ዋ ጨለንቆ !!!

ያ የግፍ ዘመን ሳያበቃ ተነግሮ
እኔሆ ጨለንቆ አነባች ዘንድሮ።
የአረጋዉያን ትንሳግ የህጻናት ዋይታ
ዛሬም ተደጌሜ ከጠዋት እስከ ማታ።
ጋራ ሸንተረሩን ወንዞችን ተሻግሮ
ኬመንደር የገባዉ በግ መሳይ ቀበሮ።
ደማችንን ስያፈስ ስጋችንን ስበላ
ስወረን አየነዉ ጂቦ ደቅ አሉላ።

ወይ አንድኔታችን ወይ የአብሮነት ኑሮ
መለዬት ተሳነን ዜንድሮን ከድሮ።
ሁሌም በአፈሙዝ ሁሌም በጠብ መንጃ
የእነሱስ አንድነት ሆነ መቀለጃ።
በአካል የዜሜኑ በመንፈስ ያረጁ
ቅሪቴ መሳፊንት ለምንም የማይበጁ።
በዚያ በወረሱት ቅሪት መንፈሳቸዉ
ሥጋ ወደሙ ነዉ ሁሌም ዉዳሴያቸዉ።

አንድዬዉ ፈጠረን መርጦ በአምሳሉ
ተገዢም አረገን ምንሰራ በቃሉ።
ብለዉ ስያበቁ ቆርበዉ በስሙ
ምነዉ ለደማችን ክፉኛ ተጠሙ ?
ጎርርፍ ያመጣዉ ሁሉ ከላይ የወረደ
ያ ዋልጌ ጠበኛ ወፍ ዘራሽ ወንበደ።
ደርሶ በመንደሬ ክብሬን የሚገፈኝ

የአባገዳዉን ልጅ እንዴት ሊያዋርደኝ ?

ጥይት ልቆጥሩልን ስንሰጥ አበባ
ሆኔ ወሮታችን የተባይ ሰለባ።
ዛሬስ እጅግ በዛ ገደቡን አለፌ
የአብረሃም በግ መሆን ለኛ ምን ተረፌ ?
ብርሌ ከኔቃ ዳግም ላይሆን እቃ
ተባያችን ይርገፍ ሁሉም በዚህ ይብቃ
አወን በዚሁ ይብቃ።

አህመድ አባቡልጉ