የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ለአድማጮች የሰጡት መልስ

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ለአድማጮች የሰጡት መልስ

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚዲቅሳ

ለጥያቄዎቻችሁ መልስ የሚሰጡት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚዲቅሳ ናቸው። ጥያቄዎቻችሁ ከምርጫ የጊዜ ሰሌዳ እስከቦርዱና የቦርዱ ስብሳቢ ነፃነትና ገለልተኛነት የሰፉ ናቸው።

ምርጫው አሁን በተያዘለት ጊዜ መቀጠል አለበት የሚሉ አሉ፤ ፈቀቅ ቢልም ፈቃዳቸው እንደሆነ የሚናገሩ አሉ፤ የብልፅግና ፓርቲ ሕጋዊነት ጉዳይም ከጥያቄዎቹ አንድ ነው፤ የምርጫ ቦርድ የፓርቲዎችን ደንቦችና መተዳደሪያዎች ምን ያህል በቅርበት ይከታተላል? የምርጫ ቦርድ የሥልጣንና አድማስ – በምን ጉዳዮች ላይ እስከምን? ሌሎችም በርካታ ጥያቄዎቻችሁ ተስተናግደዋል። አዘጋጅና አቅራቢም ትዝታ በላቸው ነች።

የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚዲቅሳ የጊዜውን ሠሌዳ አስመልክቶ ለተነሳው ጥያቄ ከሚሰጡት መልስ እንነሳ፤

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።


የቤተ ክርስቲያኒቱ ህብረት ኦኤምኤን የቴሌቪዥን ጣቢያን ከሰሰች

My question is, who is going to take the church to ICC for all the millions of Southern ”pagans” who were murdered during the time of conquest? There are still today genocidal texts in ‘sacred books’ the church has, which were used as justification during southern conquest and wiping out of people. The church blessed the conquest as noble work and actively took part in killings and dispossession of people from their land.Biyya Oromiyaa


ጣቢያው በዘገባዎቹ የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም አጉድፏል ተብሏል

ጴጥሮሳውያን ህብረት የተሰኘውና ለቤተ ክርስቲያን መብት መጠበቅ እንደሚሟገት የገለፀው ማህበር፤ የኦኤምኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ክስ ማቅረቡን ገለፀ፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ህብረት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ ለሠላም ሚኒስቴር፣ ለሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ ለምርጫ ቦርድ፣ ለብሔራዊ መረጃና ደህንነትና ለሌሎች ተቋማት ግልባጭ አድርጐ ለብሮድካስት ባለስልጣን ባቀረበው አቤቱታ ኦኤምኤን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትና ቤተ ክርስቲያንን የሚያጠለሹ ዘገባዎችን አስተላልፏል ብሏል፡፡
ህብረቱ ባቀረበው ክስ ላይ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ፣ በሰሜን ሸዋ ባካሄደው “የምርጫ ቅስቀሳ” ላይ የሀገሪቱን ህገ መንግስትና የምርጫ ህግ በተፃረረ ሁኔታ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለጥቃት የሚያጋልጥ ቅስቀሳና የሃሰት ውንጀላ ፈጽሟል፤ ይህንንም ኦኤምኤን በጣቢያው አስተላልፏል ብሏል፡፡
በተጨማሪም ኦኤምኤን ስለ ቤተክርስቲያኒቱ በሚያስተላልፋቸው የተዛቡ መረጃዎች የተነሳ የዘንድሮ የጥምቀት በዓል አከባበር ላይ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለታየው ችግር መነሻ ሆኗል ብሏል – ህብረቱ፡፡

ህብረቱ በክስ ደብዳቤው፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የተላለፉ የጥላቻ መልዕክቶች ያላቸውንም በዝርዝር አቅርቧል፡፡ በቴለቪዥን ጣቢያው ከተሰራጩ መልዕክቶች መካከልም ‹‹ቤተ ክርስቲያን የፖለቲካ ኢምባሲ ናት›› ‹‹የፖለቲካ ኤምባሲ መፍረስ አለበት››፣ የፊውዳሎች የፖለቲካ ኤምባሲ መፍረስ አለበት›› የሚሉት ተጠቅሰዋል፡፡ ኦኤምኤን ባሠራጨው በዚህ ፕሮግራሙ የቤተክርስቲያኒቱን ክብር እና ልዕልና የሚጋፋ ከመሆኑም በላይ አለም አቀፋዊት የሆነችውን የኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ለተወሰኑ ቡድኖች የሚሰጥ ሆኗል ብሏል – ህብረቱ፡፡
በዚህም የቤተክርስቲያኑቱን በጐሣና በሃይማኖት ከፋፋይ እንደሆነች አድርጐ በማቅረብ ክብሯን የተዳፈረ ፕሮግራም ተሠራጭቷል ብሏል፡፡
የብሮድካስት ባለስልጣንም ተገቢውን የእርምት  እርምጃ እንዲወስድ ህብረቱ ጠይቋል::

Via: addisadmassnews