የሀይማኖት ተቋማት ህገ-ወጥ በሆኑበት ሀገር ፣ የህግ የበላይነትን የሚያከብር ትውልድ ለመፍጠር ፣ ራዕይ ካለክ ? ወይ አንተ ወይ ህዝቡ ተሳስቷል።

የሀይማኖት ተቋማት ህገ-ወጥ በሆኑበት ሀገር ፣ የህግ የበላይነትን የሚያከብር ትውልድ ለመፍጠር ፣ ራዕይ ካለክ ? ወይ አንተ ወይ ህዝቡ ተሳስቷል።

ህገ-ወጥ ፣ ህገ-ወጥ ነው።

ነፍጠኞች ከጎንደርና ጎጃም ተደራጅተው በመምጣት በሃይማኖት ስም የኦሮሞን መሬት ለመውረር ግልፅ ጦርነት ውስጥ እየገቡ ነው!!


በአዲስ አበባ ለሊት በተቀሰቀሰዉ ግጭት የሰዉ ሕይወት ጠፍቶአል

በአዲስ አበባ ከተማ በፀጥታ አስከባሪ ፖሊሶች እና በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ነን በሚሊ ሰዎች መካከል በተከሰተ ግጭት ሁለት ሰዉ መሞቱ ተነገረ። የተጎዱም እንዳሉ እየተገለፀ ነዉ። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር ከስፍራዉ የዓይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበልን ግጭቱ የተቀሰቀሰዉ በአዲስ አባባ በተለምዶ 22 ወይም 24 አካባቢ በሚባለዉ ቦታ የሃይማኖቱ ተከታዮች ነን የሚሉ አካባቢዉ ላይ ቤተክርስትያን እንድናንጽ በህልም ታይቶናል ብለዉ አካባቢዉ ላይ አጥረዉ ቤተክርስትያን ለመስራት ዝግጅት ላይ በነበሩ ሰዎች እና በፖሊስ መካከል መሆኑን ነዉ። ቦታዉ ላይ አጥረዉ የሚኖሩትን ሰዎች ለማስነሳት የፊደራል ፖሊስ ኃይላት ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ተኩሰዋል አስለቃሽ ጢስ ተጠቅመዋል። ሰዎችን ለማንሳት ፖሊስ ተኩስ ሲያስነሳ፤ አካባቢዉ ላይ ሃይማኖታችን ተነካ የሚሉ አካላት ከፀጥታ አስከባሪ አካላት ጋር ግብግብ ማስነሳታቸዉን የዓይን እማኞችን ጠቅሶ የአዲስ አበባዉ የ«DW» ወኪል ጨምሮ ዘግቦአል። ተኩስ ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋት ድረስ ይሰማ እንደነበረና አካባቢዉ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች እጅግ ስጋት ላይ መዉደቃቸዉንና ልጆቻቸዉን ትምህርት ቤት መላክ ሁሉ እንዳልቻሉ እየተናገሩ ነዉ ተብሎአል። በግጭቱ አንድ የፖሊስ መኪና ተቃጥሎአልም ተብሎአል። «በመሬት ቅርምት » የሚከሰሱት እና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ነን የሚሉትን እነዚህን ወገኖች ፖሊስ ከስፍራዉ ለማስነሳት ለምን ለሊት ሰባት ሰዓትን መረጠ?» ሲሉ የአካባቢዉም ሆነ የከተማዋ ነዋሪዎች አጥብቀዉ እየጠየቁ ነዉ። በግጭቱ በርግጥ ሁለት ሰዎች መሞታቸዉን እና ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ከፖሊስ ማረጋገጫ ለማግኘት ያደረግነዉ ሙከራ እስካሁን አልተሳካም። ይሁንና ሙከራችንን እንደቀጥልን ነዉ።

ዘገባ፤ DW- ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር

DW Amharic


Nafxanyaa lafa Oromoo saamuuf ba’e malee mirgaa isaa falmachuuf ba’ee miti Finfinnee naannoo 24 fi 22 jedhamee beekamuutti . Lafa oromoo Takkalaa fi Abiyyi irra ishee haftee nafxanyaa maqaa bataskaana saamaa jira.

Fekadu Fayisa


በፊንፊኔ ከተማ 22 አካባቢ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር የ2 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰመ፡፡

የሰው ህይወት ያለፈው ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው ክፍት ቦታ ላይ ቤተክርስቲያን ለመስራት አከባባቢውን ባጠሩና በመንግስት ፀጥታ ሀይሎች መካከል በተፈጠረው ግጭት ነው ተብሏል፡፡

በግጭቱ የሁለት ሰዎች ህይወት ስያልፍ፤ ሌሎች ደግሞ ቆስሏል ነው የተባለው፡፡

የፊንፊኔ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ጉዳዩን በማስመልከት በፌስቡክ ገፃቸው በፃፉት መልእክት የከተማ አስተዳደሩ የሃይማኖት ተቋማት በተለይም ከይዞታ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ሲመልስ መቆየቱን ገልፀዋል።

ይሁን እንጅ በጥቂት አጥፊዎች ምክንያት ያልታሰበ ድርጊት ተፈፅሟል ነው ያሉት፡፡

ለችግሩ ምክኒያት የሆኑ አካላት ለህግ እንደሚቀርቡ ነው ምክትል ከንቲባው ያስታወቁት፡፡

ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአካባቢ ነዋሪዎች በበኩላቸው የተኩስ ድምፅ ሲሰማ እንደነበረ ነው የተናገሩት፡፡

ከመካከላቸው አንደኛው በስፍራው አዲስ የፈለቀ ፀበል መኖሩን እና እርሱን ተከትሎም ቤተ ክርስትያን ይሰራል ሲባል እንደሰማ ለቢቢሲ ተናግሯል።

መንግስት በበኩሉ በፊንፊኔና አካባቢዋ በሀይማኖት ስም የመሬት ወረራ ላይ የተሰማሩ አካላት እንዳሉ በተደጋጋሚ ስገልፅ ነበር፡፡

በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞንና ፊንፊኔ አካባቢ ታቦት ወርዷል በማለት መሬት የማጠር ሁኔታ በተደጋጋሚ ተስተውሏል፡፡

የኦሮሚያ ቤተክህነት መስራች ኮሚቴ ልቀመንበር ልቀአእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን በበኩላቸው በቤተክርስቲያኗ ስም የመሬት መቀራመት ላይ የተሰማሩ አካላት ቤተክርስቲያኗን እንደማይወክሉ ከዚህ በፊት ገልፀው ነበር፡፡


OMN: ዕለታዊ ዜና (FAB. 05, 2020)


OMN:ቆይታ ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ብርቲካን ሚደቅሳ ጋር
በቅርቡ ጠብቁን