የመጨረሻው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር?

የመጨረሻው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር?
By Tullu Liban

የአማራ ኤሊቶች የብሔር ፖለቲካን በብሔር ተደራጅተው የሚቃወሙ ጉዶች ናቸው። አንድ ነገር በግልፅ መነጋገር ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድሮም የዘር ፖለቲካ ነው። እንደዛሬው በግልፅ ሳይ ነገር “ኢትዮጵያዊ” ሽፋን ተሰጥቶት ሳይገለጥ ለብዙ ጊዜ ቆይቷል። አሁን ግን ጎራ ለይቷል። ጎራው ርዕዮተ ዓለማዊ አይደለም፤ ብሔር ነው።

በአማሮችና አማራ ባልሆኑት መካከል ሆኗል ግብግቡ። የአጼ ኃይለሥላሴን ወይም የደርግን አገዛዝ መሰል የአስተዳደር ዘይቤ ለመመለስ የሚፈልጉ ኃይሎችና ባንድ ወገን ተሰልፈዋል። ኢትዮጵያዊ ካባ አጥልቀው ቢንቀሳቀሱም እኛ በትክክለኛ ስማቸው አማራ ብለን እንጠራቸዋለን። እነዚህ ኃይሎች አሁን በሥራ ላይ ያለው ህገመንግሥት ዋና ጠላታቸው ነው። በሌላ አንፃር ደግሞ አሁን ያለው ህገመንግስት በትክክል እንዲተገበር በሚፈልጉ ኃይሎች ተሰልፈዋል። ፊልሚያው በሁለቱ መካከል ነው።
የአማራ ፖለቲከኞችና ተከታዮቻቸው የብሔር ፖለቲካን የዘር ፖለቲካ ይሉታል። አሁን ያለውን የክልሎች ራስን የማስተደደር ጥያቄ የሁሉ ችግር መነሻ አድርገው ይመለከቱታል። የሚገርመው ግን የክልል የራስ አስተዳደርን የሚቃወሙት በዘር ተደራጅተው ነው። ሰሞኑን ለአብይ የድጋፍ ሰልፍ የሚወጣውን ማህበረሰብ ማየት በቂ ነው። አማሮች ናቸው። ጥቂት የማንነት ቀውስ የሚያጠቃቸው ከኦሮሞና አማራ ተወልደው በአማራ ስነልቦና የታነፁ ሰዎችም አሉበት።

የድጋፍ ሰልፍ ማውጣታቸው ባልከፋ። እየከፋ ያለው ነገር ኦሮሞን ግደልልን፣ እሰርልን፣ አፍንልን መባሉ ነው። ወያኔን ደምስስልን ማለታቸው ላይ ነው። የአማራ ኤሊቶች አቋም በዳንኤል ክብረትና የማንነት ቀውስ ባላቸው በነ ካሳዬ ጨመዳ፣ ዮናታን ተስፋዬና፣ አስቴር በዳኔ፣ ታምራት ነገራ በኩል እየተነገረን ነው። ክልሎችን ማፍረስ የኦሮሞን መሪዎች ማስወገድ የድጋፋቸው ማጠንጠኛ ነው።
ጥያቄው ግን ክልሎቹን አፍርሰው አማሮቹ ኢትዮጵያን ሊገዙ ይቻላቸዋል ወይ ነው። በኢትዮጵያ የኃይሎች አሰላለፍ ውስጥ ትልቁን ሚና እየተጫወቱ ያሉት ሦስት ብሔሮች ናቸው። አማራ ትግራዋይና ኦሮሞ። ሲዳማ፣ ወላይታ፣ አፋርና ሶማሌ ክልሎችም አሰርቲቭ እየሆኑ መጥተዋል። ከአማራ በስተቀር ሌሎቹ ማህበረሰቦች አሁን ያሉ ክልሎች እንዲፈርሱ አይፈልጉም። ይልቁንም የክልልነት ደረጃ ያላጉኙት ጥያቄአቸው እንዲመለስ እየገፉ ነው። ለሌሎቹ የማትመች ለአማራ ብቻ የምትመች ኢትዮጵያ ታዲያ ትዘልቃለች ነው ጥያቄው።

