የመላው ኦሮሚያ የቄሮ ለነጻነት እና እኩልነት መዋቅር አቋም

የመላው ኦሮሚያ የቄሮ ለነጻነት እና እኩልነት መዋቅር አቋም
 
በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች የሚገኙ የኦሮሚያ ቄሮ ለነጻነት እና እኩልነት መዋቅር ባደረገው ውይይት ሃገሪቱ ካለችበት የፖለቲካ አረንቋ በመነሳት ለዚህ ሃገር፣ ለብሄር እና ብሄረሰቦች፣ እዲሁም ለኦሮሚያ ዜጎች የሚከተሉትን የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፈናል፡፡
ለሰፊው የኦሮሞ ህዝብ እዲሁም ለብሄር እና ብሄረሰቦች፣ እና ለኦሮሚያ ዜጎች እንዲሁም ለኦሮሚያ አዋሳኝ ክልሎች ጥቅም እዳለው በመወያየት ድርጅታችን ኦነግ ያስላለፈውን ውሳኔ በመቀበል ለተግባራዊነቱም ሁሉን አቀፍ ውይይት እዲካሄድ እንሰራለን
የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ኢምፓየር ስርዓት ውስጥ ወዶም ይሁን በስዓቱ ባደረበት ጫና ምክንያት ስርዓቱንም ሆነ ስርዓቱ ስር የሚተዳደሩ ህዝቦችንም ተሸክሞ እዚህ ደርሷል፡
 
ይሁን እንጂ ይህንን ፍቅር እንጂ ጥላቻን የማያውቅ እና አቃፊ ህዝብ ከሌሎች ጋር አብሮ መኖ የማያውቅ እና የተጠላ በማስመሰል ሲያልፍ ሲያገድም በነበሩ ስርዓቶች ውስጥ ሲከሰቱ የነበሩ ችግሮችን ሁሉ በኦሮሞ ህዝብ ላይ በመጫን የተለያዩ አዋጆችን በህዝቡ ላይ በማውጣት ስራ ላይ አውለዋል፡፡
 
ለምሳሌ፤
 
የጸረ ሽብር አዋጅ፣ የመሬት ሊዝ አዋጅ፣ የኢንቨስትመንት አዋጅ፣ የማስተር ፕላን አዋጅ እና የመሳሰሉትን ማንሳት ይቻላል፡፡
ከዚህም በላይ በዚህ ሃገር በ1983 በነበረው የሽግግር መንግስት በተለያዩ የሐረርጌ እና አርሲ አካባቢዎች ህዝቡን እና ለህዝቡ የሚፋለመውን ድርጅት በተለያዩ ክስተቶች ስም በማጠልሸት በሐረርጌ – በደኖ እንዲሁም በአርሲ – አርባጉጉ የሰሩትን ዶክመንተሪ መመልከት ይቻላል፡፡
ሁል ጊዚ የኢትዮጵያ ኢምፓየር በህዝቦች መካከል ጥፋት እየፈጸመ ኦሮሞ እና የኦሮሞን ህዝብ የሚወክለው ድርጅት ነው ይህንን የሚያደርገው በማለት የሚጽፉት ልብ ወለድ ለኦሮሞም ሆነ ለኦሮሚያ ዜጎች አዲስ አይደለም፡፡
 
