ወቅታዊው ጥያቄ…

ወቅታዊው ጥያቄ…

የመጀመሪው የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት የነበረው አቶ ገብሩ አስራት “ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ” በሚል ርኢስ ባሳተመው መጽሃፉ ውስጥ፣ ወያኔ ከጦር ሙርከኞች ውስጥ መልምላ ኦህዴድን ከማቋቋሟ በፊት (እንደነ ኩማ ደመቅሳ ያሉቱኑ ሻቢያም በገፍ ማርካ መንገድ እያስቆፈረቻቸውን የነበሩትን ጨምሮ) በወቅቱ ከነበረው organic የኦሮሞ ፖለቲካ ቡድን OLF ጋር ለመስራት ያደረገችውን ጥረት በሰፊው አስፍሯል።
አቶ ገብሩ በመጽሃፉ ውስጥና ሌሎችም የህወሃት ጸሃፊያን ካስቀመጧቸው ወሳኝ ነጥቦች ውስጥ የሚከተሉትን በግርድፉ መጥቀስ ይቻላል፥
1- በክንፈ ገ/መድህን (በኋላ ወያኔ መንግስት ስቶን የደህንነት ሃላፊ የነበረ) የሚመራ ቡድን ወያኔ ወደ ኦነግ ‘ያብረን እንስራ’ መልክት እንደላከችና በወቅቱ የነበረው የኦነግ አመራር “ከሃበሻ ጋር አንሰራም” በሚል ግብዣውን ቅርጫት ውስጥ እንደጣሉት፤
2- በአውሮፓም ወያኔዎች Dr Kahsay Berhe የተባለውን የነሱ ሰው አሰማርተው “ዲሞክራት የሆነ የኦሮሞ ምሁር” እንዲፈልግ ቢያሰማሩትም ከዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በቀር ማግኘት አለመቻሉን ጽፏል። በነገራችን ላይ አውሮፓ እያለው ከዶ/ር ካህሳይ ጋር ባያሌው መወዳጀት ችዬ የነበረ ሲሆን፣ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ጠይቄው ገብሩ አስራት በመጽሃፉ ውስጥ ያስቀመጠው መጥብ ትክክል መሆኑን አረጋግጦልኛል። ዶ/ር ካህሳይም ሆነ ዶ/ር ነጋሶ በዚሁ ”የሽግግር ጊዜ” ነው በሞት የተለዩን። ለሁለቱም ነፍስ ይማር ብያለው….REST IN POWER!
********
የሆነው ሆኖ… ወቅታዊው ጥያቄ ግን ያሁኖቹ የኦሮምያና የትግራይ ህዝቦች ነጻነት ተፋላሚዎች (#OLA & #TDF) በሚሆን መንገድ ይተባበራሉ ወይስ ታሪክ ራሱን ይደግማል የሚል መሆን ያለበት ይመስለኛል።

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.