ከተማ ቀመስ አማሮች በሚቆጣጠሯቸው ሚዲያዎች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ስለጮሁም መሬት ላይ ያለውን እውነታ ይለውጡታል ማለት ዘበት ነው። እርግጥ ነው ኦሮሞና ትግራይ በቁጥር አነስ ያሉ ሚዲያዎች አሏቸው። በነበረው መዋቅራዊ አድልዎ ምክንያት ሌሎቹ ገና አቅማቸውን አላዳበሩምና ድምፃቸውን በሚዲያ እንደልብ ማሰማት እየቻሉ አይደለም። አንድ ኦ ኤም ኤን ቢኖር እርሱን በአማራ ኤሊቶች ጩሀት ኮሎኔል አብይ አህመድ ዘግቶታል። ይህ ማለት ግን መሬት ላይ ያለው ሃቅ ይለወጣል ማለት አይደለም።

በብዛት በሀገር ውስጥም በውጭም የሚንቀሳቀሱ ሚዲያዎችን የያዙት አማሮቸ ናቸው። እነዚህ ሚዲያዎች በዘር ተደራጅተው ነው ሌላውን እያጠቁ ያሉት። የተለየ ድምፅ፣ የተለየ አማራጭ አያስተናግዱም። ክልል ይፍረስ፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር ክልሎች ናቸው ይሉናል። መደዴው ጠቅላይ ሚኒስትርም ይህን ጩሀት እውነት ብሎ ተቀብሎ ከማይወጣበት አዘቅት ውስጥ ተዘፍቋል። የርሱ የስልጣን ጉጉትና የነዚህ ኃይሎች ጦረኛ ከበሮ በጋራ ኢትዮጵያን ወደ ሞት እያንደረደራት ነው።

ባሻዬ፣ ከእንግዲህ አንድ ብሔር በሌላው ኪሳራ እየተደሰተ ኢትዮጵያን ማስቀጠል አይቻለውም። ለምሳሌ አማራው በኦሮሞ ላይ እያላገጠ፣ እየፈረጀው፣ እያንገላታው፣ እያሰረው ኢትዮጵያን መግዛት አይቻለውም። የኦሮሞን ሚዲያ እየዘጋ፣ ፖለቲከኞቹን በአሸባሪነት እየፈረጀው፣ ዘብጢያ እየወረወራቸው ኢትዮጵያን ሊያክም አይችልም። ይህ ዘዴ ጊዜው አልፎበታል። ትግራይን ደምስስልኝ ወልቃይትን መልስልኝ የሚል በዘር የተደራጀ ኃይል የኢትዮጵያ በሽታ እንጂ የኢትዮጵያ ሀኪም ሊሆን አይችልም። ግምባር ግምባሩን ፈርክስልኝ፣ በደረት ግጠምልኝ የሚል ሞት ጠሪ፣ ቅጠል በጣሽ ደም አፍሳሽ ደብተራ የኢትዮጵያ ደዌ እንጂ ፈውስ አይሆንም ኃይል ጉልበት፣ እብሪት ትናንት ሰርቶ ይሆናል። በ19ኛውና በ20ኛው ክፍለዘመናት እነዚህ ዘዴዎች ሰርተው ነበር።
የቂሎች ቂል አብይ አህመድ ይህን ዘዴ ዛሬም ሊተገብረው ይሞክራል። ትንሽ እንኳን መሬት ላይ ያለውን እውነታ የማይረዱ ድንዙዛንን ሰምቶ ወደ መቀመቅ እየሮጠ ነው።

