የ“ማዕከላዊ” እስር ቤት እና የምርመራ ቦታ: ማዕከላዊ: የሰው ልጆች በህይወት እያሉ ደም እና እንባ የሚቀዳበት፣ ህሊና የሚሰለብበት፣ ሞራል የሚኮላሽበት፣ አካል የሚጎድለበት፣ ሳይሞቱ ተስፋ እንዲቆርጡ

የ“ማዕከላዊ” እስር ቤት እና የምርመራ ቦታ: ማዕከላዊ: የሰው ልጆች በህይወት እያሉ ደም እና እንባ የሚቀዳበት፣ ህሊና የሚሰለብበት፣ ሞራል የሚኮላሽበት፣ አካል የሚጎድለበት፣ ሳይሞቱ ተስፋ እንዲቆርጡ የሚደረግበት፣ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጸምበት

(ቪዲዮ፦ ሰለሞን ሙጬ – ከአዲስ አበባ)

የ“ማዕከላዊ” እስር ቤት እና የምርመራ ቦታ

የቪዲዮ ዘገባ፦ ላለፉት 40 አመታት በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና ሰቆቃ ሲፈጸምበት የነበረው በተለምዶ “ማዕከላዊ” ተብሎ የሚጠራው እስር ቤት እና የምርመራ ቦታ ዛሬ ጎብኚዎች ሲመለከቱት ውለዋል። እስር ቤቱ ልዩ ልዩ መጠን እና ቅርጽ ባላቸው ቤቶች የተሞላ ሲሆን እጅግ ጠባብ በሆኑ ክፍሎች የተከፋፈለና ጨለማ የሚበዛበት ነው።

የእስር ክፍሎቹ ቀድሞ የነበራቸው ይዘት እንደተቀየረ እና ቀለም ተቀብተው እና ተጸድተው ለእይታ መቅረባቸውን በስፍራው ታስረው የነበሩ ለዶይቼ ቬለ (DW) ተናግረዋል። እስረኞች ግድግዳዎች ላይ ይጽፏቸው የነበሩ ጽሁፎች ሁሉ እንዲወገዱ መደረጉን የቀድሞዎቹ ታሳሪዎች ይገልጻሉ።

“ማዕከላዊ” ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ለህዝብ ዕይታ ክፍት ሲደረግ ብዙ ቁጥር ያለው ተመልካች በስፍራው ተገኝቶ ጎብኝቶታል። ጎብኚዎች ምስሎችን በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ሲያስቀሩ፣ በሃዘን ተውጠው ሲመለሱም ተመልክተናል።

ጉብኝቱን ያዘጋጀው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ መስሪያ ቤት “ማዕከላዊን” “የሰው ልጆች በህይወት እያሉ ደም እና እንባ የሚቀዳበት፣ ህሊና የሚሰለብበት፣ ሞራል የሚኮላሽበት፣ አካል የሚጎድለበት፣ ሳይሞቱ ተስፋ እንዲቆርጡ የሚደረግበት፣ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጸምበት” ሲል ገልጾታል። የማዕከላዊ እስር ቤት እና ምርመራ ቦታ እስከ መጪው ጳጉሜ 4 ድረስ ለህዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

(ቪዲዮ፦ ሰለሞን ሙጬ – ከአዲስ አበባ)


#Daawwachaa_hidhamna_hidhamaa_Daawwanna!
Kun dhiiga obbolaawaan qabsaa’ota haqaa Maa’ikelaawwii keechatti Girgiddaarratti dibameerudha. Baay’eensaa qalama haaraa dibuun balleessameera. Dhaloota seenaa dhiigaan barreessetu askeechatti dhume.


Barreeffamoota Har’a BBC Afaan oromoo gabaase keesss maqaa Jaal Ibsaa yaadataa yeroo arguu . Seenaan Gootota keenya bara hanga baraa jiraatadha.Abdii fi injifannoo ati mana hidhaa keessatti nuuf kennate har’aa of biraa si dhabnus Yaadannoo umrii keenya guutuutti .Galmee seenaa irraa bara hanga baraa jirta…..Jaal Ibsaa yaadataa.


ይህ ከታች የምትመለከቱት የእጅ ጹሑፍ በምስል ላይ የምትመለከቱት ኢብሳ ያደታ ነው ። በ2009 ማዕከላዊ ታሰረ ። ከዛም ሲፈታ ቀጥታ ኦነግን ተቀላቅሎ ለህዝቡ ነጻነት ታግሎ ሲያታግል ቆይቶ በቅርብ ጊዜ ከ መከላከያ ሰራዊት ጋር እየተዋጋ በውጊያ ላይ ህይወቱ አልፏል ።

እንግዲህ ትላንት ጦቁመው ያስያዙት ናቸው ዛሬ ህይወቱን የቀጠፉት ።

ኢብሳ ሆይ ታርክህ በወርቅማ ብዕር ይጻፋል ፣ የሞትክለት ዓላማም በእኛ ወንድሞችህ ጥረት እውን ይሆናል ።

Boolla kee Bookni Haa Guutu Lubbuun kees Nagaan Haa Boqotu

Dábessá Gemelal