ኮርኔል አብይ ስለሸክላ ድስት እንድሁም በየቀኑ ስለጥቅሶቹ ሲያወራ እንደሞኝ ቆጥረነው መናቅ የለብንም፡፡

ኮርኔል አብይ ስለሸክላ ድስት እንድሁም በየቀኑ ስለጥቅሶቹ ሲያወራ እንደሞኝ ቆጥረነው መናቅ የለብንም፡፡ የተናቀ ያስረግዝ የለ ዓላማውን ማወቅ እሱን ለማሸነፍ ይረዳል፡፡
 
ዓላማው፦ አንድና አንድ ብቻ ነው፡፡ እናቱ የተነበየችለትን እሱም ሲያልመው የኖረውን 7ኛ ንጉስ ሆኖ አገርቷን ቢያንስ 20 ወይም 30 ዓመታት መግዛት!
ይህን ለማድረግ የማይፈነቅለው ድንጋይ፣ የማይሰዋው ነገር ፈጽሞ አይኖርም፡፡ አባቱን ስፖንሰር ባደረገው መጽሃፍ አበሻቅጧል፤ ለማን ከፖለቲካ ውጭ አድርጎት የቤት እስረኛ አድርጎታል፤ ለርሱ ስልጣን መያዝ ያበቁትን ቄሮዎች ገድሏል ወይም አስሯል፡፡ሚልዮኖች ለመማገድ አያቅማማም፡፡ ሌንጮ ባቲ 10 ሚልዮን ኦሮሞዎችን ከትግራይ ጋር ለማዋጋት መዘጋጀቱን ገልጾልን የለ ይህ ሁሉ ተቃውሞ እየደረሰበት እንዴት ዕቅዱን ሊያሳካ ይችላል? የተከፈተበትን ጦርነት ሁሉ አንድ ጦርነት አድርጎ ትርኪት በመፍጠር፡፡ እንዴት? የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ አለማቀፉ ማህበረሰብ የተከፈተበት ጦርነት በርሱ (የለውጥ አመራር) እና በህወሃት (የለውጡ ተግደርዳሪ) መካከል መሆኑን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ማስነገር፡፡ ለዝህም ህወሃት ወደዝህ ትርኪት እንድትገባ መቆስቆስ ዋንኛ ስራው ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል በኦሮሚያ የተነሳበት ህዝባዊ አመጽ “እንደማይጸና፣ እንደማይቆጠር” አድርጎ ማየት ይህን ህዝባዊ አመጽ የህወሃት ሴራ እንደሆነ ማስነገር፡፡ ለዝህ ነው በአገርቱ በማንኛውም ቦታ ላይ አንድ ነገር ኮሽ ካለ ህወሃት ናት የሚትባለው፡፡ ይህ ትርኪት ተቀባይነት እንዲያገኝ ሁሉም የመንግስት አመራር እና ተከፋይ ሚድያዎች አቅጣጫ ተበጅቶላቸዋል፡፡
 
ስለዝህ ጦርነቱን በሁለቱ ካምፖች በማድረግ እስከ ምርጫ መዝለቅ ዋንኛ ዓላማው ነው፡፡ ምርጫ ከተካሄደ በኃላ በሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ከህወሃት ጋር ይስማማል፡፡ ምርጫቸውን ያጸድቅላቸዋል፡፡ የሱንም ይቀበሉታል፡፡ እስረኞቹም ይፈታሉ፡፡ ነገር ግን….. እስከ ምርጫ ምን ሊከሰት ይችላል፡፡
አንድ፦ ህወኃት የሱን ጨዋታ ነቄ ካለችበት፤ ጨዋታው ይፈርሳል፡፡ ይህን ጨዋታ ለማፍረስ ህወኃት ባልተጠበቀ ሁኔታ ጦርነት ልታካሂድ ትችላለች፡፡ አሁን የታሰበው ኤርትርያ በላይ በኩል ስላለች ህወኃት ደፍራ ወረራ አታደርግም የሚል እሳቤ አለ (በነገራችን ላይ ኢሳያስ በህወኃት ጥላቻ የታወረ ስለሆነ ከአብይ ፍቃድ ካገኘ ከመውረር ወደኃላ አይልም)፡፡ ኮርኔል አብይም ጦርነት ውስጥ መግባትን አይጠላም፡፡ የአማራን ክልል ወደጦርነት ለማስገባት ብዙ ጥሮ አልተሳካለትም፡፡ ይህ ማለት ጦርነት ቢገጥም ያሸንፋል ማለት እንዳልሆነ ልብ ሊባል ይገባል፡፡ በመሳሪያም ሆነ በሰለጠነ የሰው ኃይል እና ልምድ ህወኃትን ማሸነፍ ይከብዳል፡፡
 