በዚህ አያያዝ አብይ የመጨረሻው የኢትዮጵያ መሪ መሆኑን መናገር ነብይነትን አይጠይቅም።
በለው በለው ባዮች፣ ምሁርና ዲያቆን መካሪዎች፣ ቅጥር አንጋቾች፣ ሰልፍ ወጪዎች፣ባንድራ ለባሾች የማያዩት ነገር አለ። በአንድ ሳምንት የገበያ አድማ የኢትዮጵያን መንግስት ማንበርከክ የሚችል ቄሮ ጉልበቱን ባለፈው ሰሞን አሳይቷቸዋል። አሁንም ሌላ ዙር ኢኮኖሚያዊ ዕቀባ ሊተገብር ነው። መሪዎቹ ታስረው የሚተኘ ኦሮሞ ካለ እርሱ የሞተ ብቻ ነው። ፊሊሚያው ግልፅ ነው። አማራ ኦሮሞን አንበርክኮ ይገዛል ወይስ አይገዛውም ነው። የህግ የበላይነት ገለመሌ የሚባል የዳቦ ስም ቦታ የለውም። እንከባበር እያልን ነው። እስካሁን አሰላለፉን ያልተረዳ ካለ እርሱ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጭ ነው። አንድ ነገር ግልፅ መሆን አለበት። የኦሮሞ ህዝብ የማይፈልገው አገዛዝ ከእንግዲህ ቦታ የለውም። ኦሮሞ ጦርነቱ ከማን ጋር እንደሆነ ገብቶታል። ምን ላይ በማተኮር ታንክና መትረየሱን እንደሚያሸንፍ ያውቃል። ጀዋር፣ በቀለ፣ አብዲ፣ ሽጉጥ፣ ሚካኤል፣ ሃምዛ ባጠቃላይ አስር ሺዎች የኦሮሞዎች ታስረው የምትረጋጋ፣ የምምትታከም ኢትዮጵያ አትኖርም። የአማራ ኤሊት ወይም የዚህ ኤሊት ቅጥረኛ ኦሮሞን እያሰረው፣ እየፈረደበት፣ እያስፈረደበት ኢትዮጵያ ማከም አይቻለውም።

ይልቅ እነዚህ የህግ የበላይነት መከበር ኦሮሞ ሲገደል፣ ሲታሰርና ሲገፋ መሆኑ ደስታ እንደሚሰጣቸው ማየት ወገኖች ወደ ህሊናቸው ሊመለሱ ይገባቸዋል። በዚህ ዓይነት በሌላላው ሞትና ስቃይ የሚፈነድቁ ወገኖችን ማየት ያማል። ለኢትዮጵያ የሰከነ ፖለቲካም መንገዱ በጣም ጠባብ መሆኑን ያሳያል። ኢትዮጵያ እንዲትቀጥል ከተፈለገ አዋጩ መንገድ አንድና አንድ ብቻ ነው። ደግሞም እርሱ መንገድ ቀላል ነው። ከማሰርና ከመግደል በላይ ቀላል ነው። የኦሮሞ ፖለቲከኞችን መፍታት፣ ለጠረጴዛ ዙሪያ ዉይይት በሩን በሰፊው መክፈት። ስልጣን ለሽግግር መንግስት ለማስረከብ መዘጋጀት። ኢትዮጵያ ምናልባት የምትታከም ከሆነ በውይይት ብቻ ነው።
አለበለዚያ አብይ አህመድ ስሎቮዳን ሜሎሶቪች የመጨረሻው የዩጎዝላቪያ ፕሬዝዳንት እንደሆነ ሁሉ፣ አብይ አህመድም የመጨረሻው የኢትዮጵያ ኤምፓየር ጠቅላይ ሚኒስተር መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው።


የቀሩት ምርጫዎች

BY Mekbib Gebeyehu
·
ኮሎኔል አቢይ ብዙ ችግሮች ዉስጥ ገብቶአል. ችግሮቹ ዘርፈ-ብዙና ስር የሰደዱ ናቸዉ. በኔ ግምት ችግሮቹ ኮሎኔል አቢይ መፍታት ከሚችለዉ በላይ ሄደዋል. የያዜዉ መንድ የጥፋትና ሊሆን የማይችል መሆኑን ቢገነዘብ የብዙ ህይወት ማለፍንና የንብረት መዉደምን መቀነስ ይቻላል. “When you have eliminated the impossible, whatever remains, however improbable, must be the truth”. የሚባል አባባል አለ.

