የሃይማኖት በdhaadhaa ገዳይ: ሰዉን በቢለዋ እንዲያርድ የምስክር ወረቀት የሚሰጥ ሥርዓት!!

ሰዉን በቢለዋ እንዲያርድ የምስክር ወረቀት የሚሰጥ ሥርዓት

የሃይማኖት በdhaadhaa ገዳይ የሆነውን ደግነት ወርቁን ከተጠያቂነት ለማስመለጥ ወይም የፍርድ ውሳኔውን ለማዛባት አንድ የብልፅግና ካድሬ ከታች የሚታየውን ፍፁም አደናጋሪ የሆነ የድጋፍ ደብዳቤ አሁን ለጥፎወል።

ደብዳቤው የተፃፈው በጋሙ ጎፋ ዞን ባለስልጣን ሲሆን የሃይማኖት ገዳይ የሆነው ደግነት ወርቁ ፍቱን የሆነ የኤድስ መድሃኒት የሰራ መሆኑንና ለዚህ ተግባሩም ድጋፍ እንዲደረግለት ይጠይቃል።

ተመልከቱ፣ ደግነት ወርቁ ከኤድስ ይፈውሳል የተባለውን መድሃኒት የቀመመው በ2009 አመተ ምህረት ነው። እውን ነፍሰገዳዩ ሰው ያን መድሃኒት ሰርቶ ከሆነ እስከዛሬ እንዴት ለአለም ሳይገለፅ ቆየ?

እና ዛሬስ ይህ ደብዳቤ ከዬት መጣ?

የዚህ ደብዳቤ አላማ፣ ደግነት “ተመራማሪ” ነው በማለት በፍትህ ላይ ለማላገጥ የተዘጋጀ አካል መኖሩን የሚጠቁም ይመስላል።

“ተመራማሪ” ተብዬውም ሰዉን በቢለዋ እንዲያርድ የምስክር ወረቀት የሰጠ ሥርዓትም በፍፁም ከተጠያቅነት አያመልጡም።


Update Haayimaanot Badhaadhaa!!

ANI Dubbii TANA Ammas Shakkiin irraa Qaba.
Barataan Kutaa 12ffaa ti. Qorataa Dhibee HIV ti.
Qoricha HIV argatuuf Osoo Deemuu Haayimaanot Badhaadhaa argatee Ajjeese.

Maqaan Isaa Dagginnat Fiqaaaduu jedhama Jedhan
Kanaatu Haayimaanot Badhaadhaa Galaafate.

Durumaahuu Maaltu Ablee Harkatti Isa Qabachiise Yoo Kan Virus Qoratu Tahe??
Hattuu Yoo tahe Magaalaa Finfinnee Kan guute isaan Mitii?
Laboratory Seenee Hanga Kutatti Seenee Ajjeesu Maaltu Godhe Yoo ergama biraa qabaate malee??
HIV Osoon taane Silaa Koronaan Qorachaa jira jedhee Wayya. Kun Nama Shakkisiisa.
Mobile Fi Computer Fudhachuuf jedhee Lubbuu Intalaa Galaafataa?
Sanumaahuu Haayimaanot Nama Mucaa kanaahuu Barsiisuu dandeessudha malee Nama Mucaan Kun Ajjeesun malee Miti.
Sababni Inni Kutaa 12 barata isiin MASTERS QABDI ,Qorattuudha (MSC).

Boonaa Abduu


This is the suspect, Degnet Werku, in his 20s, in the brutal murder of post graduate medical student Haimanot Bedhadha.

According to police he is apprehended in a joint operation between #AddisAbeba Police & #NISS.

The suspect, Degnet Werku, in his 20s, was arrested following a lead from a Bajaj driver who the suspect asked for help to cash a cheque he stole from his victim.


