ከ ኦሮሞ ቄሮ የተላላፋ በነፍጠኛው የአብይ አህመድ ሥርዓት ላይ የሚደረግ ተቃውሞና የኢኮኖሚ እቀባ ጥሪ::

ከ ኦሮሞ ቄሮ የተላላፋ በነፍጠኛው የአብይ አህመድ ሥርዓት ላይ የሚደረግ ተቃውሞና የኢኮኖሚ እቀባ ጥሪ::
KMN :- July 24/2020

የአብይ አህመድ አስተዳዳር፣ በቃልና በተግባር የተደገፈ ጦርነትን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ከፍቷል:: ኦሮሞን መግደል፣ በጅምላ ማሰር፣ እና ማንገላታት በሰፊው ቀጥሏል:: ተወዳጁን አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን በመግደል ውድና የአይናችን ብሌን የሆነውን ልጃችንን ነጥቆናል:: የትግላችንን መሪዎች ያለ አግባብ በማሰር መሪ አልባ ሆነን እንድንቀር ለማድረግ በመሯሯጥ ላይም ይገኛል:: የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን በማስፈራራት፣ በአንዳንድ ቦታዎችም፣ ቢሮዎቻቸውን አላግባብ በመቀማት፣ ህዝባችን፣ ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅት እንዳይገነባ፣ የገነባቸውንም እንዳያጠናክር፣ ከፍተኛ የሆነ ጫና በማድረግ ላይ ይገኛል::
የኦሮሞ ህዝብ ልሳን የሆነውን OMNን በመዝጋት፣ የኦሮሞ ህዝብ ድምፅ እንዳይሰማ አድርጓል:: የተለያዩ የኦሮሞ ሚዲያዎችን ከሳተላይት ላይ እንዲወርዱ በማድረግና የኢንተርኔት መረብን በማቋረጥ፣ ሚዲያዎቻችንን በሙሉ ለማጥፋት በሰፊው እየሰራ ይገኛል::
ይህ አልበቃው ብሎ የመንግሥት መገናኛ ብዙኅን ሚዲያዎችንና ፀረ-ኦሮሞ የሆኑ የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም፣ ሕዝባችን ላይ መጠነ ሰፊ የሆነ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ በመስራት፣ የህዝባችንን ስም ለማጉደፍ እየሰራ ይገኛል::
የተለያዩ የኦሮሞ ጋዜጠኞችንና አክቲቪስቶችን ያለ አንዳች ጥፋት በማሰር ሕዝባችን ድምፁ በየትኛውም መልኩ እንዳይሰማ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት በማድረግም ላይ ይገኛል:: በሀገር ውስጥ የሚሰራው እኩይ ተግባራቱ ሳይበቃው፣ በውጭ ሀገር ሆነው ለሕዝባቸው የሚተጉ አክቲቪስቶችን፥ የማሕበራዊ ድረ-ገጽ አውድማቸው እንዲዘጋባቸው በማድረግ፣ የኦሮሞ ህዝብ ሙሉ በሙሉ፣ ድምፁ፣ በውጭም በውስጥም እንዲታፈን ለማድረግ እየተጋ ይገኛል:: በአጠቃላይ፣ አብይ አህመድ እንደ አዲስ እየዘረጋ ያለው የነፍጠኛ ሥርዓት፣ የመጨረሻውን ጦርነት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ከፍቷል:: በመሆኑም፣ የኦሮሞ ቄሮ ይህንን ግልፅ የሆነ አደገኛ ጠላት ትግሉን በማፋፋም፣ እስከ መጨረሻው ለመታገል ወስኗል::
4