ኮሎኔል አቢይ ቢያንስ ሁለት ሊሆኑ የማይችሉትን ከአላማዉ ማሰጣት አለበት. በጥቅሱ እንዳነሳሁት የቀረዉ ምናልባትም ቢሆን እዉነት ይሆናል . ይህ የማይሆነዉን የማስወገድ ዜዴ በምርምር እንዲሁም ለችግሮች መፍትሄ በማምጣት ረገድ ይጠቀሙበታል.
ዛሬም ሆነ ወደፊት በዚይች ሃገር የማይሆኑት፡

1. ኢትዮጵያ ዉስጥ አሃዳዊ አስተዳደር በፍጹም ሊመሰረት አይችልም. ሙከራዎች አይደረጉም ማለት አይደለም፣ ግን በፍጹም አይሳካም. ለብዙ ህይወት መጥፋትና ንብረት መዉደም ዋናዉ ምክንያት ሊሆን ይችላላ. የአሃዳዊዉ ስርአት አቀንቃኞች በብዛት ካንድ ብሄር ብቻ የወጡ የፖለቲካ ኤሊቶች መሆናቸዉና ስርአቱ ተሞክሮ የከሸፈ መሆኑ ከምርጫዉ ዉጪ ያደርገዋል. የፈደራል ስርአቱ ድክመት እንዳለ ሆኖ የተለላያዩ ብሄሮች ከፈደራል አስተዳደሩ ያግኙት ጥቅም ለምሳሌ በማንነት፣ በቁዋንቁዋና በባህል አከባቢ አሃዳዊዉን ስርአት እንዳይቀበሉ ያደርጋል. በመሆኑም ያአሃዳዊው ስርአት ሊሆኑ ከማችሉት ዉስጥ የሚመደብ ነዉ. ስርአቱ እንደ ነፍጠኛዉ ስርአት ላለመመለስ ሄዶአል.

2. ኮሎኔል አቢይ አምባገነን ሆኖ ማስተዳደር አይችልም. የህዝቡ ንቃተ ህሊና የደረሰበትና አልገዛም ባይነቱ ጸጥታዉን ለማስጠበቅ አቅም ያሳጣዋል፡ መቆጣጠር ወደ ማይቻልበት ሁኔታ ያደርሰዋል. የኮሎኔሉ ወደ አስመራ ሩጫ ለዚህ ማስረጃ ነዉ. ኤሪትሪያ ደግሞ ብዙ የሚትረዳዉ አይመስለኝም. የአቢይ ለራሱ ጥበቃ ከኢትዮጵያ ይልቅ በኢርትሪያ ጠባቂዎች መተማመን በሌሎች አከባቢ ቅራኔ ያስነሳል. በዉጪ ወታደር እርዳታ አምባገነን መሆን ከባድ ነዉ. የኦሮሚያ ፖሊስ ካለፈዉ የተማረዉ ልምድ አለዉ. ሁኔታዎቹ እየገፉ ሲመጡ ከራሱ ህዝብ ጋር ይሰለፋል. የመከላከያ ሰራዊቱም ቀስ በቀስ ያንኑ ይከተላል. ይህ ብቻ ሳይሆን ኤኮኖሚዉም ለዚህ አመቺ አይደለም. ያለም አቀፉም ህብረተሰብ የኮሎኔሉን ማንነት እየተረዳዉ ነዉ. ብዙ የመገናኛ መሳሪያዎች በሰፊዉ እየዘገቡ ነዉ.
ባጭሩ ከላይ ያነሳኋችዉ ሁለት ሁኔታዎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ ሊሆኑ የማይችሉ ናቸዉ. ያንን ስራ ላይ ለማዋል መስራት የጥፋት መንገድ ነዉ. የአማራዉ ኤሊት ይህ ሳይገባዉ ቀርቶ ሳይሆን “ምናልባት ቢሳካ” ከሚል አስተሳሰብ ነዉ. ያን አስተሳሰብ ቢትዉ የበለጠ ይጠቀማሉ.

