ዛሬ ኢትዮጵያ ተብሎ የሚታወቀው ሃገር በእድሜ ከኦሮሚያ የሚበልጠው በ57 ዓመታት ብቻ ነው::

ዛሬ ኢትዮጵያ ተብሎ የሚታወቀው ሃገር በእድሜ ከኦሮሚያ የሚበልጠው በ57 ዓመታት ብቻ ነው።
ዛሬ ኢትዮጵያ በመባል የሚታወቀው ሃገር አሁን የምናውቀው ካርታው ተሰርቶ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦፊሴል ይፋ የሆነው ሚኒሊክ ከአንኮበር በመነሳት የኦሮሞን ሃገርና ሌላውን የደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች በወረራ ከያዘ ከ34 ዓመታ በኋላ እንደነበረ በታሪክ ይታወቃል። ይህ ማለት ሚኒሊክ እነዚህን አካባቢዎች ሁሉ በወራራ ይዞ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ስር ያስገባው በ1900 አካባቢ ነበር ብንል (ምንም እንኳን ከዛ በኋላ በጣም ቆይተው ወደ ግዛቱ የገቡ እንደ ኦጋዴንና ጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል ወዘተ ያሉ አካባቢዎች ቢኖሩም)፣ አሁን ኢትዮጵያ ሲባል ወደ አእምሮአችን የሚመጣው ካርታ የተሰራው በ1934 ዓ.ም አካባቢ ነበር ማለት ነው። ኦሮሚያ በኦሮሞ ልጆች ትግልና መስዋዕትነት በኦፊሴል ካርታ ላይ የተገለጸው በ1991 ነበር። በዚህ መሰረት ዛሬ ኢትዮጵያ ተብሎ የሚታወቀው ሃገር በእድሜ ከኦሮሚያ የሚበልጠው በ57 ዓመታት ብቻ ይሆናል ማለት ነው። ዛሬ ኦሮሚያ የሚባለው ሃገር በታሪክ አልነበረም ብሎ የሚናገር ሰው ዛሬ ኢትዮጵያ የሚባለው ሃገርም በእድሜ ከኦሮሚያ የሚበልጠው በ57 ዓመታት ብቻ ስለሆነ እሱም በታሪክ አልነበረም የሚለውንና ተመሳሳይ የክርክር ሎጅክ የተከተለውን ነጥብም መቀበል ይኖርበታል።

Girma Gutema

ሀሮምሳ ፊንፊኔ ማህበር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። ከሶስት ሺህ በላይ የፊንፊኔ ከተማ ነዋሪ ኦሮሞ በኦሮሞ ባህል ማዕከል በመታደም ሀሮምሳ ፊንፊኔ ማህበርን እውን አድርጓል
እናመሰግናለን ቄሮና ቀሬ ፊንፊኔ!!


ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ ጠዋት ከክቡር ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በመሆን ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሞ ስኳር ፋብሪካን ከመረቁ በሁዋላ በቅርቡ የጋሞ ሽማግሌዎች ለሰላም ምሳሌ በመሆን ሁላችንን በማስተማራቸው ምስጋና ለማቅረብ አርባምንጭ ከተማ ሲደርሱ የጋሞ ሽማግሌዎችና የከተማው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አደረጉላቸው::