ኮሎኔል አቢይ የመጨረሻ ካርዱን – – -ኮሎኔል አቢይ ትልቅ እልክ ዉስጥ ገብቶአል!

ኮሎኔል አቢይ የመጨረሻ ካርዱን – – – .

ኮሎኔል አቢይ ትልቅ እልክ ዉስጥ ገብቶአል. “የሚሞተዉ ይሞትታል እንጂ” የሚሉት መፈክሮች እልክ የወለዳቸዉ ናቸዉ. ይህ ነዉ የመጨረሻ ካርዱን ያስመዘዘዉ. ዳር ዳሩን ከኦሮሞና ከትግራይ እሊት ጋር ይምሰል እንጂ እልኩ ከሁሉም ጋር ነዉ. ከዚህ ከገባበትና እልክ ከወለደዉ ቀዉስ ለመዉጣት የሚወስዳቸዉ መፍትሄዎች መፍትሄ ከመሆን ይልቅ ቅራኔዎቹን የሚያሰፉ እየሆኑ ነዉ.
“እንትን የገባ እባብ ሆነ ከለቀቁት ይገባል ከሳቡት ይበጠሳል”. ይህን ያሉት ኦቦ ሃይለማሪያም ጋማዳ ከመጫና ቱላም ድርጅት መስራቾች አንዱ ናቸዉ ይባላል-አባባሉ ኮሎኔል አቢይ የገባበትንና ከቀዉሱ ለመዉጣት የሚያደርገዉን ዲራማ በደምብ ይገልጻል.

ሰሞኑን ለክፉ ቀን ያስቀመጣትን እያወጣ ነዉ. “ኦነግ ከወያኔ ጋር ተባብሮ እየሰራ ነዉ” የሚል. በፊት መፈክሩ ኦነግ ሁለት ቦታ ቆሞአላ የሚል ነበር.”ወያን በኦነግ እርዳታ ወደ ስልጣን እየመጣ ነዉ” የሚለዉ በሰፊዉ እየተወራ ነዉ. ይህ ለያንዳንዱ ካድሬ የተሰጠ የቤት ስራ ነዉ. ሰሞኑን ሺመልስ አብዲሳ የተናገርዉ ነገር ማስታወሱ ይበቃል. “ወያነ ኦሮሞን እንደ ፈረስ ተጠቅሞ ባይመጣ ኖሮ አይጫወትብንም ነበር” ይላል ሺመልስ. ልክ ነዉ ኦፒዲኦ መንገድ ባይመራ ኖሮ ወያነ አይጫወትብንም ነበር. ቀጥሎ “ዛሬ ወያነ ኦነግን እንደ ፈረስ ተጠቅሞ ሊመጣ ነዉ” ይላል.ወያኔ በኦፒዲኦ ጀርባ ተንጠልጥሎ ኦሮሞን ማሰቃየቱ ሁሉም የሚያዉቀዉ ነዉ. ሺመልስ ራሱ ከተላላኪዎቹ አንዱ ነበር. ይህን እየካደ እንዴት በሌላዉ እንመነዉ? አዲስና ማስረጃ ያላቀረበው ግን ኦነግ እንዴት የወያነ ፈረስ እንደሆነ ነዉ. ኦነግ ከወያነ ጋር ምንም ንክክ እንደሌለዉና ወያኔ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የፈጽመዉ ወንጀል የማይረሳ መሆኑን ኦነግ ደጋግሞ ገልጾአል.”አያ ጅቦ ሳታመሃኝ ብላኝ” የተባለዉ መሆኑ ነዉ. ለጊዜዉ ነጥብ የሚያስገኝ መስሎአቸዉ ነዉ እንጂ ኦነግ ለኦሮሞ ህዝብ በስተቀር ለማንም እንደማይንበረከክ ጠንቅቀዉ ያዉቃሉ. ኦነግ ከኦፒዲኦ ጋር ያለዉ ዋናዉ ቅራኔም ከዚህ ይመነጫል. ኮሎኔል አቢይ ከዚህ አይነቱ ዉሸት ራሱንና ካድሬዎቹን ነጻ አድርጎ መፍታት እንኩዋን ባይችል ቅራኔዎቹ ማጣበብ መሞከሩ ይሻለዋል.

የፖለቲካ እሊቶች እስር ቤት ማጎር መፍትሄ አይሆንም.የመጀመሪያ እርምጃ ማሰርና መግደል ማቆም፣ የፖለቶካ እስረኞችን ሁሉ መፍታት መሆኑን ራሱ ያዉቃ፣ ግን ይህን ማድረግ ይፈራል. እርግጥ መፍታቱ ብቻዉን መፍትሄ አይሆንም. ለምሳሌ የኦሮሞ ጥያቄ የፖለቲካ እስረኞችን ቢፈታም መልስ አገኘ ማለት አይደለም.
የመፍትሄዉን ጉዞ ለመጀመር ከሁሉም በፊት ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች መፍታት ከዚያ ሁሉንም ያካተተ በኮሎኔል አቢይ የማይመራ ዉይይት ማካሄድ ነዉ. ግልጽ ይሁን፣ ኮሎኔል አቢይ ተሳታፊ እንጂ የዉይይቱ መሪ ሊሆን አይገባዉም. በሌላዉ የታመን አወያይ ያስፈልጋል.
ይህ የመጀመሪያዉ እርምጃ ነዉ.

