የሱዳን ሰራዊት የኢትዮጵያን መሬት ተቆጣጥሯል ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ምሽግ ቆፍሮ ሰፍሯል

የሱዳን ሰራዊት የኢትዮጵያን መሬት ተቆጣጥሯል ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ምሽግ ቆፍሮ ሰፍሯል:

የሱዳን ሰራዊት መጋቢት 20 ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በመግባት በምዕራብ ጎንደር ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ እና ኮር ሁመር ከተማ አካባቢ የሚገኙ ባለሃብቶች ንብረት ላይ ጥቃት መሰንዘሩን የ TFI ምንጮች ነግረውናል። ይሄ ሰራዊት በድጋሚ መጋቢት 29 ወደ አካባቢው በመሰማራት ምሽግ ቆፍሮ በመስፈሩና ድንበር አካባቢ ነዋሪ የሆኑ የሁለቱም ሀገራት ዜጎች ግጭት ይነሳል ብለው በመሸሻቸው የኢትዮጵያና የሱዳን ኢታማዦር ሹሞች በሳምንቱ መጨረሻ ለድርድር ተቀምጠው ነበር። ከሱዳን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ጋር ውይይት ለማድረግ ወደ ካርቱም ያቀኑት ጀነራል አደም መሀመድ መሬቱ የሱዳን በመሆኑ ኢትዮጵያ የይገባኛል ጥያቄ ማቅረቧ ተገቢ አይደለም መባላቸውን ሰምተናል። የሱዳን መንግስት ወኪሎች የድንበር ውዝግቡ በ 1902 እንግሊዝ ባከናወነችው demarcation መሰረት እንዲከናወን ሃሳብ አቅርበዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ስለ ውዝግቡ ብሪፍ መደረጋቸውንም ሰምተናል። ዲፕሎማቲክ ምንጮች እንደሚሉት ሱዳን በህዳሴው ግድብ ድርድር ላይ ያላትን ተሳትፎ እንደ leverage በመጠቀም ለኢትዮጵያ ከመወገኗ በፊት ድንበር አካባቢ ያለ ሰፊ ለም መሬት ወደ ሱዳን እንዲካለል የማድረግ ፍላጎት አላት። ጉዳዩን አለሳልሳ የያዘችው ኢትዮጵያም የሱዳን ሰራዊት ወደ ድንበሩ እንዲመለስ ለማግባባት ከመሞከር ባለፈ ጠንከር ያለ ጥያቄ አላቀረበችም። ምክንያቱም በግድቡ ጉዳይ ሱዳንም እንደሌሎቹ የአረብ ሊግ አባላት ከግብፅ ጎን እንዳትሰለፍ በመፍራት መሆኑን ውዝግቡን በቅርበት ከሚከታተሉ ምንጮች ሰምተናል። አርብ በተደረገው ውይይት በድንበር አካባቢ የሚያስቸገረው ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርና ወንጀልን መከላከል ላይ ስምምነት ላይ ቢደርሱም በሱዳን የተያዘውን መሬት በተመለከተ እሰጣገባው እስካሁን አልተፈታም። የሱዳን ሰራዊት አሁንም ወደ ራሱ ድንበር አልተመለሰም።

THE FINFINNE INTERCEPT


Currently, lunatic Abiy has created problems with all countries around Ethiopia with exception of Somalia. Djibouti, Kenya, Eritrea, Sudan and South Sudan have expressed their displeasure over the last six month.

Sudan has invaded and occupied Kimant land in Amhara region.
Kenya has accused lunatic Abiy for supporting Farmajo to attack regional leaders such as in Jubaland.
Ethiopia is no longer part of South Sudan peace process.
Djibouti has never been happy since lunatic Abiy ‘came to power’.
There is no longer ‘smile and laugh’ with Eritrea. The border is still shut, no progress.

We are in mess and Abiy is responsible.

Biyya Oromiyaa