ኮሎኔል አቢይ በኦሮሚያ ዉስጥ በሚያካሄደዉ ፖእቲካ የሚጎዳዉ ኦሮሞ ብቻ አይደለም!

ኮሎኔል አቢይ በኦሮሚያ ዉስጥ በሚያካሄደዉ ፖእቲካ የሚጎዳዉ ኦሮሞ ብቻ አይደለም!

በኦሮሚያ ዉስጥ የሰላም እጥረቱ ሁኔታ እየተባባሰ ነዉ. ባለፉት ሳምንታት ባንዳንድ ከተማዎች የፈሰሰዉን ደምና የወደመዉን ንብረት እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል. ሌላ መጥቀስ የሚቻለዉ መጠኑ ሊየያይ ቢችልም የፈሰሰዉ ደምም ሆነ የወደመዉ ንብረት ባንድ ብሄር ላይ ያተኮረ አለመሆኑን ነዉ. ነገሩ መንግስትና አንዳንድ ሃላፊነት የማይሰማቸዉ መዲያዎች ሊያሳምኑን እንደሚሞክሩት ድርጊቱን የፈጸሙት ኦርሞዎች ብቻ አይደሉም. ኦሮሞ አልሞተም ንብረቱ አልወደመም ማለት አይደለም. ጉዳዩ አንድ ቀን ግልጽ ይሆናል

ወደ አስር ሚሊዮን አማራ ኦርሚያ ዉስጥ እንደሚኖር ስታቲስቲክ ይናገራል. በዚያ ላይ ኦርሞም አማራም ያልሆኑ ሌሎች አሉ. እነዚህ ህዝቦች የኦሮሞን ደስታም ሆነ ሃዘንም የሚጋሩ ናቸዉ. ኦሮሞ ነፍጠኛ ሲል ስርአቱን ነዉ.
የኦሮሞ ህዝብ ትግል ማንንም በመጉዳት ላይ ያነጣጠረ እንዳልሆነ ተደጋግሞ ተነግሮአል. ይህ ግልጽ ሆኖ እያለ ኮሎኔል አቢይ ህዝብን ክህዝብ እያጋጩ ነዉ በሚል የኦሮሞን ፖለቲካ መሪዎችንና የመብት ታጋዮችን አንድ ባንድ ወደ እስር ቤት አያገዘ ነዉ. ኦሮሞ ይህን ዝም ብሎ አይመለክትም. በሚችለዉ ሁሉ ይከላከላላ. በዚህ ዉስጥ ለሚደርሰዉ አደጋ ተጠያቂዉ መንግስት ነዉ. ግራህን ሲመታህ ቀኝህን ስጠዉ የሚለዉ ዘመን አልፎአል.

ኮሎኔል አቢይ ኦሮሞ ከሎሎች ጋር የማጋጨት ፖለቲካ ብቻ አይደለም እየሰራ ያለዉ. ኦሮም ራሱን በሃይማኖት፣ በአከባቢ በአድሜ ልዩነት ወዘተ. ለማለያየት ያላደረገዉና የማያደርገዉ ሙከራ የለም. ወለጋ ብሄድ ይገድሉኛል የሚለዉ የታሰበበት ኦሮሞን ከኦሮሞ ለማጣልላት ያደረገዉ ነበር. አልተሳአካም. ወደ ፊት ግልጽ የሚሆነዉ የአርቲስት ሃጫሉ ሞትና ከሱ ጋር ተያይዞ እጅን ወደ አንድ አከባቢ መጠቆምም ከዚሁ ጋር የተያያዝ ነዉ. ብዙ ማለት ይቻላል.

መልእክቴ፡ አማሮችና ሌሎችም በኦሮሚያ ዉስጥ የምትኖሩ ሁሉ አትጠራጠሩ. ኦሮሞ ከናንት ጋር ጥል የለዉም. ለሰላማችሁ ግን የሚሰጠዉ ዋስትና የለዉም. ለራሱም ሰላም ዋስትና የለዉምና.
ያለዉ አማራጭ በኦሮሞ ላይ የሚደርሰዉን በደል እኩል ተቁውቁሞ የሁሉም እኩልነት የተከበረባትና ሰላም የሰፈረባት ሃገር መመስረት ነዉ.

ኦሮሞ እየታሰረ እየሞተ ሌላዉ በሰላም ሰርቶ በሰላም ነግዶ መኖር አይችልም. ኦሮሞና በኦሮሚያ ዉስጥ ያሉት ህዝቦች ባንድ መርከብ የተሳፈራችሁ ናችሁ. ከዳር ሆነዉ ከሚጮሁት ይልቅ አብራችሁ ያላችሁት ኦሮሞ ነዉ የሚደርስላችሁ.

