የመካሪው ስህተት ወይም የፖለቲካ ጠልቃ ገብነት ፍላጎት ይሆናል ንጂ በህገመንግስቱ ክፍተት የለም።

ጉዳዩ፣ ከአለማወቅም በላይ፣ የአብይ ድርቅና ቢሆንም… እንደዚህ እውነቱን መግለጡ ለታሪክም ለትዝብትም ይጠቅማል።

#የመካሪው_ስህተት_ወይም_የፖለቲካ ጠልቃ_ገብነት_ፍላጎት_ይሆናል_እንጂ_በህገመንግስቱ_ክፍተት_የለም።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል የመዋቅር ጥያቄዎች በህገመንግስቱ መሰረት ለምን እንዳልተመለሰ ሲጠይቃቸው ስመልሱ፦

“…ህገመንግስቱ ክፍተት አለ፤ ለምሳሌ አንቀፅ 47(3) መ ላይ ‘የክልሉ ምክር ቤት ለጠየቀው ብሔር ወይም ብሔረሰብ ወይም ህዝብ ሲያስረክብ’ ይላል።ይህ ለማን እንደሆነ ግልፅ አይደለም” ብሎአል።

በዚህ መልስ ላይ ሁለት ነገሮች ማለት እንፈልጋለን።

1ኛ የጠቅላይ ሚንስትሩ መልስ የተነጣጠረው እጃቸውን መክተት ለፈለጉት የሲዳማ ክልል ጥያቄ መሆኑን ነው። ምክንያቱም አባሉ የጠየቁት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ይግባኝ ስላስገቡት ለሎች የደቡብ ክልል ዞኖች ጉዳይ ሆኖ ሳለ ጠ/ሚንስትሩ ያወሩት ግን ሁሉ ነገር አልቆ ርክክብ ደረጃ ላይ ያለው ጉዳይ ነው። ይህ ደግሞ የሲዳማ ጉዳይ መሆኑ ግልፅ ነው።

2ኛ ርክክቡን በተመለከተ ህገመንግስቱ ስህተት አለበት ያሉት አግባብነት የሌለው ነው። ርክክቡ ለማን ማድረግ እንዳለበት ግልጽ ነው።ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉን። አንደኛው በህገመንግስቱ ውስጥ ዋና ሀሳብ እንጂ እንደሌሎች ሕጎች ሁሉም ህደት ወይም ዝርዝር ጉዳዮች አይፃፍም። ሁለተኛ በህገመንግስቱ አንቀጽ 8 (2) ላይ የህዝብ ሉአላዊነት የሚገለጸው በተወካዮቻቸው ወይም በቀጥታ በመረጧቸው ሰዎች አማካኝነት እንደሆነ በግልጽ ይደነግጋል። የሲዳማ ህዝብ የተወከለውም ጥያቄውን አቅርቦ የነበረው የሲዳማ ዞን ምክር ቤት ነበር። አንቀፅ 47(3) መ ” ምክር ቤቱ ለጠየቀው ብሔር….ሲያስረክብ” ስል የሚረከበው የሲዳማ ብሔር ምክር ቤት መሆኑ ግልፅ ነው።

#ታዲያ_ስህተቱ_ከየት_የመጣ_ልሆን_ይችላል?

1. በአማካሪዎቻቸው፦ የጠቅላይ ሚንስትሩ አማካሪዎች አብዛኛው አሃዳዊነትን የሚያቀነቅኑ ሲዳማ ብሔራዊ ክልል እውን እንዳይሆን የምሰሩ፣ ሲዳማ ክልል ክላስተር ሆኖ አማርኛ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ለት ቀን የሚሰሩ ናቸው። እነዚህ ሰዎች ፍላጎታቸው እንጂ ልመጣ የሚችለውን አደጋ ደንታም የላቸውም። ስለዚህ አውቀው ያሳስቱታል።

2. ሌላ መንስኤ ልሆን የሚችለው ጠ/ሚንስትሩ እራሳቸው እንዲህ አይነት ውሳኔ ምን አይነት አደጋ ልያስከትል እንደሚችል ቀድሞ ባለመገመት በፖለቲካ ጠልቃ ለመግባት አስበው ልሆን ይችላል። ምክንያቱም ባለፈው ጊዜ ጠቅላይ ሚንስትሩ ደቡብ ሰዎች ጋር ንግግር ሲያደርጉ ”ሲዳማ ቢወስንም ማንን ይዞ ክልል መሆን እንዳለበት አልወሰንም” ብለው ኢ_ህገመንግስታዊ ንግግር ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። መቸም ብሔሩ የራሱን ጉዳይ/እድል በራሱ ብቻ መመለስ እንዳለበት አንቀጽ 39(1) በግልጽ ተደንግጎ እያለ እኔ ሳልወስን አይሆንምማለታቸው በሕገመንግስታዊ መብት የፖለቲካ እጃቸውን ማስገባት ፍላጎት እንዳላቸው ያሳያል። በዚህ ረገድ ለሲዳማ አስተዳደርም ህዝቡን እንዲያሳምኑ ድብቅ ትዕዛዝ እንደሰጡም ይነገራል።

ህዝቡ በተጠንቀቅ ቆሞ ለዘመናት ታግለው በርካታ ደሙን አፍሰው ያመጣው ነፃነት እንዳይነጠቅ መጠበቅ አለበት እንላለን።

Buurisame Qanisalo Jaja