ከ1000 ኪ/ሜ በላይ የባህር ጠረፍ፣ የተፈጥሮ ጸጋን ከታታሪና ንቁ ህዝብ ጋር የታደለን አገር ያቆረቆዘና ያደኸየ አምባገነን

ከ1000 ኪ/ሜ በላይ የባህር ጠረፍ፣ የተፈጥሮ ጸጋን ከታታሪና ንቁ ህዝብ ጋር የታደለን አገር ያቆረቆዘና ያደኸየ አምባገነን ስለ መልካም አስተዳደርና ልማት የሚለግሰው ምክር የለውም፤ ሊኖረውም አይችልም።
በተለይ በተለይ …
 
የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መርህ አንግቦ ለ30 አመታት ኢትዮጲያን የወጋው ኢሳይያስ አፈወርቂ፤
ነጻ አወጣሁ ካለ በኋላ የኢትዮጲያን አንጡራ ሀብት መዝረፍ ቀረብኝ ብሎ በድንበር ሰበብ ዳግም የጦርነት እሳት ጭሮ 120 ሺህ ኢትዮጲያዊያንን ያስጨረሰው ኢሳይያስ አፈወርቂ፤
 
ለኢትዮጲያዊያን የ100 አመታት የቤት ስራ ሰጥቼቻዋለሁ ብሎ የተዘባበተው ኢሳይያስ አፈወርቂ፤
ከሀዲጊዎች (አማራ) ጋር አብሮ መኖር አይደለም አብሮ መለመን አይታሰብም ሲል የተዛለፈው ኢሳይያስ አፈወርቂ
እንዴት ለኢትዮጲያና ለኢትዮጲያዊያን መልካም አስተያየትና ደግ ምክር ይኖረዋል ተብሎ ይታሰባል?
ግብዝን ሰው እባብ ሁለቴ ነከሰው እንደሚባለው ኢትዮጲያዊያን እያሉ ራሳቸውን የሚኮፍሱት ሁለቴ በኢሳይያስ መነከሳቸው ትምህርት ሊሆናቸው ሲገባ ጭራሽ ሱስ ሆነባቸው። ለ3ኛ ዙር ወጥመዱ ውስጥ ገብተውለታል፤ ያሁኑ መጥፊያቸው ይመስላል።
 
★★የግርጌ ማስታወሻ
ኢሳይያስ ለአማራ ህዝብ ያለውን ጥላቻና ንቀት ማወቅ የሚፈልግ ኤሌን ገብራይ በሚትባል ኤሪትራዊት የተጻፈ Eritrea : The Miracle Land መጽሀፍ ፈልጎ ያንብብ
 

‹‹ዐቢይ ችኩልና ስሜታዊ ነው፤ጦርነቱ አላለቀም›› ኢሳያስ አፈወርቂ | ETHIO FORUM