ወጣት ሀይማኖት በዳዳን የገደለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታ ልዩ ጤና ኮሌጅ የሁለተኛ ድግሪ ተማሪ የሆነችው ሀይማኖት በዳዳን የገደለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡፡ ወጣት ሀይማኖት ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ/ም በኮሌጁ አስተዳደር ህንፃ ላይ በሚገኘው የላቦራቶሪ ቤተ-ሙከራ ክፍል ለምርምር በገባችበት ሁኔታ መገደሏ በኮሚሽኑ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ ገልጿል፡፡
ግለሰቡ ወንጀሉን ፈፅሞ ቢሰወርም የሠው መግደል ወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ከኮሚሽኑ የወንጀል ክትትልና ኦፕሬሽን ዳይሬክቶሬት ጋር በመቀናጀት ባደረገው ክትትል ወንጀሉን በፈፀመ በአንድ ቀን ተኩል ጊዜ ውስጥ ተጠርጣውን መያዙን የሰው መግደል ምርመራ ዲቪዚዮን ኃላፊ ም/ኢ/ር መንግስቱ ታደሰ ገልፀዋል፡፡
ግለሰቡ የምርመር ስራ አለኝ በማለት በተለያዩ ቀናት ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የጤና ኮሌጅ ይመላለስ እንደነበር ገልጾ ሟችን ከዚህ ቀደም ፈፅሞ እንደማያውቃት ክፍሉ ውስጥ ብቻዋን መሆኗን በማረጋገጥ አስፈራርቶ ገንዘብና ንብረት ለመውሰድ ሲሞክር ግብግብ ተፈጥሮ ሟችን መግደሉን አስረድቷል፡፡

በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ባንክ ቤት መግባት እንደማይፈልግ በመግለጽ እና የባጃጅ አሽከርካሪ የሆነውን አቶ እንዳለማው ታረቀኝን በማግባባት በሟቿ ስም የተዘጋጀውን የአምስት ሺህ ብር ቼክ ኢንዶርስ በማድረግ ገንዘቡን አቃቂ ቃሊቲ አካባቢ ከሚገኘው አዋሽ ባንክ ካቻማ ቅርንጫፍ ወጪ አድርጎ መውሰዱን ም/ኢ/ር/ መንግስቱ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
የኮቪድ ወረርሽኝን ምክንያት በማድረግ በሆስፒታሉ ፍተሻው መላላቱ ግለሰቡ ቢላውን ይዞ እንዲገባ እንዳስቻለው እና በተለይ በሆስፒታሉ ለደህንነት ተብለው የተገጠሙ ካሜራዎች በአግባቡ የማይሰሩ መሆኑን ለወንጀሉ መፈፀም ምክንያት እንደሆኑ ከኃላፊው ገለፃ መረዳት ተችሏል፡፡

ለስራው ውጤታማነት ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የሟች ቤተሰቦች፣ የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት የድርሻቸውን በመወጣታቸው ግለሰቡን በአጭር ጊዜ መያዝ እንደተቻለ ም/ኢ/ር መንግስቱ ተናግረው ትብብር ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በከተማችን በተለያየ ጊዜ መሰል የነፍስ ግድያ ወንጀሎች ቢፈፀሙም ኮሚሽኑ ከህዝብ ጋር በመቀናጀት ባደረገው ብርቱ ክትትል ወንጀል ፈፃሚዎቹ መያዛቸውን በማስታወስ በወጣቷ ላይ የተፈፀመውን የግድያ ወንጀል በማጣራት በቀጣይ ውጤቱን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
(ምንጭ፡-የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን)


ፈቃድ የተሰጠው ገዳይ:የኦሮሞ ሰብአዊ ክብሩ ነፃነቱ ብቻ ነው።

በተኛችበት በአባቷ አንገቷን ተቀልታ የተገደለችው የ14 ዓመቷ ኢራናዊት ጉዳይ በሀገሪቱ ቁጣን ቀስቅሷል::
የህዝቡ ቁጣ በማየሉ አባቷ በቁጥጥር ስር ውሏል::

በርካታ ሴቶች በክብር ማስጠበቅ ሰበብ በገዛ ቤተሰባቸው በሚገደሉባት ኢራን አሁን አሁን ህዝቡ “በቃ” ማለት ጀምሯል:: የኢራን ፕሬዚዳንት ሐሰን ሮሃኒ ይህ በሀገሪቱ በልማድ የኖረ የክብር ግድያ ብሎ ነገር በሕግ ሊታገድ ይገባል ብለዋል:: እስከዚያው የአዳጊዋ ወጣት የሮሚና አሽራፊ እና በመላ ዓለም በእንዲህ ያለ ግፍ ህይወታቸውን ያጡ ሴቶች ደም ስለ ፍትሕ ይጮሃል::

በአመርካ ሚኒያ ፖሊስ እየሆነ ያለውን እያያችሁት ነው። ነጩ ጥቁሩን በመግደሉ የተቀሰቀሰው የሕዝብ ቁጣ ከዕለት ወደ ዕለት እያየለ መጥቷል ። እንቅስቃሴዎች ታግደዋል። የንብረት ቃጠሎና ውድመት እየደረሰ ነው። ከፕረዚዳንቱ ጀምሮ የነጩን ገዳይ ድርጊት በእጅጉ እየኮነኑ ነው።

