ካድሬነት ዕዳ ነው! ታላቁ ካድሬ ኤርሚያስ ለገሰ(ወዲ በረከት) የጨለማውን ጉዞ ተያይዞታል።

ካድሬነት ዕዳ ነው: ታላቁ ካድሬ ኤርሚያስ ለገሰ(ወዲ በረከት) የጨለማውን ጉዞ ተያይዞታል። ካድሬነት ህሊና ቢስነት ነው ስንል በማስረጃነት ከምንጠቅሳቸው ሰዎች አንዱ ኤርሚያስ ለገሰ ነው።
 
ከወራት በፊት ኤርሚያስና ሌላኛው ካድሬ ሀብታሙ አያሌው የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ ለአፍሪካ የሚያሰጋ አይደፈሬ ጦር መሆኑን “እጃቸው ላይ በሚገኝ ማስረጃ” አጣቅሰው ነግረውን ነበር። አያይዘውም ለህወሓት ያደላ ፕሮፓጋንዳ በመስራት ተጠምደው ነበር። ያው ህወሓትን ወደ ጦርነት እንዲገባ ምኞት ስለነበራቸው። በእርግጥ በህወሓት ድንቁርና ምኞታቸው ሰምሯል።
 
አስቂኙ ነገር ጦርነቱ ከተጀመረ ከአንድ ሳምንት በኋላ(የህወሓት ከተከዜ ማዶ ማፈግፈጉን ተከትሎ) የኃይል ሚዛኑን በማየት የኢትዮጵያ ወዳጅ ሲሉት የነበረውን “ኢሱ” ጠላት ለማለት ትንሽ ሀፍረት እንኳ አልተሰማቸውም። ካድሬነት ከአዝማሪነትም የከፋ ውሻነት መሆኑን ለምንገነዘብ ሰዎች የነኤርሚያስን ባዶነት መናገር ከጀመርን ሰነባብተናል።
 
የህወሓት ጉዳይ ከዚህ በኋላ ለሽቀላ አጀንዳነት የማይበቃ መሆኑን የተረዳው ባለ ዲፖ ሆዱ ኤርሚያስ ዛሬ ደግሞ “ባለሳምንት” ያደረገው የአማራ ልዩ ኃይልን ነው። ከወራት በፊት የአማራ ልዩ ኃይል ለኤርሚያስ ትንኝ ነበር። ዛሬ ደግሞ የማይገፋ ተራራ ነው እያለን ነው። ያው ካድሬ ማለት ከአንገቱ በላይ ያለው የሰውነት ክፍሉ የጎደለ ፍጡር ማለት ነዋ!
በቀጣይ የእነኤርሚያስ ዋና የትንታኔ ማጠንጠኛ “ኢሱ” እና አማራ ናቸው።
 
ካድሬነትን በጣም ነው የምንፀየፈው
Via: Dan Dimension