ሊሆኑ የሚችሉት”however improbable”

1. በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ብሄር ተኮር ጠንካራ ፈድራሊስም ሊፈጠር ይችላል. ይህ አዝማሚያ በሰፊዉ እየታየ ነዉ. ብዙ ጥናት አዘል ስብሰባዎች እየትካሄዱ ነዉ. የፈደራል ሃይሉ ማለትም ከአምራዉ ኤሊት በስተቀር ሁሉም በዚህ ጎራ ዉስጥ የተሰለፉ ናቸዉ. የተለያዩ ብሄሮች ለምሳሌ የሲዳማ፣ የሃረሪ፣ የትግራይ፣ የቅማንት ወዘት ተወካዮች ትናንት ኦሮም ግሎባል ፎሩም ባካሄደዉ ስብሰባ ላይ የተናገሩት አንዱማስረጃ ነዉ.
2. ኢትዮጵያ የዛሬዉን ቅርጽዋን ታጣለች. ለምሳሌ ትግራይ ወይም ኦሮሚያ ወይም ሁለቱም የራሳቸዉን መንግስት መመስረት ይችላሉ. ለብዙዎቹ ይህ እስኪሆን እዉነት አይመስልም. ሲሆን ግን ለመቀብለ ይገደዳሉ.ይህ የመጀመሪያዉ ሰናሪዮ ካልተሳካ የሚመጣ ነዉ. እንዲዲህ ሊሆኑ የማችሉትን ካስወጣን ሊሆኑ ከሚችሉት ሁለት አማራጮች ጋር ቀርተናል. ማተኮር ያለብን በነሱ ላይ መሆን አልበት. ያንን መረዳት ከላይ ለመንካት እንደሞከርኩት የሚጠፋዉን ህይወትና የሚወድመዉን ንብረት መቀነስ ይቻላል.


የሀበሻ የቅኝ ግዛት ሰለባ የሆኑ ኦሮሞዎች

በፈልመቱ ሮሮ (Falmattuu Roorroo)

ይህ እንደ ርዕስ የቀረበዉ ታሪካዊ ሂደት እጅግ በጣም ትልቅ ችግር ከመሆኑ የተነሳ ሰፋ ያለ ትንታኔን የምጠይቅ ጉዳይ ነው። ስለዚህ ምናልባትም ሌላ ጊዜ በሰፊዉ እመለስበት ይሆናል። ለዛሬዉ ግን ይህንን አጭር ፅሁፍ እንዳቀርብ ያነሳሳኝ አንድ ነገር ኣለ። በቅርቡ ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ስለዚሁ ጉዳይ ስንወያይ፣ ያለኝ ነገር ስለነበረ ለሱ ማብራራት የሞከርኩትን ለዉይይት ለማቅረብ ፈልጌ ነዉ።

ውድ የኦሮሞ እሀቶቼ እና ወንድሞቼ ፣ የአንድ እናትና የአንድ አባት ልጆች፦ ወደ ጉዳዩ ከመግባቴ በፊት በቅድምያ ላሳስባችሁ የምፈልገው በመልካም አስተሳሰብ እና በቅን አይምሮ መነሻ ሃሳቤን እንድትረዱና ይህንን ጉዳይ እንድንነጋገርበት እና እንድንማማርበት ነው።