የኦሮሚያ ግን የተለየ ነው። ገድለው ወይም እስገድለው ሲያበቁ በድንገት ሞተች ይሉናል። የእሬቻውን አሰቃቂ ድርጊት ያስታውሱናል። አረመነነታቸውን ደግመው ተደጋግመው ያረጋግጡልናል። እጅግ የሚያመው ደግሞ ይህንን አስከፊ ድርጊታቸውን ለመሸፈን የለመደባቸውን የበሬ ወለደ ወሬ መቀባበላቸው ነው። ሃይማኖት በdhaadhaaን ገዳይ ለመደበቅ እየሄዱበት ያለው ርቀት አሳፋሪ ነው። በእውነት የአንድ ሀገር ዜጎች ነን? ያስብላል። የሌሎቹ ዝምታም ድርጊቱን እንደመደገፍ ይቆጠራል። እነዚያ ሴት ሚኒስትሮች ከወደት ናቸው? ያ ሁሉ የሚዲያ ጋጋታና የአዞ እንባ ከወደት ነው ያለው?

በዉሸት ድራማ ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተጠለፉ ለተባሉት ልጃገረዶች አመቱን ሙሉ ስትጮሁ ለነበራችው የመንግስት አፈቀላጤዎች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ፣ ስለ ሴቶች መብት እንታገላለን የምትሉ ፌምኒስቶች ፣ አርቲስቶች እንዲሁም የኢትዮጵያዊነት ጭንብል ያጠለቃችው ዘረኞች የዚህችን ሚስኪን እህታችን አሰቃቂ ሞት አልሰማችሁም?

አዎ አልሰማችውም። ለወደፊትም አትሰሙትም። የእናንተ ሥራ ያልተፃፈውን ማንበብ ነው። በገሃዱ አፍንጫችው ሥር እየተፈፀመ ያለው ሐቅ አይታያችውም። ለነገሩ የውሸት ድራማ እስክርፕት እየተለማመዳችው ሊሆን ይችላል። ጊዜያችውን ሐሰት በመፈበረክ ስለሚታጠፉ ለእውነት ቦታ ሊኖራችው አይችልም ። ለተንኮል የተፈጠረ ጭንቅላት ለሥራ ቦታ የለውም ይባል የለ?

ሰው በመግደል አስክሬን ለጅብ የወረወሩ ጅቦች የነገሱባት ሀገረ ኦሮሚያ እንደት ነሽ ብዬ ጥያቄ አላበዛብሽም። እንደት እየኖርሽ እንደሆነ ፣ በምን ሰቆቃ ውስጥ እንዳለሽ በዓይኔ በብረቱ እያየሁ አልጠይቅሽም። ባልና ምስት አንድ ላይ ሲገዱሉ፣ የልጆች አናት የሆነችውን ሴት ገበረ በገዛ ማሳዋ ውስጥ ከልጆቿ ፊት ጥይት አርከፍክፈውባት ሲገድሉ፤ባዶ እጁን ከቁጥጥራቸው ሥር ያሉትን ወጣቶች ከእሥር ቤት አስወጥተው ሲረሽኑ……ከፀሐይ በታች ያለ የጭካኔ ወንጀል ሁሉ ስፈፀምብሽ እየሰማሁ ውሎ አዳርሽን መጠየቅ አልሻም።

የኦሮሚያዬ ዝምታሽ ግን አልበዛም?

ልጆችሽ ከየዩኒቨርሲቲው ተለቅመው ሲታሰሩ፣ ሲሰወሩና ሲረሸኑ የያዘው ዝምታሽ ዛሬም ድረስ መኖሩ ለምንድነው? አመሪካ ላይ እየተካሄደ ያለው ተቃውሞ እኮ በሥሜ ጥቁርነት ነው። ያንቺ እኮ እያለቁ ያሉት የአብራክ ክፋይዎችሽ ናቸው። ከሟህፀንሽ የወጡ እንቦቀቅላዎች በየመንገዱ ሲወድቁ እንደት አስቻለሽ? የልጆችሽ ደም ከየጥሻው ይጮሃል። የፍልቅልቋና ብርቱዋ ሃይማኖት በdhaadhaa ደም ከፊንፊኔ ይጣራል።

