“ውሾች ይጮሃሉ ፤ ግመሉም ይጓዛል”ኢትዮ 360 እና ኢሳት የሚባሉ የፅንፈኛ አህዳዉያን ሚዲያዎች

“ውሾች ይጮሃሉ ፤ ግመሉም ይጓዛል”

ኢትዮ 360 እና ኢሳት የሚባሉ የፅንፈኛ አህዳዉያን ሚዲያዎች የዎላይታን ክስተት አስታከው እንደለመዱት ሲዳማን ሲሳደቡ እና ሲያጠለሹ ውለዋል ።

የዎላይታን ህዝብ ጥያቄ ከዎላይታ ህዝብ ፍላጎትና ከሃገሪቱ ህገ-መንግስት አንፃር ብቻ ማየት እየተቻለ የህዝቡን ጥያቄ ከሲዳማ አንፃር እየተነተኑ ሲዳማን ማንቋሸሽ ፍፅሙ ጥላቻ ነው ።

በሲዳማ የክልል ጥያቄ ሂደት ወቅት እነዚህ የጨፍላቂ ፖለቲካ አራማጅ ሚዲያዎች ሲዳማ ክልል ከሆነ ሌሎች ብሄሮች ችግር ውስጥ እንደሚገቡና ሃዋሳ በቁሟ እንደምትዘረፍ ሲሰብኩ ነበር።

ከክልል ምስረታ በኻላ ያየነው ግን ፍፅሙ ተቃራኒ ነው። ሁሉም ህዝብ ተደስቶና ሰላም ተሰምቶት እየኖረና እየሰራ ነው። ከተማዋ ከመቼም ጊዜ በላይ ተረጋግታለች። የሃዋሳ ከተማ መስተዳድርም የከተማዉን ነዋሪ በማወያየት አሳታፊ የሆነ የልማት እቅድ በማውጣት ስራውን እየሰራ ነው። መሬት ላይ ያለው ሃቅ ይህ ሆኖ ሳለ Ethio 360 ዎች ዛሬም የሚያወሩት ሌላ ነገር ነው።

የሲዳማ ገበሬ እየተፈናቀለ እና ከአከባቢዉ በሚሰበሰብ ሃብት(ጫት፣ ቡና) የለማን ከተማ ልክ ከሌላ አከባቢ ሃብት ጎርፎ እንደለማና የሲዳማ ሚና ዜሮ እንደሆነ አድርገው ሲያወሩ መስማት ይገርማል። ከሲዳማ የሚሰበሰብ ሃብት ሃዋሳን የሚያካክሉ አስር ከተማዎች ሊገነባ እንደሚችል ማን በነገራቸው?

ሌላው የሲዳማ ህዝብ የክልል ጥያቄ በህዝቡ ያልተቋረጠ ትግል፣ መስዋትነት እና ፖለቲካዊ ጥበብ (ጊዜና ሁኔታ የፈጠረውን ዕድል ሳያባክኑ መጠቀም) ሆኖ ሳለ ዛሬም ሌሎች እንደሰጡን ማዉራት ሲዳማን አለማወቅና መናቅ ነው።

እነዚህ ሰዎች በሚነዙት ጥላቻ እንቆረቆረለታለን የሚሉትን ማህበረሰብ ማህበራዊ መስተጋብር እየጎዱ ነው። አንዳች ነገር ጠብ ለማያደርጉለት ወገኔ የሚሉት ማህበረሰብ መሬት ላይ ተሳስቦ እንዳይኖር ልዩነትን ሲሰብኩ ይውላሉ። ይህን የሚያደሩት ለማህበረሰቡ አስበው ሳይሆን ለፖለቲካ ቁማራቸው ሲሉ ነው።

ለማንኛውም ሲዳማ የናንተን የተደራጀ ስም የማጥፋት ዘመቻ ተቋቅሞ በማሸነፍ ክልል ሆኗል።

ውሾች ይጮሃሉ ፤ ግመሉም ይጓዛል እንዲሉ እናንተ ጩሁ፤ ህዝባችን ቀና ብሎ በክብር ይሄዳል።።

via:Dábessá Gemelal