የዚህ ዙር ተቃውሞ ዋነኛ አላማ በአብይ አህመድ እየተገነባ የሚገኘው የነፍጠኛው ሥርዓት፣ ሙሉ በሙሉ በኦሮሚያ ውስጥ ተበጣጥሶ፣ ከዚህ የግፍ ሥርዓትና ከብልጥግና የወንጀል ቡድን ነፃ የሆነች ኦሮሚያን ለመፍጠር የሚያስችለውን ምቹ ሁኔታ መፍጠር ነው:: ከዚህም በተጨማሪም፣ የተቃውሞአችን ግብ፣ የአብይ አህመድን የነፍጠኛ ሥርዓት፣ አቅም ኑሮት ሕዝባችን ላይ እየወሰደ ያለውን መራራ ግፍ እንዳይገፋበት አቅሙን ማሽመድመድ ነው::
የዚህ ትግል የአጭር ጊዜ አላማ፣ የነፍጠኛው ሥርዓት ያለ አግባብ ያሰራቸውን የትግላችን መሪዎችን እንዲፈታ ማስገደድ ነው:: በመሆኑም፣ የሚከተሉት የትግል አቅጣጫዎች ከመላው የኦሮሚያ ቄሮ ተላልፏል::
ሕዝባችንን በመጀመሪያው ዙር የተደረገለትን ጥሪ በመቀበልና እርስ በርስም በመጠራራት ለአምስት ቀናት ባደረገው የኢኮኖሚ እቀባ ከፍተኛ ድል ማሰዝገቡ ይታወሳል:: በዚህ ዙር ትግላችን ደግሞ፣ በሚከተለው መንገድ ይቀጥላል።
ወደ መዲናው የሚያመሩ ዋና ዋና ጎዳናዎች እንዲዘጉ የቀረበ ጥሪ
ከሰኞ ሐምሌ 20፣ 2012 ዓም ጀምሮ ባሉት ቀጣይ ሳምንታት መጨረሻው ላልተወሰነ ጊዜ የሚቀጥል
የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለማድረግ እንዲቻል፦
1. በመላው ኦሮሚያ ውስጥ ማንኛውም የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የተቋረጠ ይሆናል። የኦሮሚያን
ከተሞች የሚያገናኙ አውራ መንገዶች ሁሉ ይቋረጣሉ።
2. በተመሳሳይም፣ ትላልቅ የሆኑ፣ ወደ ፊንፊኔ የሚወስዱ የሀገሪቱ ዋና ዋና ጎዳናዎች [Highways] ሙሉ
በሙሉ ተቋርጠው፣ ትራንስፖርት እንዲቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::
3. ይህ የትራንስፖርት ሙሉ በሙሉ የማቋረጥ ተግባር፣ ከሰኞ ሀምሌ 20 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ
ይሆናል::
4. በዚህ የትራንስፖርት ማቋረጥ ተግባር በሚፈጸበት ወቅት፣ ከአምቡላንስ በቀር ከኦሮሚያ ወይም ወደ
ኦሮሚያ የሚደረግ እንቅስቃሴ ሁሉ ሙሉ በሙሉ የተገታ ይሆናል።
5. በዚህ ዙር የሚደረገው ዕቀባ፣ በከተሞች መካከል የሚኖረውን የትራንስፖርት ፍሰት ለማስቆም ብቻ ያነጣጠረ በመሆኑ፣ በየከተሞቹ ውስጥ ያለ የታክሲ አገልግሎት፣ እንዲሁም የተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ሳይስተጓጎሉ ይቀጥላሉ። በከተሞች መካከል የሚኖረው የትራንስፖርት ግንኙነት ግን ሙሉ በሙሉ የተቋረጠ ይሆናል።
6. ይህ የትራንስፖርት እቀባ እንቅስቃሴ ፣ ቄሮ በይፋ መግለጫ በማውጣት ዕቀባው የተነሳ መሆኑን እስኪገልጽ ድረስ ተፈፃሚ ይሆናል።
5