ሀገረ ኦሮሚያ ይህንን ግን ልብ ብለሻል? በዚህ ምድር ላይ ከቅኝ ገዥዋ ሀገር ጋር ሀገር የመሠረተች ኦሮሚያ ብቻ ናት። የቅኝ ገዥዋን ሐውልት አንጋጣ እየተመለከተች “ስለ ተቆረጡ ጡቶትሽ፤ ስለ ተቆረጡ እጅችሽ እንደ ጎርፍ ስለፈሰሰው ደምሽ አታውሪ” የተባለች አገር ኦሮሚያ ብቻ ናት። እምብርቷ የሆነችን ፊንፊኔን ስም ቀይረው ሲጠሩ ያለ አንዳች ጥያቄ አቤት ያለች ኦሮሚያ ብቻ ናት። ልጆቿ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሲነጋገሩ ከውጭ የመጡባት እንግዶች የሚገላምጡባት አገር እናት አገሬ ኦሮሚያ ብቻ ናት። የለም እናት አገሬ ልጆችሽ በአውሬ እየተበሉብሽ ነው፤ ትዕግስት ይብቃሽ፤ ልጆችሽ እንዲሰሙ ሕመምሽን አሰሚ እንጂ።

ሆነም ቀረ ግን

በመላው ኦሮምያ የተቀነባበረ ግድያ ከተጀመረ ሰንበተበት ብሏል። ያሁኑ ጭራሽ ከእስር ቤት እያወጡ መረሸን ፣ሃገሪቱ አለኝ ከምትለው ትልቅ ሆስፒታል ውስጥ ጭምር ሳይቀር አሰቃቂ ግድያ እየተፈፀመ ይገኛል ።

ይሄ ባለበት ሁኔታ ሃገር ሰላም ነው ማለት የለየለት ቅዠት ነው። አሊያም ኦሮሞንና ኦሮሚያን አይመለከትም ማለት ነው። መንግስት ባለበት ሃገርና በሚያስተዳድረው ማረምያ ቤትና ሆስፒታል እየገባ እየገደለ ለአውሬ የሚሰጥ አረመኔ ማን ያሰማራው ገዳይ ነው? በተቃዋሚ ወይም አማፂ እንዳይላከክ በመንግስ ወታደርና ፌደራል ፖሊስ በሚጠብቀው የመንግስት ተቋም እንደልቡ እየገባ አረመኔያዊ ድርጊት ፈፃሚውና ከጀርባ እረጅም እጅ ያለው ማነው? ወይስ ፍቃድ ያለው ገዳይ ተቋቁሟል?

ገዳይም አስገዳይም መጨረሻው እንደ ኢህኣፓና መኤሶን ተባልቶ ማለቁ አይቀሬ ነው።

ለማንኛውም እራስን መከላከል ተፈጥሯዊ መብት ነው። አሁን መሬት ላይ ባለው ተጨባጭ ሁነታ እራስን መከላከል ፍቱን መፍትሔ አይሆንም። ዘላቂ መፍትሔ የሚሆነው መለያየትና መለያየት ብቻ ነው።

ይህን የምንለው በስሜት ተገፋፍተን አይደለም። አሁን ባለው ሁኔታ አይደለም አንድ ሀገር ጎረበት መሆን እንኳን አማራጭ በመጥፋቱ ነው።

እስኪ ልብ በሉና አስቡ።በምዕራቡ ዓለም ነጮች ጥቁሮችን በድለዋል፤ የዘር መድሎ አድርገዋል። እዚያው በምዕራቡ ዓለም ነጮች ለጥቁር መብትም አምፀው ታስረዋል። አብረው ነቅለው ሰልፍ ወጥተው ጮኸዋል። የነጭ ሚዲያዎችም ያለ አድሎ ኢቨንቶችን ዘግበዋል። በኢትዮጵያ ታሪክ ይህ ሆኖ ያውቃል? አማራ ድንገት ተሳስቶ ለመብታቸው ከሚያምፁ ሕዝቦች ጋር ተሰልፎ ታይቶ ያውቃል?

በፍፁም! በኛ ዕድሜ ታይቶ የምንጠቅሰው የለም። በቡድንም ሆነ በግለሰብ ሲሰለፍብን እንጂ ሲሰለፍልን አይተን አናውቅም። ከዚህ የምንረዳው መለያየቱ የተሻለ ምርጫ መሆኑን ነው። ምርጫ ብቻ ሳይሆን ዘላቂና ብቸኛው መፍትሔ መለያየትና መለያየት ብቻ ነው። ከሚመስሉን ጋር ሌላ ሀገር መመስርት። ያም ካልተሳካ የራስን ሀገር መመስረት። ፈቃድ ተሰጥቷቸው ከሚገድሉን አረመነዎች እስከወድያኛው መለያየት ።

የኦሮሞ ሰብአዊ ክብሩ ነፃነቱ ብቻ ነው።

አበቃው።

ቸር ሰንብቱልኝ።