ከጨረባ ትርጉም፣ “የጨረባ ምርጫ” ይሻላል!

ከጨረባ ትርጉም፣ “የጨረባ ምርጫ” ይሻላል!

ብልጥግና እና ምሁራኖቿ፣ ትርጉም የማያስፈልገውን የሕገ-መንግሥት ድንጋጌ፣ በጨበጣ (የጨረባ) ትርጉም አድርገውለት፣ ያለ ምርጫ በሥልጣን ካልቆየን እያሉ በድርቅና ሲፎክሩ ውለው፣ አንድ አንድሪያስ ውሃ ሲቸልስባቸው፣ መነጫነጭና መራገም ጀምረዋል።

ፕሮፌሰር አንድሪያስ፣ ለኢህአዴግና ለሕገ-መንግሥቱ ቅርብ ሰው ነው ተብሎ እየታሰበ፣ በጉዳዩ ላይ እራሱን ከኢህአዴግ/ብልጥግና ያራቀ አተያይ ሲያቀርብ፣ እነሱ (‘ተረኛ የኢሕአዴግ ምሁራን’ ሆኑና)፣ ከብልጥግና የአንድርያስን ያህል እንኳን እራሳቸውን ያራቀ ሃቲት ማቅረብ ሲያቅታቸው ታዘብን። ታድያ እኛን መራገምን ምን አመጣው? አንድሪያስም ቢሆን ከኛ ይልቅ ለእናንተው ነው የሚቀርብ።)

ለመንግሥትና ለሕገ-መንግሥቱ ቅርብ ነው ብለው (ድሮ እንዳላወደሱት) አሁን የሚወቅሱት አንድሪያስ እንኳን፣ በዚህ ደረጃ እራሱን ለአብይ የስልጣን ጥማት ከተመቸ አተረጓጎም እራሱን ሲያርቅ (distance ሲያደርግ)፣ እነሱ፣ የሕግ ሊቃውንት ሆነው፣ የእሱን ያህል እንኳን ከአብይ ግለሰባዊ አምባገነንነት እራሳቸውን ማራቅ ካቃታቸው፣ ምን ያህል በምግባር የላሸቁ፣ ለጥቅም ያደሩ፣ ለባለሥልጣን ያጎበደዱ፣ የጨረባ ትርጉም አፍላቂ ስለመሆናቸው ከራሳቸው በላይ ምስክር የለም።

#ለጨረባ_ትርጉም_አፍላቂ_የጨበጣ_ምሁራን#To_apologists_of_power
#Where_your_money_is_there_goes_your_heart
#Leave_the_principles_alone!

Tsegaye Ararssa