የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አገር ለማፍረስ የተቀመጠ ነው ያለውን የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 እንዲሰረዝ ጥያቄ አቀረበ፡

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አገር ለማፍረስ የተቀመጠ ነው ያለውን የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 እንዲሰረዝ ጥያቄ አቀረበ

Lunatic Abdi Iiley tried to invoke article 39 and failed. It was an illegal move only intended to extend his stay on power.

While it is a good lesson the country absorbs, what Abdi Iiley did can’t be taken as an excuse to bash a perfectly reasonable and justifiable article on the constitution.

Nothing can actually annul or remove article 39. Even state of emergency can’t suspend it.

It is very very hard to change Ethiopian constitution. But hey who knows what AEUP is capable of? They might convince all states in the federation to back constitutional amendment. We all actually want constitutional amendment but the articles on our mind differ.

Biyya Oromiyaa

መኢአድ አንቀጽ 39 እንዲሰረዝ ጠየቀ

(ethiopianreporte)—-የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አገር ለማፍረስ የተቀመጠ ነው ያለውን የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 እንዲሰረዝ ጥያቄ አቀረበ፡፡

ፓርቲውን ይህን ጥያቄ በይፋ ያቀረበው ሐሙስ ነሐሴ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ‹‹አገር ለማፍረስ የተቀመጠው አንቀጽ 39 የወለደው ችግር የበርካታ ዜጎችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል፤›› በማለት፣ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ዋና ጽሕፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነው፡፡

ለ27 ዓመታት የተገነባው የጥላቻ ግንብ ዘርና ቋንቋን መሠረት በማድረግ የተመሠረተው የፌዴራሊዝም ሥርዓት፣ ውጤቱ እንደዚህ ሕዝብን በማጋጨት የአገርን ንብረት በማውደም ላይ ይገኛል ሲሉ መኢአድ ሥጋቱን ገልጿል፡፡

መኢአድ ይህን ያለው ሰሞኑን በጂግጂጋ ከተማ የደረሰውን ግጭት መሠረት አድረጎ ሲሆን፣ በአንቀጽ 39 ሳቢያ እንዲህ ያሉ የአገርን አንድነትና ክብር የሚነኩ ጉዳዮች እንደሚከሰቱ በማስጠንቀቅ፣ ላለፉት በርካታ ዓመታት ሥጋቱን ሲገልጽ መቆየቱንም አስታውቋል፡፡

‹‹ዛሬ ወደ ሶማሌ ክልል በመሄድ አገራቸውንና ወገናቸውን ሲያገለግሉ የነበሩ ዜጎች ሕገወጥ በሆኑ ግለሰቦች በዘራቸው የተነሳ ብቻ እንዲገደሉ ተፈርዶባቸዋል፣ ተሰደዋል፣ ተጠቅተዋል፣ ንብረታቸውም እንዲወድም ተደርጓል፡፡ ከዚህ በባሰ ሁኔታ ደግሞ ቤተ እምነቶች እንዲቃጠሉ ተደርጓል፤›› በማለት፣ የብሔር ፌዴራሊዚሙ ያመጣው ችግር ሳይባባስ መንግሥት አስፈላጊውን ዕርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል፡፡

‹‹አሁን በየቦታው እየተፈጸመ ያለው በዘር ላይ የተመሠረተ ግጭት ወደ ከፋ ደረጃ በመሸጋገር ላይ ስለሆነ፣ መንግሥት ሕገ መንግሥቱን መሠረት ያደረጉ ዕርምጃዎችን እንዲወስድ ድርጅታችን ይጠይቃል፤›› ብሏል፡፡

‹‹በዚህም መሠረት መንግሥት በአስቸኳይ በሕገ መንግሥቱ ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ አጥብቀን እንጠይቃለን፤›› ሲልም ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

‹‹የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ስንጠይቅ የአንቀጽ 39 ጉዳይ አንገብጋቢው ነው፡፡ ስለሆነም ከሕገ መንግሥቱ እንዲወጣ እንጠይቃለን፡፡ የምንጠይቅበት ዋነኛ ምክንያት ደግሞ አንቀጹ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭና ሕይወት እስከ ማጥፋት የደረሰና አገር ሊያፈርስ የሚችል አንቀጽ በመሆኑ ነው፡፡ አንቀጹ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ክብር አይመጥንም፣ አስፈላጊም አይደለም፤›› ሲሉ የመኢአድ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙሉጌታ አበበ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

መኢአድ ዜጎች በአገራቸው ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው የመሥራትና ሀብት ንብረት የማፍራት ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው እንዲጠበቅላቸው፣ መንግሥት ለዜጎች ጥበቃ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት ተረድቶ አደጋ ከመድረሱ በፊት ሕይወታቸውን ሊታደግ የሚችል ጥበቃ እንዲያደርግ መንግሥትን ጠይቋል፡፡

የፈረሱ ቤተ እምነቶች፣ የወደሙ የዜጎች አንጡራ ሀብትና ንብረቶች በአስቸኳይ ተጣርተው፣ በዚህ ኢሕገ መንግሥታዊ ድርጊት የተሳተፉ ባለሥልጣናትም ሆኑ ግለሰቦች ለፍርድ እንዲቀርቡ መንግሥትን አጥብቆ እንደሚጠይቅ መኢአድ አስታውቋል፡፡

1 Comment

Comments are closed.