በ2003 ዓ.ም የጸረ ሽብር ህጉ በታወጀ ጊዜ ብዙ የኦሮሞ ልሂቃን እና ፓርቲዎችን ከስራ ውጪ አድርጓል፡፡
የመብት ጥያቄ የጠየቀውን የኦሮሞ ህዝብ ባደረሱበት ረገጣ እና ጫና ቀኤ እና ንብረቱን በመዝረፍ፣ በማስፈራራት፣ በማሰር፣ በመገግደል፣ ከቤቱ በማሳደድ ስደተኛ እንዲሆን በማድረግ እንዲብድ እና እንዲቸገር ተደርጓል፡፡ ሌሎች በጎረቤት ሃገራት አጥንታቸው እንዲከሰከስ፣ ሌሎች ደግሞ የአሞራ እና አሳ ነባሪ እራት እንዲሁም ሌሎች በጎረቤት እና በተለያዩ ሃገራት ውስጥ የሰው ተላላኪ ሆኖ በመኖር አቻ ለሌለው መከራ ተዳርገዋል፡፡
ዲፕሎማሲ በሚል ስም የኦሮሞ ህዝብ ከጎረቤት ሃገራት ጋር በሰላም እንዳይኖር በብሔራዊ ደህንነት አካላት አማካኝነት ከፍተኛ ደባ ሲሰራበት ቆይቷል፡፡ ለምሳሌ ያህል በሱዳን፣ ኬንያ፣ ጅቡቲ እና ሶማሊያ ብዙ የኦሮሞ ልጆች በኦሮሞነታቸው ብቻ ተወንጅለው በኢትዮጵያ ኢምፓየረር ደህንነት እና በጎረቤት ሃገራት ትብብር በኦሮሞ ልጆች ላይ ሲደርስ የነበረው መከራ ከባድ ነበር፡፡ ከዚህም ውስጥ በኢንጅነር ተስፋሁን ጨመዳ ላይ የደረሰውን እግልት ማንሳት ይቻላል፡
 
ኦሮሞ እንደ ህዝብ በአላፊ አግዳሚ የኢትዮጵያ ኢምፓየር ስዓቶች ተጎዳ እንጂ አንዳች ጥቅም እዳላገኘ እየተረዳ መጥቷል፡፡ ከዚህ በመነሳት የራሱን ዕድል በራስ በመወሰን በህዝብ እና ለህዝብ የጠመረጠ የራሱን መንግስት መምረጥ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ወሳኝ መሆኑን በአግባቡ ተረድቷል፡፡
በዚሁ መሰረት፤
 
ሀ. ማንኛውም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ውስጥ እና አጎራባች የሚኖር አካል ኦነግ ያወጀውን የኦሮሚያ ብሐራዊ ክልላዊ መንግስት አዋጅ ማክበር እና ተቀብሎ እዲተዳደርበት በአክብሮት እናሳውቃለን፡
 
ለ. የዚህ ሃገር ህገመንግስት ሲያልፍ ሲያገድም የተለያዩ አዋጆችን በመጠቀም ልጆቻችንን ከምድረ ገጽ የማጥፋት አዋጅ ስላወጀብን እኛም እንደ ህዝብም ሆነ እንደ ብሁር ብሄረሰቦች/የኦሮሚያ ዜጎች የህዝባችንን ደህንነት እየጠበቅን የዜጎቻችንን ፍላጎት በማሟላት ክልላችንን ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት በማስፈን ህገመንግስቱ እንደሚለው ከፈለግን ከጎረቤቶቻችን ጋር ሆነ ህብረ ብሄር ፌደራሊዝምን በማረጋገጥ ከህዝቦች ጋር በአብሮነት መኖር፤ ከፈለግን ደግሞ አንቀጽ 39ን በማረጋገጥ የራሳችንን ነጻ ሃገር ለመገንባት ህገመንግስታዊ መብት አለን፡
በመሆኑም በዚህ አሸባሪ ስርዓት ህዝቦችን ከገጠመው የፖለቲካ አረንቋ ጋር በተያያዘ እየወደመ ያለውን የህዝቦች ሃብት እንዲሁም እየተቀጠፈ ያለውን የዜጎች ህይወት በማትረፍ በክልላችን ኦሮሚያ ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት በማምጣት በህዝቡ ለህዝቡ የተመረጠ መንግስትም ሆነ ነጻ ሃገር ለመገንባት በኦነግ የታወጀውን የኦሮሚያ ብሔራዊ የሽግግር መንግስት ምስረታን ማሳካት ጊዜው የሚጠይቀው ግዴታ ነው ብለን አናምናለን፡፡
ዘመኑ የባርነት ቀንበር ማብቂያ ዘመን ነው!
 
ድል ለኦሮሚያ ዜጎች!
November 4/2020