ሁለት፦የኦሮሞ ህዝብ ኮርኔል አብይን አንቅሮ ተፍቶታል፡፡ ነገር ግን አመራሩም በመታሰሩ እስከ አሁን ድረስ ወጥ የሆነ የተሳካ ትግል ማካሄድ ሳይችሉ ቀርትዋል፡፡ ይህም የሆነበት ሌላው ምክንያት የተሰማራው ወታደር ህዝባዊ አመጽ ማድረግን እጅግ ከባድ አድርጎታል፡፡ ይህ ትግል በቀላሉ የሚዳፈን ግን አይሆንም፡፡ ግዜውን ጠብቆ ይፈነዳል፡፡ ማቆሚያም አይኖረውም፡፡ ይህ የሚሆንበት ዋንኛ ምክንያት መንግስት እንድናምን እንደሚፈልገው ሳይሆን (የህወኃት ሴራ ሳይሆን) ትግሉ ህዝባዊ በመሆኑ ነው፡፡ ይህን የነቃ የኦሮሞ ህዝብ ማስተኛት አይቻልም! መሪም ያገኛል!
ሦስት፦ ሰዉ ተርቧል፤ ኢኮኖሚው አፈር ድሜ ግጧል፡፡ ሰዉ የሚበላውን ሲያጣ፣ ፍርሃቱ ይጠፋል፡፡ ፕርፌሰር መረራ እንደሚሉት መሪዎቹን ክርትፍ አድርጎ መብላት ይጀምራል፡፡ ወንጀሎች ይበራከታሉ፡፡ በቅርብም ችግሮች ይባባሳሉ፡፡ ልብ በሉ ብር በአሁኑ ሰዓት ከገበያ እየጠፋ ነው፡፡ ብዙ ገንዘብ እንዳይወጣ በማድረግ የወደቀውን ኢኮኖሚ ማሻሻል አይቻልም፡፡
 
አራት፦ ኮርኔል አብይ አንድ ያለው ወዳጅ የአማራው ኤሊት ነው፡፡ የአማራው ኤሊትም ለ42 ዓመታት ያጡትን ስልጣን በአብይ አማካይነት ስላገኙ ድጋፋቸውን እየሰጡት ይገኛል፡፡ በአሁን ሰዓት እሱን ማንሳት ጠላት ስለሚያበዛባቸው ከጀርባ ሆነው ይህን አድርግ ያንን አታድርግ እያሉት ይገኛል፡፡ ለዝህም ነው የሶማሊ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት ሙስጠፌ ከአብይ ይልቅ ከአማራው ኤሊት ጋር በአንድ ፖፖ ካልተጸዳዳሁ ሞቼ እገኛለሁ የሚሉት፡፡ የአማራው ኤሊትም የሚፈልጉት ከምርጫው በፊት ህገ መንግስቱ እንድሻሻል፣ ሽመልስ እንዲነሳ ካላደረገ ወይንም እርስ በርሳቸው በሴራ ፖለቲካቸው ከተጠላለፉ አብይ እርቃኑን ይቀራል፡፡ አልያም ኮርኔል አብይም የነሱን ጨዋታ ገብቶት ቀብራቸውን በግዜ ሊቆፍርላቸው ይችላል እባብ ለእባብ ይታያያል ካብ ለካብ አይደል የሚባለው
አምስት፦ አለማቀፉ ማህበረሰብ የኮርኔል አብይን ንጉስነት ይቀበለዋል ወይ? አለማቀፉ ማህበረሰብ ከባድ ሚዛን ፖለቲከኞች በታሰሩበት ከራስ ጋር የሚደረግን የጨረቃ ምርጫን ያጸድቃል ወይ? ሌላው ሊጠየቅ የሚገባው ጉዳይ ሶማሊያ 15 ሚልዮን ህዝብ ኖሯት የዓለም የጸጥታ ስጋት ከሆነች 115 ሚልዮን ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ ቢትፈርስ የሚኖረው ስጋት እና የአንድን የእናቱን ትንቢት ለማስፈፀም የሚተጋ ሰው ሀሳብ መደገፍ የሚያመጣው ትርፍ አስልተው ያልተጠበቀ እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ፡፡ ስለዝህ ኮርኔል አብይም ያስባል፣ ይመክራል፤ ሌላውም እንድሁ …… አሁን ያለው የልጅ ፖለቲካ አደጋው ከባድ ነው፡፡ አገሪቱ ልትፈርስ ትችላለች!
Source: