የሟች የሐይማኖት አባት ኑሮ በዘዴ በተባለው የቴልቪዥን ዝግጅት ላይ የሟች አባት ቀጥታ በቴሌቪዥን ቀርቨው የሰጡትን ኢንተርቪው ተመልክቻያለሁ ።

የሟች የሐይማኖት አባት ኑሮ በዘዴ በተባለው የቴልቪዥን ዝግጅት ላይ የሟች አባት ቀጥታ በቴሌቪዥን ቀርቨው የሰጡትን ኢንተርቪው ተመልክቻያለሁ ።

አባት አንዳሉት ለልጃቸው ሐይማኖት የላብራቶራ ክሊኒካል Instructor አድቫይዘሯ ደውሎ ጠርቷት ላብራቶሪ መታ ምርምሯን አንድታደርግ ጠርቷት እሷም ልትሄድበት የነበረውን ፕሮግሯሟን ቀይራ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል መሄዷን እና ኢንስራክተሯ የላብራቶሪ ቁልፉን ሰቷት ስራዋን ስትጨርስ ቁልፉን የምታስቀምጥበትን ቦታ ነግሯት ብቻዋን ትቷዋት እንደሄደ አስረድተዋል።
እዚህ ላይ ኢንስትራክተሩ ለምን ደውሎ ጠራት አንደኛ አጠራጣሪነገር ከጠራትስ በውኃላ ለምንስ ጥሏት ሄደ ሁለተኛ አጠራጣሪ ነገር ። ገዳዩ እሷ ያለችበት አራተኛ ፎቅ ድረስ ሐይማኖት ብቻ መኗራን በዚያ ቀን እና ሰአት እንዴት ተገኘ ሶስቸኛ አጠራጣሪው ነገር ሲሆን በመጨረሻው ላይ ወንድሟ እንደተናገረው ሟች አዲስ የፈራ ግኝት እንዳገኘችና ስራዋው ለየት ያለ በኮምፒውተር የታገዘ ሽልማት የምታገኝበት እና ለፍፃሜ የደረሰ እንደሆነ ያስረዳል ።

ከዚህ ሌላ ገዳዩ ወንጀሉን የፈፀመበት ምክንያት ሲጠየቅ እንደተናገረው ሴልፎን ወይንም ላብቶፕ ሰርቄ ባገኝ ሽጬ ለጠቀም ነው ብላል እዚህ ላይ ሌባ ሲሰርቅ speciality አለው ወይንስ ሪሰርች የተደረገበትን ላብቶኘ ነው እያነፈነፈ የሚሰርቀው ? በመጨረሻም ቁልፍ ይዛብኝ ጠፋች ካለ በውኃላ ቤተሰቧቿ በስሟ በተመነዘረው ቼክ ምክንያት ተጠራጥረው የሆስፒታሉ ላብራቶሪ ድረስ የመጡት ሰዎች እና የሆስፒታሉ ሜዲካል ባሉበት በሩ ይከፈት ሲባል ቀድሞ የፈሳ አፍንጫውን ይይዛል እንደሚባለው ፖሊስ ካልመጣ በሩ አይከፈትም ብሎ ድርቅ ማለቱ ከዐንጀሉ ቨስተጀርባ ይህ ኢንስትራክተር(Instructor) ተብዬው ግለሰብ መኖሩን በግልጽ ያመለክታል ስለዚህ ምርመራው ኢንስትራክተሩ ላይ ቦግ ብሎ መውጣት አለበት ። እንደኔ የማስተዋል ከሆነ የወንጀሉ አቀነባባሪ አስፈፃሚ ኢንስትራክተሯ ነው። ለምርምር ከ12 ኛ ክፍል ከደቡብ ክልል መጣ የተባለው የ21 አመቱ ሰው ዐንጀሉን እንዲፈጽም በገንዘብ የተገዛ ክፍያ የተቀበለ ሰው ነው ። ሕግ ግፋ ወንጀለኛን ለፍርድ አቅርብልን እላለሁ አመሰግናለሁ ።
ወንጀለኛ በፍጽም ከፍርድ አያመልጥም። የሕዝብ አይን 360 ዲግሪ ይመለክትሃልና ወንጀልን ፈጽመሕ የትም አታመልጥም ። በመጨረሻም ለምሁር እሕታችን በአረመኔዎች ሕይወቷ ለተቀጠፈው ለሐይማኖት በdhaaሳ ድምፅ ለመሆን ይህንን ሼር በማድረግ ፍተህ የምንጠይቅ መሆናችንን እናሰማ ።

By Fitsum Kebede