በመጀመሪያ ከራሴ ልጀምርና እኔ ተወለጄ ያደኩት በሰሜን ኦሮሚያ ቱለማ (Tuulamaa) አካባቢ ሲሆን ካለው የቦታ አቀማመጥም ሆነ ከነበረዉ ተፅኖ አንፃር እራሳቸዉን ሆነዉ የማደግ አድል ካልገጠ ማቸዉ ሰዎች መካከል አንድዋ ነኝ ብል ማጋነን አይሆንብኝም። ይህም ማለት ከኦሮሞ እና ትና አባት መፈጠሬን እንጂ እራሴን መሆንና ቋንቋዬን የመናገር እድሉ ቢኖረኝም ፤ በትዉልድ አካባብዬ የሚጠቀሙት ቋንቋ በጣም የተቀላቀለ ከመሆኑ የተነሳ እኔም ስጠቀምበት የነበረዉ አፋን ኦሮሞም ይሁን አማርኛ ሁለቱም የተስተካከሉ አልነበሩም። ብቻ በጠቅላላው ኦሮሞ ሆኜ መወለዴን እንጂ እኔነቴን የሚገልፅ ፣ ባህሌንና ኦሮሞነቴን የሚያንፀባርቅ ነገር ሁሉ ተነጥቄ እራሴን ፈልጌ ሳላገኝ ቆየሁ።

ወደ ፊንፊኔ (Finfinnee) ከመጣሁ በኋላም ብዙ እራሴን ፈልጌ የማግኘቱ እድል ኣልገጠመኝም። እንድያዉም በራሴ እንዳፍርና እንድሸማቀቅ የሚያደርጉ ነገሮችን መስማትና ማየት የተለመደ ነበር። ብዙ የማዉቃ ቸዉ ሰዎችም ሆኑ ዘመዶቼ ኦሮሞ ሆነው ግን እንደ እኔው ማንነታቸውን ያጡና ፍለጋ ላይ የነበሩ ገጥመዉኛል። ብዙዎቹ ግን ባገኙት ኣጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም የኦሮሞን ታሪክ በማንበብም ሆነ ወደ መጫና ቱለማ የመደራጃ ማህበር በመሄድ የኦሮሞ ልጆችን በማግኘት እራሳቸዉን ፈልገው እንዲያገኙና ቋን ቋውን እንዲማሩ፤ ባህላቸውን እንዲያውቁ፥ በራሳቸው እንዲኮሩና እንዲተማመኑ በር ተከፈተላቸው ። ይሁን እንጂ ይህን እድል ያላገኙ በርካታ ቁጥር ያላቸዉ ኦሮሞዎች ነበሩ ዛሬም ኣሉ።

የዛሬው ዋናው ሃሳቤና ትልቁ ነጥቤ የሚያተኩረዉ የኦሮሞን ህዝብ ለዘመናት ሲከተለን ስለኖረው በተለይም የእምነትና የቋን ቋ ጭቆና ነው። ይህንን ስል በባሀላችን ላይ ተፅዕኖ አልደረሰም ማለቴ አይደለም። ሆኖም ግን እነኚህን ሁለት ትልልቅ ነገሮችን በመነጠቃችን ያጣነው እጅግ ብዙ ነገሮች ኣሉ። ስነ ልቦናዊ በደልን ጨምሮ ተገዢነት ያደረሰብን እስከ ዛሬም ድረስ ይከተለናል። እምነታቸ ውንና ቋን ቋቸውን ተነጥቀው ፣ ወደውም ይሁን ተገደው የለሎችን ዲሪቶ በመከናነብ በሃበሻ ጥላ ስር ተሸሽገው የምገኙ ብዙ ኦሮሞዎች እንዳሉ የማይታበል ሀቅ ነዉ። እጅግ በጣም ትልቅ እውቀት ያላቸው ምሁራን፥ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ እስከ ዛሬም ድረስ ኢትዮጲያን በኣለም ላይ አያስተዋወቁ የሚገኙ ኣትሌቶች፥ ኣንገፋውን ኣርቲስት ጥላሁን ገሰሰን ጨምሮ ሃበሾች የሚኩራሩበት ድንቅ ችሎታ ያላቸው ዘፋኞች፥ የኦሮሞ ልጆች ናቸው።