Mekbib Gebeyehu

Atis beekta anis beska – – – – አንተም ታውቃለህ እኔም አዉቃለሁ – –

ሰውዬዉ በሬው ጠፍቶበት “አምላኬ በሬዬን ብታገኝልኝ ፊየል አርድልሃለሁ” ብሎ ላምላኩ ይሳላል. በሬዉ ይገኛል፣ የፊየል መግጃ ገንዘብ ግን አልነበረዉም. በመጨረሻ የጎረቤቱን ፊየል ሰርቆ ያርድና “አንተም ታዉቃለህ እኔም አዉቃለሁ ስለቴን ተቀበለኝ” አለ ይባላል.

ኮሎኔል አቢይ ትናንት ከተፎካካሪ ፖአርቲዎች ጋር ያደረገዉን “ዉይይት” ሳዳምጥ ይህ ትዝ አለኝ. ኮሎኔል አቢይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወዴት እያመራ እንደሆነ ያውቃል. እንደ ገበሬዉ ግን ሃቁን አያምንም. ይህን አለማመኑና መቀየር አለሞሞከሩ የሚያመጣዉ አደጋ ትልቅ መሆኑም ይገባዋል. ከፍራቻና ለስልጣን ካለዉ ጥም የተንሳ መቀየር ከብዶታል.
የተፎካካሪ ፓርቲዎች ተወካይ ንግግር ደግሞ የንጉሱን ዘመን አስታዉሶኛል. “ለሚወድዎትና ለሚወዱት ህዝብዎ ይህንን ያድርጉ” የሚል ነበር ለንጉሱ የሚቀርበዉ አበቱታ. ትናንት ለኮሎኔል አቢይ የቀረበ ጥያቄ ከዚህ ብዙ የተለየ አልነበረም. የምስጋና ጋጋታዉም ለንጉሱ ይቀርብ ከነበረዉ አያንሱም.ያንድም ተፎካካሪ ጠንካራ ድምጽ አልሰማሁም፣ በራሳቸዉ ላይ የሚተማመኑ መሪዎች በቦታዉ አልነበሩም. ያሳዝናል!! የዚህ አይነቱ ስብስብ ለኮሎኔሉ የልብ ልብ ሰጥቶታል

ሌላዉ የሰማሁት ያንኑ የተለመደ ፍርሃት ያዘለ ዉሸት ነዉ. “ኦነግ አቢይ ላይ የግድያ ሙከራ አደረገ” የተባለዉ ሁለት አመት አለፈዉ. የታሰሩ ሰዎች እንዳሉ እንሰማለን. በጥርርጣሬ እንድንኖር ስለሚፈልጉ የሰጡት ፍርድ የለም. ያዉ ድራማ በየጊዜዉ መልኩን ቀይሮ ይመላለሳል. ወለጋ ብሄድ ይገድሉኛል የሚለዉ ከዚያ የቀጠለ ድራማ ነበር. ትናንት ደግሞ ኦነግ ፊንፊነ ዉስጥ ገዳይ አቁዋቁሞ ሊያስገድለኝ ነዉ የሚል ዜና አሰማን. የዚህ ሁሉ ድራማ ትልቁን ለኦሮሞን ጥቅም ያስጠብቃል የተባለዉንና ብዙ ድጋፍ ያለዉን ድርጅት ጥላሸት ለመቅባት፣ በሌሎች አከባቢ ጭራቅ አድርጎ ለማቅረብ ነዉ. ይህ ኦሮሞ ፎቢያ ባላቸዉ ድጋፍ እንደሚያሰጠዉ ያውቃል. ኮሎኔል አቢይ ይህንን የጀመረው ዛሬ አይደለም. ለወያኔ ሲያገለግልም ይህንኑ ነበር የሚያደርገዉ፣ ቦምብ አፈንድተዉ በኦንግ ማላከክ፣ ከዚያ በአሸባሪነት መፈርጅ!

ትናንት ከተናገረዉ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ.”እኔ በፍትህ ሂደት ዉስሽ ጣልቃ አልገባም፣ እገለ ይታሰር እገለን ፍቱልኝ አልልም” ይላል ኮሎኔል አቢይ. ይህ ነጭ ዉሸት ነዉ. ኮሎኔል ጋማቹ አያና (የድሮ ጉዋደኛዉ) የፍርድ ቀጠሮ ተይዞለት እያለ ቤተመንግስት አስጠርቶ ይቅርታ ጠይቆት አስፈትቶታል. ይህን ኮሎኔል ገመቹ በሰፊዉ ገልጾታል. አሁን ግን መልሶ አስሮታል. ለትግራይ ጋር ሰላም ለመፍጠር በሚል ብዙ የትግራይ ተወላጆች ከእስር እንዲፈቱ አድርጎአል፣
ዛሬ በፍትህ ሂደቱ ዉስሽ እጄን አላስገባም ቢል የሚያምነዉ የለም. የኔም አቁዋም እጅህን አታስገባ ነዉ. በፍትህ አካሄዱ ላይ ወሳኝ ዉሳኔ እየሰጡ የለሁበትም ማለት ግን ለትዝብት ይዳርጋል.
ለመሆኑ የወለጋ ህዝብም ሆነ ኦንግ እሱን ለማስገደል ያደረጉት ሙከራ በፍርድ ቤት ሳይረጋገጥ በዚህ ከባድ ወንጀል መወንጀሉ በህግ ዓያስቀጣም? ኮሎኔሉ ይህን ያዉቃል?ይህስ ካንድ የሃገር መሪ የሚጠበቅ ነዉ?


