ሪፖርተር እንደዘገበው ከሆነ በሸገር በመልሰው ማልማት ስም ከደሃው

ሪፖርተር እንደዘገበው ከሆነ በሸገርበመልሰው ማልማት ስም ከደሃው ወደ ሃብታም ሊሸጋገሩ ነው።

ሪፖርተር እንደዘገበው ከሆነ በሸገር
አሜሪካን ጊቢ
ገዳም ሰፈር
ሾላ እና መገናኛ
ካሳንቺስ እና
ጌጃ ሰፈር
በመልሰው ማልማት ስም ከደሃው ወደ ሃብታም ሊሸጋገሩ ነው።
አሁን መልሰው ይለማሉ የተባሉት አከባቢዎች ወደ 78 ሄክታር የሚሆኑ ሲሆን እስካ አሁን የመልሶ ግንባታው የዘገየው በመልሶ ማልማቱ ላይ ድሆች በቀረቡት አቤቱታ ነው።አሁን የመልሶ ማልማቱ ሲጀመር ለዳሃው አቤቱታ የተሰጠው ምላሽ ምን እንደሆነ ጋዜጣው አልዘገበም።
እኔን በጣም የሚገርመኝ መንግስት አካባቢውን መልሶ ማልማት ከፈለገ በሊዝ ስም ከሚያግበሰብሰው የመሬት ኪራይ ገንዘብ ደሃውን ከአከባቢው ሳያርቅ በተወሰነ መሬት ላይ እዛው ደረጃውን የጠበቀ ፎቅ ሰርቶ ለምን አያኖራቸውም?
የፎቁን ምድር ደግሞ ለምን በህብረት ንግድ እንዲያቀላጥፉበት መሬቱ ላይ ቀድመው ለሚኖሩት ድሆች አይሰጣቸውም?
ከዚያ የተረፈውን መሬት ደግሞ ለባለሃብቶች በሊዝ መቸብቸብ ይችላል።
ሀገር ማለት መሬት ሳይሆን ሰው ከሆነ መንግስት ይህንን ለማድረግ የሚከለክለው ምንም ነገር የለም።

Via Dereje Gerefa Tullu