የሐብሊ ሊቀመንበር የመልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውን ድርጅታቸው አስታወቀ

የሐብሊ ሊቀመንበር የመልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውን ድርጅታቸው አስታወቀ

ሀረር  ሰኔ 7/10/2010 የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ/ሐብሊ/ (ena)— ሊቀመንበር የመልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውን ድርጅታቸው አስታወቀ፡፡

ሐብሊ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ   የድርጅቱ ሊቀመንበር ያቀረቡትን  የመልቀቂያ ጥያቄ በመርህ ደረጃ ችግር እንደሌለበት ነው ያመለከተው፡፡

የመልቀቂያውን ጉዳይ በመገምገም ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ሁኔታዎችን  በማመቻቸት በሂደት ተግባራዊ እንዲሆን አቅጣጫ መቀመጡን አስታውቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሐብሊ ማዕከላዊ ኮሚቴ  ሰኔ 2/ 2010ዓ.ም. በሐረር ከተማ  ነውጠኞች ቡድኖች ባላቸው በተፈጸመ   ጥቃት በሰው ላይ በደረሰው የአካል መቁሰልና የንብረት  ጉዳት በጽኑ አውግዟል፡፡

ድርጊቱ ሐብሊን እና ኦህዴድን የማይወከል የጸረ ሰላም ኃይሎች እንቅስቃሴ መሆኑን  ጠቅሶ  አጥፊዎችን በህግ መጠየቅ እንዳለባቸው ማዕከላዊ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

ሁከትን  እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ጥቂት ግለሰቦች ፍላጎታቸውን ለማራመድ ከጀመሩት ህገ ወጥ እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡም አሳስቧል


Wodaj Bahiru Southern TPLFites 

#አቶ_ሽፈራው_ሹጉጤ

የደቡብ ክልል ኦዲት ቢሮ ሃላፊ ፤ የደቡብ ክልል አቅም ግንባታ ቢሮ ሃላፊ፤ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ፤ የፌዴራል ህምህርት ሚኒስቴር፤ የኢህአዴግ ፅ/ቤት ሃላፊ ሆነው ሰርተዋል።

አሁን ደግሞ የግብርናና እንሰሳት ሀብት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።።

#አቶ_ሱራጅ_ፈጌሳ

የሳልጤ ዞን አስተዳደር፤ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፤ የመከላከያ ሚኒስቴር ሆነው ሰርተዋል።

አሁን ደግሞ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሆነው ተሹመዋል።

#አቶ_መለስ_ዓለሙ

የሀዲያ ዞን አስተዳደር፤ የደቡብ ክልል የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር፤ የደቡብ ክልል ንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ፤ የደቡብ ክልል የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ሃላፊ፤ የደቡብ ክልል ሲቪል ሰርቪስና ምክት ርዕስ መስተዳደር ሆነው ሰርተዋል።

አሁን ደግሞ የፌዴራል የማእድንና ኢነርጂ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

#አምባሳደር_ተሾመ_ቶጋ

በኬኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር፤ የፌዴራል ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር፤ የኢፍድሪ የተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ፤ በፈረንሳይ ባለሙሉ ስልጣን የኢትዮጵያ አምባሳደር፤ በአውሮፓ ህብረት ባለሙሉ ስልጣን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ሰርተዋል።

አሁን ደግሞ የመንግስት ልማት ድርጅት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

#ዶክተር_ሂሩት_ወልደማሪያም

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሌክቸረረ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምክትል ዲን፤ የፌዴራል ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሆነው ሰርተዋል።

አሁን ደግሞ – የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር

#ወ_ሮ_ሙፈሪያት_ካሚል

የሲልጤ ዞን ሴቶች ጉዳ ጽ/ቤት፤ የደቡብ ክልል የደኢህዴን አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ፤ የፌዴራል የሴቶች ጉዳይ ሚኒስቴር፤ የጠቅላይ ሚኒስቴር አማካሪ፤ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሆነው ሰርተዋል።

አሁን ደግሞ የተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ሆነው ተሹመዋል።