እነኝህን ኦሮሞዎች ዛሬ ካለዉ ሁኔታ ጋር ሳወዳድር ከእነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ ቋን ቋውን፥ ባህሉን ፥ በአጠቃላይ ማንነታቸውን የሚያውቁ ቢሆኑም እራሳቸውን መሆን ያቃታቸው ለምን እንደሆነ ለእኔም ትልቅ ጥያቄ ነው። ኣንድ ግን የተረዳሁት ነገር ቢኖር ከተገዛንበት ረጅም ኣመታት ኣንጻር ስናይ ዛሬም እንደ ኣዲስ መወለድን የሚፈልጉ ብዙ ኦሮሞዎች እንዳሉ ይሰማኛል።

ይህንን ጉዳይ በሁለት ነጥብ ለማስቀመጥ እሞክራለሁ፦

፩ኛ) ኣትሌቱ በኣለም መድረክ እምዬ ኢትዮጲያ ሲዘምር፥ ዘፋኙ ደቻሳ የመሳሰሉ አራሳቸውን ሚኪያስ ብለው በመጥራት እማማ ኢትዮጲያ ብለው በመዝፈን፥ በጣም ኣዋቂና የተማረ ነው የምንለው ደግሞ ብእሩ እምቢ ያለው ይመስል እስር ቤትን ስላጥለቀለቀው የኦሮሞ ህዝብ፥ ከትምህርት ገበታው ላይ ስለሚባረረውና ስለሚገደለው የኦሮሞ ተማሪ፥ ከመሬቱ ላይ ስለሚፈናቀለው የኦሮሞ ገበሬ ወዘተ ከመፃፍ ይልቅ ስለ እሚዬ ኢትዮጲያ ኣኹሪ የዘመናት ታሪክ እያለ ሲሞነጫጭር ምናልባትም ወደው አንዳልሆነ ተረዳሁና እዉነትም ዳግም መወለድ ኣለባቸው ኣልኩኝ። ፪ኛ) በሌላ በኩል ግን በብዙ የውድ የኦሮሞ ልጆች ደምና መራራ ትግል ሂደት ዉስጥ ራሳቸዉን ፈልገዉ ያገኙ፥ ታሪኩን ጠንቅቀው የሚያውቁ፥ እህቶቻቸው ና ወንድሞቻቸው ጎን ተሰልፈዉ ባለው እውቀትና ችሎታ ሁሉ በጋራ ለመታገል የሚፈልጉ ብዙ ሰዎች እንዳሉም ሰምቻለሁ ኣጋጥመውኛልም።

REPORT THIS AD

ይሁን እንጂ የእንደዚህ ኣይነት ጠንካራና ጎበዝ ኦሮሞዎች ችግር ብዙ ጊዜ ወደ ኋላ ሊመልሳቸው ባይችልም እንዃን ፤ ነገር ግን ወደ ህዝባቸው በመቀላቀል አንደፈለጉት ሃሳባቸውን ከመግለፅ የሚገታቸው የኦሮምኛ ቋንቋ ችግር ነው። ብዙዎቹ ኣፋን ኦሮሞን (Afaan Oromoo) መጻፍም ሆነ መናገር ኣይችሉም። በእርግጥ ባገኙት ኣጋጣሚ ሁሉ ሊማሩ ይሞክራሉ። ነገር ግን ብዙዎቻችን ቋንቋውን ባለመቻላችን ብቻ እንድንገለልና በኣንዳንድ ኦሮሞዎች ዘንድ ተቀባይነትን ያጣን፤ የተገፋን ኣለን ይላሉ።

