የሰው ልጅ ከፈጣሪ በታች ትልቁ የመጽናኛው ሃይል ተስፋ ነው ፣ ተስፋ የዕድሜ ማራዘሚያ የመኖሪያ ምስጢር ናት

የሰው ልጅ ከፈጣሪ በታች ትልቁ የመጽናኛው ሃይል ተስፋ ነው ፣ ተስፋ የዕድሜ ማራዘሚያ የመኖሪያ ምስጢር ናት

ከድህነት ይሁን ከህመሙ ከባርነት ይሁን ከረሃብ አንድ ቀን በዚህ መንገድ እገላገላለሁ የሚል ተስፋ ሰንቆ ፣ ይጽናናበታል፣ ኦሮሞ ከፖለቲካ ባርነት ነፃ ያወጣኛል ፣ከመልካም አስተዳደር ችገር ይገላግለኛልየአገር ባለቤትነት መብቴን ያጎናፅፈኛል ብሎ ለረጅም ጊዜ ተስፋ አድርጎ የኖረው ABOን ነው ፣ ABO ሕዝቡ በሚፈለገው መጠን ይህንን ሃላፊነት ተወጥቷል ወይ የሚለው ጥያቄ
እንዳለ ሆኖ ፣ቢያንስ የዛሬ 50 ዓመት የጀመሩት ትግል ፣ሕዝቡ ውስጥ የዘራው የእንብተኝነት መንፈስ የኦሮሞነት መንፈስ ፍሬ አፍርቶ ኦሮሞ የአገሪቷ ግንድ መሆኑን የማይቀበሉትን የቀኝ ዘመም ፖለቲካ አምላኪዎችን አንገት አስደፍቶ ኢትዮጵያ ያለ ኦሮሞ ፣ልትኖር እንደማትችል ፣በአንደበታቸው እንዲያረጋግጡ ፣አስገድዷቸዋል ፣ ወደ ዋና መነሻዬ ልመለስና ODP ያልተረዳው ነገር ፣ አለ ተስፋ የውስጥ መንፈስ ነው ABO ይኑር አይኑር ፈታን ካላችሁት 40,000 ሺህ ኦሮሞ እስረኛ ውስጥ የABO አባል ሆኖ የታሰረው ፣10% ቢሆን ነው ፣የተቀረው ኦሮሞ ቀርቶ OPDO ሲፍቅ ABO ነው በሚል መንፈስ ነው ፣ ይህ ማለት ደግሞ የኦሮሞ የትግል ባለቤትነት ፓተንት የተሰጠው ለዚህ ድርጅት ነው ፣ ስለዚህ በሰው ልጅ ውስጥ አንደ የተፈጠረ ተስፋ ልክ በኢርሳስ ደብተር ላይ ጽፎ በላጲስ የማጥፋትን ያህል ከሰው አዕምሮ ማጥፋት ቀላል መስሏችሁ ዳግም መታመን ወደማትችሉበት አዘቅት እንዳትወረዱና እየታየ ያለውን የተስፋ ጭላንጭል እያነሳችሁ ባላችሁ አውሎ ንፋስ እንዳታጠፋ አደራ
ተጠንቀቁ ፣ ሕዝብ አይደለም ትናት በሌላ መጥፎ ታሪክ የሚያውቀውን ድርጅት ቀርቶ አዲስ የመጣ ድርጅትን እንኳን ከመቀበሉ በፊት ተስፋ አድርጎት ከኖረው ድርጅት በተግባር በድርጊት የተሻለ ነገር ሲያሳይ ያለውን ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው ፣ አሁን ባለው ሁኔታ መሰረታዊ የኦሮሞ ጥያቄ የታሰሩት ይፈቱ ሳይሆን ለእስራት ያበቃቸው ጥያቄዎች ይመለሱ የሚል ስለሆነ ODP ከጥራጥሬ ወጥቶ የነበረውን የኦሮሞ ተስፋ ABO ከኦሮሞ ጭንቅላት የማጥፋት ደረጃ አልደረሰም ፣ ስለዚህ ይህንን በሰው አዕምሮ ውስጥ ያለውን ተስፋ ማጥፋት የሚቻለው በጦርነት ሳይሆን በተግባር የተሻለ ሆኖ በመገኘት ስለሆነ ጦርነቱን አቁሙና ወደ Yaada Mo’ataa ተመለሱ

Temesgen Gemechu

Oromoon gowwomsaa bira darbeera haqa barbaada haqa Abbaa Biyyummaa viva Qeerroo Bilisummaa Oromoo