“ዋናው ላቭ ነው” የሚል የፖለቲካ ፓርቲ ይሁን የዴቲንግ ሳይት መሆኑን ያልለየ slogan ይዞ ብቅ ያለው ኢዜማ የልብ ምልክቱ በምርጫ ቦርድ ውድቅ ተደርጎበታል።

ዋናው ላቭ ነው” የሚል የፖለቲካ ፓርቲ ይሁን የዴቲንግ ሳይት መሆኑን ያልለየ slogan ይዞ ብቅ ያለው ኢዜማ የልብ ምልክቱ በምርጫ ቦርድ ውድቅ ተደርጎበታል።

የፓርቲው አመራሮች ያልፀደቀ ምልክት ለማስተዋወቅ ያን ያህል መድከማቸው ግን ፈገግ ያሰኛል። በሌላ በኩል የአብን አመራሮች #ጊዜው_አሁን_ነው የሚል የማህበራዊ ሚዲያ ቻሌንጅ ቢያስጀምሩም መፈክሩ ሁለት አስር ሰዎች ሳይጠቀሙበት የውሃ ሽታ ሆኗል። አብኖች የምርጫ ምልክታችን #ሰዓት ነው ብለው ለቦርዱ አስገብተዋል። ያንን በቀጥታ ቢናገሩ ደጋፊዎቻቸውንም ከግራ መጋባት ባዳኑ ነበር። ለትርጉም አሻሚ የሆነው መፈክር ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእይታ መሰወር ጋር ተገጣጥሞ አስበልቷቸው ነበር።
 
በዚህ አጋጣሚ ይህን ያደረገው አንድ የኦሮሞ ተቃዋሚ ፓርቲ ቢሆን ኖሮ ኦዴፓ የሆነ ቦታ ፈንጂ ወርውሮ ጉዳት ካደረሰ በኋላ የፓርቲውን ቀሪ አመራሮች በመንግስት ግልበጣ ጠርጥሬያቸዋለሁ ብሎ ሰብስቦ ያስር ነበር። ደግነቱ አብን ከጀርባው የሚከራከርለት አዴፓ ስላለ በዚህ ዙር የእሳት እራት ከመሆን ተርፈዋል። አዴፓ ሞቅ ሲል በአብን በኩል ሲቀዘቅዝ በራሱ አመራሮች በኩል የፖለቲካ ጫና ይፈጥራል። የገንቱዎች ስብስቡ ኦዲፒ ደግሞ ትናንት ከህወሃት ሎሌነት በትብብር ያላቀቁትን የኦሮሞ ብሄርተኞች ሰብስቦ አስሮና ገድሎ ብቻውን ለምርጫ ቀርቦ ለማሸነፍ ተዘጋጅቷል። “ትንሽ እንኳን አይሰቀጠጥህም” ነው ያለው ክበበው ገዳ?
 
በሌላ በኩል ጠሚው ባንድ ጊዜ ሁለት ዛፍ ላይ ወጥቶ ማጠፍያው አጥሮታል። መሰረቱ የኦሮሚያ ብልጥግና እይታው የአማራ ብልጥግና ሆኖ ተቸገረ። እንደሚታወቀው የይድረስ ይድረስ የተጠፈጠፈው ብልጥግና የጋራ ራእይም ሆነ ፍላጎት የሌላቸው ሰዎች ገብተው ገመድ የሚጓተቱበት ስብስብ ነው። አዴፓ ልወጣ አንድ ሃሙስ ነው የቀረኝ የሚል ማስፈራሪያ በሰፊው እያስነገረ ነው። ያደርጉታል አያደርጉትም ሌላ ጉዳይ ነው። አብይ የፓርቲው ሽኩቻ ቢበረታበት ወዳጅና ጠላቱን ለመለየት Bakafasque አጠፋፍ መርጧል። ሲመለስ ቅድመ ምርጫ ምንጠራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።
 
ለማንኛውም ሀገሪቱ ያለችበት ሁኔታ ለድብብቆሽና ለፖለቲካ ኢንትሪግ አያመችም። ወደፊት ወጣ ብሎ leadership ማሳየት ያስፈልጋል። ሱዳን ሰፊ መሬት በቁጥጥሯ ስር ካስገባች ሰንበትበት ብሏል።በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ ያልሰጠ የሱዳን ከፍተኛ ባለስልጣ የለም። በኛ በኩል ዲና ሙፍቲ የፕሮፓጋንዳ ስራውን ብቻህን ተወጣው የተባለ ይመስላል። ግብፅ ግድቡን በተመለከተ ተደጋጋሚ ፉከራ እያሰማች ነው። ዛሬ እንኳን የግብፅ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሹክሪ ግድቡን በተለመከተ በፓርላማ ንግግ ር አድርጓል። በቤኒሻንጉል ንፁሃን እየረገፉ ነው። በትግራይ ከፍተኛ ረሃብና ቀውስ ተከስቷል። ምእራብ ኦሮሚያ በማርሻል ህግ (martial law) እየተዳደረ ነው። በዚህ ላይ የምርጫ አመት ነው። ይህ ሁሉ ችግር ባለበት ጠሚው ለሳምንታት ሲጠፋ ሰዎችን ስለ ደህንነቱ speculate ወደ ማድረግ መሄዳቸው አይገርምም። ጠሚው መሰረቱ አሸዋ መሆኑን የተገነዘበው ደመቀም ለዘመናት ከምክትልነት ወደላይ ሲቋምጥለት የነበረውን ቦታ ጉባኤ የማይካሄድ ከሆነ በሌላ መንገድ በእጁ ለማስገባት ደፋ ቀና እያለ ነው በሚል ኦዲፒ አካባቢ ይታማል።
 
ጠሚው በጊዜ ፊቱን ቢያሳይ የፖለቲካ እስረኞችን ቢፈታና ሀገሪቱ ያለችበትን ቀውስ ከግምት ውስጥ ያስገባ አመራር ለመስጠት ቢሞክር ለራሱም ሆነ ለሀገር መልካም ይሆናል። ኢዜማና አብን ብቻ የሚንቧቸሩበት ምርጫ ምርጫ ሳይሆን ቀልድ መሆኑን ከተረዳን ሰንበትበት ብለናል። ቢያንስ በትግራይ በቤኒሻንጉልና በምእራብ በኦሮሚያ እየደረሰ ያለው ሰብአዊ ቀውስs ረሃብና እልቂት ለባካፋዊ ድብብቆሽ ጊዜ የሚሰጥ አይደለም። Come out of your bunker!