Mekbib Gebeyehu


በመላዉ ኦሮሚያ የተጠራዉ የትራንስፖርት ማዕቀብ እና ከከተማ ከተማ የሚደርግ የትራንስፖርት አገልግሎት ለ 4ኛ ቀን ቀጥሎ ዉሏል::
KMN:- Aug. 05/2020

በመላዉ ኦሮሚያ የተጠራዉ የትራንስፖርት ማዕቀብ እና ከከተማ ከተማ የሚደርግ የትራንስፖርት አገልግሎት ለ 4ኛ ቀን ቀጥሎ ዉሏል:: በቄሮ የተጠራዉ የትራንስፖርት ዕቀባ እና በተመረጡ ድርጅቶች ላይ እየተተገበር ያለዉ የትግል ስልት ከሀገር አልፎ ጎረቤት ሀገራቶችን እንዳስጨንቀ ለአራተኛ ቀን ቀጥሏል::

በዚህ የትራንስፖርት መዘጋት እና የእንቅስቃሴ መገታት ሳቢያ ከኢትዮጵያ ወደ ሲማሌ ላንድ እና ጅቡቱ ሲገቡ የነበሩት እንደ ጫት,ሽንኩርት እና የጥራጥሬ እህሎች ወደዚያ መግባት ስላቆሙ ከፍተኛ የዋጋ ንረት እና የአቅርቦት እጥረት ማጋጠሙን አረጋግጠናል:: ከዚህም ጋር ተያይዞ ከጅቡቱ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ኮንቴነሮች እና የደርቅ ጭነት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች በኢትዮጵያና ጅቡቱ ድንበር አካባቢ በረጃጅም ስልፍ ቆመዉ እንዳሉ ከአከባቢዉ የሚመጡ መርጃዎች ያሳያሉ::

በሀገር ዉስጥ በተለይም በዋና ከተማዋ እንደ ትላንቱ ሁሉ የአትክልት, የጫት እና የእህል ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ማሳየቱ ተመልክቷል::

KMN Kush Media Network


ተወዳጁ የአፋን ኦሮሞ ሙዝቃ አቀንቃኝ አርቲስት ጃፋር ዩሱፍ ነኃሴ 04/2020 በአዳማ ከተማ መተሰሩን የአዳማ ከተማ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል::
KMN:- Aug. 06/2020

ተወዳጁ የአፋን ኦሮሞ ሙዝቃ አቀንቃኝ አርቲስት ጃፋር ዩሱፍ ከትላንት በስትያ ማለትም ነኃሴ 04/2020 በአዳማ ከተማ መተሰሩን የአዳማ ከተማ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል::

አርቲስት ጃፋር ዩሱፍ በአፋን ኦሮሞ በሚያቀንቅናቸዉ ተወዳጅ የትግል ዜማዎቹ የሚታወቅ ሲሆን በማስተር ፕላን ተቃዉሞ ግዜ ከተዜሙ ማስተር ፕላኑን ተቃዉመዉ ከተዜሙ ዜማዎች መሃል የሱ የመጀመሪያው ዜማ ሲሆን ከዛን ወዲህ ባዜማቸዉ ዜማዎቹ ለኦሮሞ ህዝብን ትግል በማነቃቃት የአንበሳዉን ድርሻ ይዛል::

አርትስት ጃፋር ዩሱፍ የመጀመሪያዉን ኢህአዲግ ለመታገል እስከ ትጥቅ ትግል የሚደርስ ትግልን የተከተለ ቆራጥ ታጋይ ሲሆን በተለያዩ ጎረቤት ሀገሮች ሆኖ የትግል ዜማዎችን ሲያቀነቅን ቆይቶ በ2018 ለዉጥ ወደ ሀገር የገባ ተወዳጅ ታጋይ አርቲስት ነዉ::

ጃፋር ሀገር ቤት ከገባ ቦኃላም መንግስት በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚያደርሰዉን በደል የሚቃወም ዜማ እና የመንግስትን አቋም የሚተች የትግል ዘፍኖችን በማቀንቀን ለህዝብ የወገነ ታጋይ አርቲስት ነዉ:: ጃፋር ያለ ምንም ጥፋት በአዳማ ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩ ነዉ የተገለፀዉ::

KMN Kush Media Network


Ittiiqaa Tafarii: Itti Muddi Oromo Music 2016 New  By RAYA Studio