ወደ ቤተ መንግስት አቅንቶ ከነበሩት ወታደሮች 66ቱ ፍርዳቸውን አገኙ

ወደ ቤተ መንግስት አቅንቶ ከነበሩት ወታደሮች 66ቱ ፍርዳቸውን አገኙ
ከወራት በፊት ወደ ቤተ መንግስት አቅንቶ ከነበሩት ወታደሮች 66ቱ በወታደራዊ ፍርድ ቤት ፍርዳቸውን ማግኘታቸውን የመከላከያ ሰራዊት ገለጸ፡፡

(EBC)—የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ዘውዱ በላይ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ወደ ቤተ መንግስት የሚገባው በምርጫ ካርድ እንጂ በጠመንጃ አይደለም ብለዋል፡፡

በሌሎች ላይ ደግሞ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን ሜጀር ጀነራል ዘውዱ አስታውቀዋል።

ሰራዊቱ ድርጊቱን የኮነነ ሲሆን ፈጻሚዎቹም ተገቢውን ፍርድ ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

በተያያዘም የመከላከያ ሰራዊት መዋቅር ማሻሻያ ማድረጉም ተገልጿል፡፡

ከአሁን ቀደም 6 የነበረው የእዝ ብዛት ወደ 4 ተቀንሷል።

4ቱ እዞች የምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ሰሜን ናቸው።

የባህር ሀይልን የሚያደራጅ ኮሚቴና የልዩ ዘመቻ እዝ ተዋቅሯል።

ይህንንም መሰረት በማድረግ የአዳዲስ አመራር ምደባ ተካሂዷል፡፡

በሰለሞን ጸጋዬ

Ethiopian Broadcasting Corporation