እንደነዚህ ኣይነት ኦሮሞዎችን እንዴት ወደ ራሳችን በማምጣት ልንረዳቸው እደምንችልና እንዲሁም የኦርቶዶክስ አምነት ተከታይ በመሆናቸው መገለል ይሰማናል ብለው የሚያስቡትን በውስጣቸው በራስ መተማመንን ፈጥረን ፤ ቋንቋውን ኣለመቻላቸው ብቻ ከኦሮሞ እንደማያገላቸው መንገድ እናመቻች የሚለውን ጥያቄ ኣነሳሁ። ታዲያ በዚህ ጊዜ ነበር ቀደም ብዬ የጠቀስኩት ጓደኛዬ ኣንድ ነገር ያለኝ፥ ምንጊዜም ከአማራ ስር መዉጣት አትፈልጊም (yoomiyyuu Amaaraa jalaa bawuu hin feetu) ነበር ያለኝ።

እንግዲህ የኦሮሞ ልጆች ሃሳቤን በመልካም ኣስተሳሰብ ተረድታችሁ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከማይፈልጉት ጎን ተሰልፈው ትግላችንን ወደ ኋላ የሚያኋትቱብን ወገኖቻችን ፤ ዛሬ ሃበሻ በጣም የምትኮራባቸውን ኣትሌቶችና ኣርትሥቶች ለአናት ሃገራችን ኦሮሚያ እንዲሰሩና ከኦሮሞ የነጻነት ትግል ጎን እንዲሰለፉ ፣ ወደ ቀና መንገድ አንዴት እንመልሳቸው በማለት በጋራ መፍትሄ መፈለጉ የተሻለ ይመስለኛል።

ሌሎችንም የኦሮሞ ብሔርተኞችን ችግሩ ከእነሱ እንዳልሆነና ለዘመናት የደረሰብን ጭቆና ኣሻራ ኣሁንም ድረስ ተሸክመን ያለነው ተገዢነት ባህላችንና ቋንቋችንን እድንነጠቅ ስላደረገን ፣ ፍዑም በራሳቸው መሸማቀቅ እንደሌለባቸውና ኦሮሞነታቸውን ኣተያያቂ እንደማያደርግ በማስረዳት በራስ በመተማመን ከወገኖቻቸው ጋር ትግሉን እንዲቀጥሉ ማድረጉ ላይ ብንሰራበት ጥሩ መፍትሄ ነዉ ብዬ አምናለሁ።

ሃሳቤን ከማጠቃለሌ በፊት በስተመጨረሻ ማስተላለፍ የምፈልገዉ መልዕክት ሁላችንም በበሰለ ኣስተሳሰብና በቅን እንደምንነጋገርበት ተስፋ ኣደርጋለሁ። የራሱን ጠማማ የሚያቃናው ባለቤቱ ነው ይባል የለም? እንኳን እኛ ለዘመናት እየተገዛን ያለነው ይቅርና ነፃነት ኣግኝተው እንኳን ቋንቋቸውንና ባህላቸውን መልሰው ሊጠቀሙበት ያልቻሉ ሃገሮች ኣሉ። ስለዚህ የማያውቀውን ማስተማሩ ላይ እናተኩር ነው መርሆዬ ባጭሩ። ይህ የመነጋገሪያ ሀሳቤ አማርኛን ማንበብ በማይችሉ ወገኖቼ ዘንድ እንድደርስ ይህንን ፅሁፍ በኦሮምኛ ቋንቋ በQubee Afaan Oromoo ለማቅረብ እሞክራሉሁ።

ድል ለነጻነት ታጋዮቻችን

ነጻነት ለኦሮሚያ ሃገራችን

ቸር እንሰንብት

Falmattuu Roorroo: falmattuur@gmail.com