ነበር::¿¿
Sidama page


ሲዳማ ትግሉን ያሳካል፤ አትጠራጠሩ…

የሲዳማ ህዝብ ጠላቶች፤ ለጊዜውም ቢሆን የትግሉን አካሄድ በመጥለፍ የሁከትና የችግር መልክ ለማላበስ በመሞከር አላግባብ ሰውን ብትጨፈጭፉም፣ ንጹሃንን ብትቀጥፉም፣ ህዝባችን በለመደው ጽናት ተመካክሮ ወደሠላማዊ ትግል መሥመሩ ተመልሶ ትግሉን ያሳካል፤ አትጠራጠሩ።

በደኢህዴንና በኢዜማ ድርሰት፣ በጠቅላይ ሚንስትሩ አጽዳቅነት፣ በፓርላማ ቡራኬ እና ባንዳንድ ወገኖች ታዛቢነት የተቀነባበረው የሲዳማ ህዝብን የመጨፍጨፍ ድርጊት ከመቶ በላይ ንጹሃንን ገድለዋል። ከ400 በላይ መታሠራቸውን ከሥፍራው የሚገኙ ምኝጮች ይገልጻሉ።

በተለያየ ድራማዊ በሚመስል በተንኮል ሥራ አጋጣሚውን ተጠቅመው የሲዳማን ህዝብ ማጥፋት፣ የትግል ራዕዩን ለማጨናገፍና ለለውጡ የተሠለፉ ሙሉ እውቀትና ችሎታ ያላቸውን፣ የኢትዮጵያም የ አፈና ፖለቲካ ቻሌንጅ የሚያደርግ የሲዳማ ትውልድን በማጥፋት ሲዳማ ፀጥ ረጭ አድርገው ለመግዛት በማሰብ የወሰዱት የተቀናጀ የጭፍጨፋ እርምጃ ነው።

እውነት ነው፣ ሲዳማ የፌደራሊስት ኃይል ፍላጎቶችን አጉልቶ በማውጣትና የትግሉ መርሆ በማድረግ፣ የአሃዳዊነት ሥርዓትንና ናፋቂዎቻቸውን በአደባባይ በመኮነንና በማውገዝ፣ የጭቁን ህዝቦች ድምጽ ይሠማ ብሎ አደባባይ በመውጣት ጠላት አትርፏል። ሲዳማ የፌዴራል ሥርዓት አራማጅነቱ ብቻ ሳይሆን ህዝቦች ያለፈቃዳቸው የታጎሩበትን፣ የሚመስላቸውን የአስተዳደር መዋቅር እንዳይፈጥሩ የተጫነባቸው ቀንበር እንዲነሳ ብቻውን ታግሏል።

ሲታገልም ደቡብ ክልልን እንደዋነኛ ምሽጋቸው አድርገው የሚቆጥሩ ከክልሉ ውጭ የራሳቸው ክልል ያላቸው አሃዳውያን የሲዳማ ትግል ይሄንን ምሽጋቸውን እንድሚያፈራርስባቸው ስለተረዱ በሲዳማ ህዝብ መብት ሠላማዊ ትግል ሂደት በተጻራሪነት በምቆም ሲያውኩ ቆይተዋል።

በመጨረሻም፣ በአሃዳውያን አስተሳሰብ የሚመራና ጽፈው የሰጡትን ድርሰት የሚተውንላቸውን መሪ ሲያገኙ እጃቸውን ጠምዝዘው በሚወዳቸውና ባከበራቸው ሲዳማ ህዝብ ላይ አፈሙዝ እንዲያዞሩ መክረውና ዘክረው ትፎዞ አሰባስበው ንጹሃንን አስጨፍጭፈዋል። ይህም ሲዳማ የሚንልክ ግዛት አካል ሆና ከተጠቃለለች ጊዜ አንስቶ ሲደገስለት የኖረ ሞትና መቁሰል ነው።

አምና እና ካቻ አምና የኦሮሞ ወጣቶችን መንግሥት ሲረሽን ነበር። በርካቶች ተሰውተዋል። ዘንድሮ ንጹሃን መብታቸውን የጠየቁ የሲዳማ ተወላጆችን በጠራራ ፀሃይና በሌሊት እየገደለ፣ በጅምላ እየረሸነ ነው። ለማስቆም ወይም ለመተቸት የሞከረ መንግሥታዊም ሆነ ሰብዓዊ ድርጅት የለም።

የሲዳማ የመብት ጥያቄ ላይ የተሠነዘረው የጭፍጨፋ ምላሽና እርምጃ ለሌችም ነገ ላይ እንደማይደገስላቸው ምንም ዋስትና የለም። የጊዜ ጉዳይ ይሁን እንጂ የሁሉንም በርና ቤት ያንኳኳል። ለውድቀት የተጋለጠ #Empire የሚበላውን በልቶ የሚያጠፋውን አጥፍቶ፣ በሌላ በኩል አገሩ የእኛ ነው የሚሉትን የተንከባከበ ቢመስላቸውም መጨረሻው ውድቀት ነው።

ፈጽሞ የማይገባውን ዋጋ ህዝባችን ከፍሏል። ያልተገባ ሞትን ደግሰውና አቀናብረው በጉዱማሌ ሊሰበሰብ የሚሄድን፣ ከሽማግሌ ጋር ለመምከር የሚሰበሰብን ህዝብ በጥይት በትነው ስሜት ውስጥ አስገብተው፣ ከተማን ገጠሩን ከበው፣ መግቢያና መውጫ አሳጥተው ህዝባችንን ጎድተዋል። የፀጥታ ማስከበር ሥራ ሳይሆን ጠቅላላ የጦር አውድማ አስመስለዋል፤ ይህም የፀጥታ ጉዳይ ሳይሆን ሌላ የተሸፈነ ፍላጎት መኖሩን ያሳያል።

ነገር ግን፣ ላለፉት በርካታ ዘመናት ሲዳማ መብቱን በጠየቀ ቁጥር ተመሳሳይ ግድያና እልቂት አስተናግዷል። ግን ያ ሁሉ በደል ከትግሉ አላስቆመውም። አንዳች ቀን ከትግሉ ፈቀቅ ያላለ ህዝብ ነው። የፍትህ ጥያቄው ለገዥዎችና አንባገነኖች የራስ ምታት እንደሆነባቸው ዘልቋል። ያኔ ጨፍጭፈው ጋብ ለማድረግ ሞክረው ሊሆን ይችል ይሆናል። አሁን ግን ወቅቱ ሌላ ነው።

መብቱን አጥቶ፣ ደሙን አፍስሶ፣ ውድ ህይወቱን በየዘመኑ ገብሮ እጁን አጣጥፎ ወደቤት የሚመለስ ሲዳማ እንደማይኖር ማወቅ ይገባል። ሲዳማ የጠየቀው ቀላል የመብት ጥያቄ ነው። ይህንን የሚያረጋግጥለት የራሱ ትግል ነው። ያንን በማድረግ ላይ ነው። ለጊዜውም ቢሆን የትግሉን አካሄድ በመጥለፍ የሁከትና የችግር መልክ ለማላበስ በመሞከር አላግባብ ሰውን ብትጨፈጭፉም፣ ንጹሃንን ብትቀጥፉም፣ ህዝባችን በለመደው ጽናት ተመካክሮ ወደሠላማዊ ትግል መሥመሩ ተመልሶ ትግሉን ያሳካል፤ አትጠራጠሩ። KKL

ሞት ለገዳዮችና ጨፍጫፊዎች።
#Free_Ejjeetto 

Below Single Post