Dubbiin kuni – – . ይህ ነገር ድንጋይ

”Dubbin kuni dhagaa taha dhagaa kana qottoon falaxu hinjiru”. ይህ ነገር ድንጋይ ይሆናል ድንጋዩን የሚፈልጥ መጥረቢያ የለም ይላል አንድ የኦሮሞ አባባል. ትምህርት ሰጪ ጥቅስ ነዉ. ችግሮች በጊዜ ካልተፈቱ ለመፍታት የማይቻልበት ሁኔታ ይደርሳሉ. ይህንን አባባል በኦነግና በኦፒዲኦ መከከል ችግሮች ሲፈጠሩ አዝማሚያዉ ታይቶኝ ጠቅሼ ነበር. “ትጥቅ ፍቱ” የሚለዉ የነ አዲሱ አረጋ “የሚፈታም የሚያስፈታም የለም” የሚለዉን የኦነግ መልስ አስከተል. በጊዘዉ ሁሉም በስምምነት እንጂ አንዱ አንዱን በማስገደድ አይሆንም የሚል ትርጉም ተሰጥቶታል. በዚህ ደረጃ የጀመረዉ ነዉ ዛሬ እዚህ የደረሰው.
ይህን በሚመለክት በተለያዩ አጋጣሚዎች ስለገለጽኩ/ ስልጻፍኩ መደጋገሙ አይታየኝም. ለማንኛዉም ይህ ነዉ ነገሮችን ድንጋይ ያደረገዉና ሰላማዊዉን የትግል መንግድ እየዘጋ ያለዉ.

ሰላማዊ የትግል መንገድ ሃሳብን ያለ ምንም ተጽእኖ የመግለጽን፣ በነጻ ተሰብስቦ የመወያየትን፣ የፖለቲካ መሪዎችን ያለ ምንም ፍርሃቻ መንቀስቀስን ያጠቃልላል. ይህ በሌልብት ቦታ ሰላማዊ ትግል ማካሄድ አይቻልም ማለት ነዉ.
የሰላማዊዉ መንገድ እየጠበበ ወይም እየጠፋ መምጣት ደግሞ ሰላማዊ ላልሆኑት የትግል መንገዶች በር ይከፍታል. አመጽ ያነሳሳል፣ አመጽ ደግሞ አመጽ ይወልዳል፣ መግስት ቁጥጥር ያጣል፣ እኮኖሚዉ ይንኮታኮታል፣ በሰዎች መካከል መተማመን ይጠፋል ወዘተ. ይህ ዛሬ በሃገራችን የምናየዉ ነዉ.

ህዝቦች ሰላም ስለሚፈልጉና ነገሮች በዚህ መቀጠል ስለማይችሉ መፍትሄ የግድ ያስፈልጋል.
ናፖሊዎን መሰለኝ “በሰላም ለመኖር ከፈልክ ራስህን ለጦርነት አዘጋጅ” ያለዉ. ይህን ሃቅ ለማረጋገጥ ብዙ መዞር አያስፈልግም፣ ኮሎኔል አቢይን በምሳሌነት ማየት ይቻላል. ”እነ ጌታቸዉ አሰፋን ለመያዝ የማንሞክረዉ ለትግራይ ህዝብ ክብር ስላለን ነዉ” ይላል. ትግራይ በሰላም እየኖረ ነዉ. ቢያንስ ጦርነት በክልሉ የለም. ሰሞኑን ደግሞ ለዶክተር ደብረጽዮን ያለዉንም ክብር እየገለጸ ነዉ. በሌላ በኩል በኦሮሚያ ጦርነት አዉጆ በየቀኑ ብዙ ሰዉ ይረግፋል. ያለምንም ፍርድ ብዙዎቹን እስር ቤት ያጉራል.የኦሮሞን ጥቅም ለማስጠበቅ የተደራጁ ድርጅቶችን ለማጥፋት ሌት ከቀን ይታገላል፣ ገንዘብ ያፈሳል. ይህ ደግሞ የሚያሳየዉ ለኦሮም ክብር እንደሌለዉ ነዉ.

ናፖሊዎን ትክክል ነዉ ማለት ነዉ. የሰላማዊዉ መንገድ እየተዘጋ ሲሄድና ኦሮሞ እንደሌሎቹ እንደ እነ ትግራይ በሰላም ለመኖር ከፈለገ ራሱን ለጦርነት ማዘጋጀት ይኖርበታል. ዝግጅቱ የራስን ክብር ለማስጠበቅ እንጂ የሌላዉን ክብር ለመቀነስ ተደርጎ መወሰድ የለበትም. የዚያን ጊዜ መከበርና መከባበር ይመጣል. የአቻዎች ጫወቻ ይሆናል.

Via: Mekbib Gebeyehu