የሕገ መንግስት ትርጉም በውል ሳይነገር ሀገሪቷ ለማይታወቅ ጊዜ መንግሰት አልባ እንደትሆንና ‘State of nature’ እንዲሰፍን ተድርጓል፡፡ ሂደቱም ፡-

የሕገ መንግስት ትርጉም በውል ሳይነገር ሀገሪቷ ለማይታወቅ ጊዜ መንግሰት አልባ እንደትሆንና ‘State of nature’ እንዲሰፍን ተድርጓል፡፡ ሂደቱም ፡-

1. ምንም አጀንዳውን ሳይናገሩ 24 ሰዓት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ታቃዋሚዎችን ለስብሰባ ተብሎ ተጠራ፣

2. ምርጫ ስለሚራዘምበት ሁኔታም አራት መፍትሔዎች ቀረበ፣

3 ከአራቱ መፍትሔዎች ህግ መንግስታዊ ትርጉም በፌዴሬሽን ም/ቤት የሚለው የተሻለ ይመስለኛል ተብሎ ጠቅላይ ሚንስትሩ አስቀድሞ ወስኖ የመጣውን ውሳኔ ተናግሮ ተቃዋሚዎችን አሰናበተ፣

4. የህዝብ ተወካዮች ም/ቤትም ጠሚ የወሰነውን ውሳኔ እንዲያፀድቅለት ስብሰባ አስጠራ፣

5. ም/ቤቱም ተሰብስቦ ለይስሙላ በመፍትሔዎቹ ላይ ተወያይ ተብሎ ቀድሞውኑ የተወሰነውን ውሳኔ (ለፌዴሬሽን ም/ቤት ለህገ መንግስት ትርጉም እንዲላክ) የሚለውን አፅድቆ እንዲለያይ ተደረገ፣

6. ጠቅላይ ሚንስተሩም በወቅታዊ ጉዳዮች መግለጫ አልና ብቅ አለ :: ከዛም ማስፈፈራሪያና ዛቻ አዘለ ንግግሮችን አደረገ :: በህገ መንግስት ትርጉም ዙሪያ እነ አሜሪካ ፣ እነ ፈረንሳይ የዳበረ ልምድ አሏዋቸው ፣ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ የሚፈጠረውን የስልጣን ክፍተትም በትርጉም መሙላት ይቻላል ብሎ የፌዴሬሽን ም/ቤትንም ውሳኔውን ከወዲው መፃፍ እንዲጀምር አመቻቸ

7. ማድበስበሱም ቀጥሎ የህገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ የባለሙያ አስተያየት ለመሰብሰብ አለና በጉዳዩ ላይ መሰማት የሚፈለጉ ሰዎች ድምፅ ብቻ እንዲሰማ አደረገ፡፡

8. የሕገ መንግስት አጣሪ ጉባኤውም ቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትሩ የወሰነውን ውሳኔ አስፍሮ የውሳኔ ሃሳብ ብሎ ለፌዴሬሽን ምክርቤት ላከ፣

9. የፌዴሬሽን ምክርቤትም የሕግ መንግስት ትርጉም በውል ሳያሳውቅ የጠቅላይ ሚስትሩን ሃሳብ ወረርሽኙ ሲጠፋ ከ9 ወር አስከ 1 አመት ምርጫ ማድረግ ብሎ አፅድቆ ተለያየ፡፡

~by Feyisa T. Gerbaba.