የሱማሌ ክልል ልዩ ሃይል በግዛት ማስፋፋት እና የድንበር ይገባኛል ስም በኦሮሞ ህዝብ

የሱማሌ ክልል ልዩ ሃይል በግዛት ማስፋፋት እና የድንበር ይገባኛል ስም በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚፈጽመውን ግድያ የሚያወግዝ ህዝባዊ


(ኢሳት ዜና – September 12, 2017)
— የሱማሌ ክልል ልዩ ሃይል በግዛት ማስፋፋት እና የድንበር ይገባኛል ስም በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚፈጽመውን ግድያ የሚያወግዝ ህዝባዊ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው። ህወሃት ከሱማሌ ክልል ልዩ ሃይል ጀርባ ነው ተብሎ ይታመናል። ተቃውሞውን ተከትሎ በአወዳይ 5 ሰዎች ሲገደሉ 6 ወታደራዊ መኪኖችም ተቃጥለዋል። (በተጨማሪ 6 አውቶብሶችም መሰባባራቸው ታውቋል)
— የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ሞሃመድ በክልሉ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ በማዘዛቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች ሐረር ከተማ እየገቡ ሲሆን ተጨማሪ ተፈናቃዮችም መንገድ ላይ መሆናቸው ታውቋል።
— ይህ በዚህ እንዳለ… የኦህዴድ ባለስልጣንና የጉርሱም ወረዳ አስተዳዳሪ ተገድሏል። ነዋሪዎች ግድያውን የሱማሌ ልዩ ሃይል አባላት እንደፈጸሙት ይናገራሉ። ሌሎች ደግሞ ሆን ተብሎ ግጭቱ እንዲባባስ በማለም የተካሄደ ግድያ ነው ይላሉ።
— ሌሎችም ዜናዎች…


ESAT Daily News DC 12 Sep 2017