በቅድሚያ የሚወሰዱ እርምጃዎች፦
1) የመንግሥትን ኢኮኖሚ ለማዳከምና የገቢ ምንጩን ማድረቅ ላይ የተኩራል:: ስለዚህ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ይህንን የነፍጠኛውን ሥርዓት የሚደግፉ የፋይናንስ ተቋማት (ለምሳሌ ባንኮችና የኢንሹራን ድርጅቶች) እንዳይጠቀም፣ እንዲሁም አዳዲስ ለገበያ የሚቀርቡ በተመሳሳይ ሴክተር ተሳታፊ የሆኑ ንግዶች በሚቋቋሙበት ጊዜና አክሲዮኖች በሚሸጡ ጊዜም፣ ሕዝባችን አክሲዮኖችን እንዳይገዛ፣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::
2) ይህ የነፍጠኛ ሥርዓት አቀንቃኝ መንግሥት፣ ህዝባችንን እየፈጀ የሚገኘው፣ ከህዝብ በሚሰበሰብ ገንዘብ በመሆኑ ሕዝባችን ለዚህ መንግሥት ምንም እይነት ግብር እንዳይከፍል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::
3) የህዝባችን ጠላት በሆኑ ሀይሎች የሚንቀሳቀሱ የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ እንዳይጠቀምና እነዚህም ተቋማት ኦሮሚያ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ ሙሉ እቀባ እንዲደረግ፣ ለህዝባችን ጥሪ እናስተላልፉለን::
4) በህዝባችን ላይ በቀጥታ የዘር ማጥፋት ወንጀልን የሚሰብኩ፣ እንደ EBC, WALTA, ABBAY Media, ESAT, MEREJA tube, ETHIO Tube፣ አሃዱ ሚዲያ፣ እና Fana BC የመሳሰሉትን ሚዲያዎች እንዳይከታተል፣ ለነሱም ምንም አይነት መረጃ እንዳይሰጥ ለህዝባችን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::
5) የነፍጠኛውን ሥርዓት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚደግፉና በአርቲስት ሀጫሉ ግድያ ውስጥ ተሳትፎ አድርገዋል ተብለው በሚጠረጠሩና ለዚህ ሥርዓት የገቢ ምንጭ የሆኑ ህዝብ በስም የሚያውቃቸው ድርጅቶች ላይ ሙሉ በሙሉ የኢኮኖሚ እቀባ እንዲደረግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::
ልዩ ጥሪ
በኢትዮጵያ ውስጥ የምትገኙ ብሔር ብሔረሰቦች የወደፊት እጣ ፈንታችሁ በቀጥታ ከኦሮሞ ህዝብ እጣ ፈንታ ጋር የተያያዘ እንደሆነ የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይደለም:: ህግና ሥርዓት ይሰፍን ዘንድ፣ የኦሮሞ ቄሮ የሚያደርገው ትግል ትግላችሁ ነው:: ስለዚህ ከኛ ጋር በመቆም ትግላችንን እንድትደግፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::
በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የምትገኙ የሐገር መከላከያ ሠራዊት፣ የኦሮሚያ ፖሊስ፣ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል እንዲሁም በመንግሥት የደህንነት ተቋማት ውስጥ በማገልገል ላይ የምትገኙ የኦሮሞ ልጆች፣ በህዝባችሁ ላይ እየተፈጸመ የሚገኘውን ግፍ እንደምትረዱት አያጠያይቅም። ወደዚህ የሥራ ዘርፍ የገባችሁት፣ ሕዝባችሁን ለመጠበቅ እንጂ ልታሰቃዩት እንዳልሆነ አውቃችሁ፣ ሕዝባችንን ከመጉዳት እንድትታቀቡና መብታችንን ለማስከበር በምናደርገው ትግል እንቅፋት እንዳትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::
6

በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ሆነው፣ በካድሬነት ሥርዓቱን እያገለገሉ የሚገኙትን አካላት ከማንኛውም ማህበራዊ ህይወት እንዲገለሉ፣ ቢሞቱ እንዳትቀብሯቸው፣ አሊያም ዘመድ ቢሞትባቸው እነሱ ጋር ለቅሶ እንዳትደርሷቸው፣ ሰርግና መሰል ፕሮግራሞች ቢኖራቸው ከነሱ ጋር ምንም አይነት ግኑኝነት እንዳይደረግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::
የብልፅግና ካድሬዎች በገጠርም ሆነ በከተማ በሚጠሯቸው ማናቸውም ስብሰባዎች ላይ ሕዝባችን እንዳይገኝ፣ እንዲሁም በጥቅም ተደልለው ይሁን ባለማወቅ በሽምግልና ስም ወዲያ ወዲህ የሚሉ አካላትም ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባለን::
ማሳሰቢያ
——
በምንወስዳቸው እርምጃዎች ወሳኝ የሆኑ ማህበራዊ ተቋማት፣ ለምሳሌ፣ ትምህርት ቤቶች፣ የሰውና የእንሰሳት የጤና ተቋማት፣ እንዲሁም የግብርና ማሰልጠኛ ጣቢያዎች አይነኩም::
የትግላችን ዋነኛ ትኩረት በነፍጠኛው የአብይ ሥርዓተ-መንግሥት ላይ በመሆኑ፣ ሌሎች የባህል፣ የማሕበረሰብ እና የሀይማኖት ተቋማት በምንም ሁኔታ አይነኩም:: ልክ እንደ ከዚህ በፊቱ፣
አፈላጊው ጥበቃ ሁሉ እንዲደረግላቸው እናሳስባለን:: በውስጣችን የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦች፣ የኛው አካል በመሆናቸው፣ ምንም አይነት ጉዳት አይደርስባቸውም::
ማጠቃለያ
——–
ከላይ በግልፅ እንደተገለፀው፣ ህዝባችን በዚህ ወቅት የገባበት ትግል፣ ሙሉ በሙሉ የኦሮሞ ህዝብ በራሱ ሀገር ላይ ባለቤት ለመሆን እስኪችል ድረስ የሚቀጥል ይሆናል:: ስለዚህ ይህ የትግል ምእራፍ ሲገባደድ በቀጣይ በመላው ኦሮሚያ የሚደረግ አዲስ የትግል ምእራፍ እንደሚገለፅ ከወዲሁ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን::
ድል ለኦሮሞ ሕዝብ።


የጠ/ሚ አብይ 4ቱ ልዩ ባህሪያት በዳንኤል ክብረት @Arts Tv World


Birruu Qananiisaa Abbaa Biyyaa New Oromo Music 2020. Offiicial Video. #Seenaa Studio


“Never follow a follower who is following someone who has fallen. Its why the whole world is falling apart.”
― Suzy Kassem.

1 Comment

 1. Oromo, Abbaa Biyyaa:

  Freedom is never given voluntarily; it is bitterly fought for and taken by defeating vicious enemies such as the naftagna and neo-naftagna (warning: the naftagna and neo-naftagna are not necessarily representatives of any particular ethnic group in Ethiopia. They are pseudo-Ethiopian gangs and gangsters who are using the Ethiopian regime to suppress you and other nation nationalities of Ethiopia, including the Amhara mass). You already know this fact and have taken responsibility for freeing yourselves.

  Abiy Ahmed is the most incompetent egoistic neo-naftagna surrounded by the most dangerous enemies of the great Oromo people. Your struggle for just cause shall prevail. The present as well as future of all nation nationalities of Ethiopia living in Oromia is intertwined with your fate and destiny. It is expected that the communities who live among you support your just struggle for your inalienable freedom and stand with you to defeat the anti-Oromo campaigns of the fascistic Ethiopian regime. Conduct your struggle with at most care and wisdom in highly organized and coordinated manners. Read each other; listen to instructions from your leadership and act in unison. No doubt that Abiy Ahmed is existential threat to the Oromo people in particular and the Ethiopian peoples in general. He must go immediately!

  Oromia shall be free!
  Best wishes
  OA

Comments are closed.