ከጋምቤላ ነጻነት ግንባር ( ጋነግ) የተሰጠ መግለጫ

ከጋምቤላ ነጻነት ግንባር ( ጋነግ) የተሰጠ መግለጫ
ሐምሌ 16 : 2013 ዓ/ም
 
በማንኛውም ሀገር ሁለት አይነት የትግል ስልቶች እንዳሉ ይታወቃል። የታደሉ ሀገሮች የፓለቲካ ተቃርኖን በሰላማዊ እና በዴሞክራሲያዊ መንገድ ስለምያስተናግዱ የሀሳብ ውድድሮች ተደርገው በህዝብ ድምፅ ይዳኛሉ። በኢትዮጵያ በተደረገው 6ኛው ብሄራዊ እና ክልላዊ ምርጫ ተሳትፈን ለህዝባችን የሚበጅ ስራ ለመስራት ከፍተኛ ጉጉት ነበረን። የብልፅግና ፓርቲ በኪሱ ያስገባውን ብሄራዊ ምርጫ ቦርድና በእጁ ያለውን የፀጥታ ሀይል በመጠቀም አሳፋሪ ምርጫ አካሂዷል። በዚህም የሰላማዊ ትግል መንገድ ተዘግቶአል።
 
በመሆኑም ለጋምበላ ህዝብ ነፃነትና ፍትህ ለማስገኘት የትግል ስልታችንን ወደ ትጥቅ ትግል ማሸጋገር የግድ ሆኖአል።
የትጥቅ ትግል መስመር ለመመረጥ ያስገደዱን ፤
 
1ኛ የ6ኛው ብሄራዊ እና ክልላዊ ምርጫ በብልፅግና ፓርቲ ማጭበርበር የተነሳ የደሞክራሲ መንገድ ሙሉ በሙሉ ዝግ መሆን
 
2ኛ በጋምቤላ ክልል ያለ አስከፊ የመሠረተ ልማት ችግር
 
3ኛ በጋምቤላ ክልል የተንሰራፋው ሙስና
 
4ኛየህግ የበላይነት አለመከበርና የብልፅግና መንግሥት በስራ ላይ ያለውን ህገ መንግሥት እ-ህገ መንግሥታዊ በሆነ መንገድ ለመቀየር መስራቱ ለሀገር አደጋ በመሆኑ
 
5ኛ የብልፅግና መንግሥት ብሔርን ከብሔር እያጋጨ ለዘመናት ስልጣን ላይ ለመሰንበት እየሰራ መሆኑ ግልፅ ነው። በብልፅግና መንግሥት ሴራ ኢትዮጵያ በደም ጎርፍ እየተጨማለቀች ነው። በአማራ እና በትግራይ ክልሎች መሀከል እየተካሄደ ያለው ደም አፋሳሽ ጦርነት የብልፅግና መንግሥት የሴራ ፓለቲካ አካሄድ ውጤት ነው ብለን እናምናለን።
 
በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በክልላችን ጋምቤላ በአሁን ሰዓት ህዝባዊ መንግሥት እንደሌለ ያሉት ነባራዊ እና ወቅታዊ ሁኔታዎች በተጨባጭ ያሳያሉ።
በመቀጠል፣ የብልጽግና መንግስት የህዝብ ጥያቄዎች ሰምቶና መልስ ከመስጠት ይልቅ ከሀገርና ከህዝብ በታኝ የሆኑትን የራሱን ድርጅት ፍላጎቶች እያስቀደመ ይገኛል።
ለምሳሌ ፣ ለህዝባችን አንገብጋቢ የሆኑትን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ከመመለስ ይልቅ፣የብልፅግና መንግስት ህዝቡ በግድ አለአግባብ መዋጮ ለብልፅግና ፓርቲ በተደጋጋሚ እንዲከፍል አድርጓል፣ አሁንም ድሀውን ሕዝባችንን በመዝረፍ ላይ ይገኛል፣ ወጣቶችን ለልማት ስራዎች ከማደራጀት ይልቅ ራሱን ስልጣን ላይ ለማቆየት ከትግራይ ወንድሞቻችን ጋር እንዲጋደሉ ለውትድርና እየቀሰቀሰና እያደራጀ ይገኛል፣ በሀገራችን በታርክ ያልተለመዱ በርካታ የብሔር ግጭቶች ተከስቷል። የብልጽግና መንግስት ስልጣን ላይ ለዘመናት ለመሰንበት ብሔርን ከብሔር በይፋ የማጋጨት ፖሊሲ እንደሚከተል በአማራ ክልልና ትግራይ ክልል መሀል የፈጠረው ደም አፋሳሽ ጦርነት ብቻውን በቂ ማሳያ ነው።
 
በመሆኑ፣ የብልጽግና መንግስት እስካለ ድረስ ሰላማዊ ኑሮ፣ፍትህ፣ ድሞክራስ፣ ልማት፣ ሰላማዊ ትግል እና በሚቀጥለው 7ኛ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ተስፋ ማድረግ በፍፁም አይታሰብም።
ስለዚህ ያለው ብቸኛው አማራጭ የጋምቤላ ህዝብ በተለይ ሙሁራን እና ወጣቶች ለራሳችሁ መብት፣ነጻነት፣ ልማትና እኩልነት ከለሎች ትጥቅ ትግል ላይ ካሉት ወንድሞች፤ ብሔር ብሔረሰቦች ፤ድርጅቶች ጋር በመሆን የጋራ ጠላታችን የሆነውን የብልጽግና መንግሥት ለማስወገድ ወደ ትጥቅ ትግል እንድትቀላቀሉ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።
 
የጋምቤላ ነጻነት ግንባር (ጋነግ) ጉባኤ እስኪደረግ ድረስ በጊዝያዊነት ድርጅቱን የሚመሩት፤
1ኛ ጋትሉዋክ ቡዎም ፓል (ሰብሳቢ)
2ኛ ጋትሉዋክ ፓል ታርጂያት (ም/ሰብሳቢ)
3ኛ ፒተር ማሞ ኡኬሎ (ፀሐፊ)
ለነጻነትና እኩልነት እንታገላለን!!
ድል ለጭቁን የጋምቤላ ሕዝብ!!