ከኦሮሞ ነፃነት ቄሮ (QBO) ጅማ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ የተላለፈ የትግል ጥሪ

ከኦሮሞ ነፃነት ቄሮ (QBO) ጅማ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ የተላለፈ የትግል ጥሪ
____________________________
እንደሚታወቀው እኛ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ የኦሮሞ ነፃነት ቄሮ የሆንን ተማሪዎች ለበርካታ አመታት የነበረብንን መራራ የፀረ ጭቆና ትግል በጋራ ስንታገል እንደቆየን ሁሉ ዛሬም ለኦሮሞ ነፃነት ትግል ሆ ብለን ተነስተናል።
ለብዙ ዘመናት በኦሮሞ ህዝብ ጫንቃ ላይ ሆኖ በህዝቡ ላይ የጫነውን ማህበራዊ፣ እኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ባህላዊ ጠባሳ በተለይ በአሁኑ ሰዓት እየባሰ በመጣበት ሁኔታ እኛ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ የኦሮሞ ነፃነት ቄሮ የሆንን ተማሪዎች በማንኛውም መልኩ ቢሆን ለነፃነታችን እውን መሆን በዚህ አምባገነን መንግስት ፊት ቆመን ለመታገልና የትኛውንም መስዋዕት ለመክፈል ተዘጋጅተናል።
በዚሁ መሰረት ከ29/06/2013 ዓ.ም ጀምሮ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ የኦሮሞ ነፃነት ትግል ተጨቋኞች እና አክራሪዎች የዘመናት ባርነትን የመጨረሻ ለማድረግ ከዚህ በታች ባወጣናቸው መፈክሮች የትግሉን ጎራ ተቀላቅለናል።
 
1. የኦሮሞ ህዝብ የሃገር ባለቤትነት መብት ይከበር ፣
 
2. የኦሮሞን ህዝብ በአካባቢ እና በተለያዩ ሸሮች ማጋጨት ይቁም እኛ ከኦሮሞ ተወልደን ኦሮሞ ሁን ለኦሮሞ እንኖራለን፣ እኛ አንድ ነን፣
 
3. የኦሮሞ ታጋዮችን ማሰር፣ ማሰቃየት እና ማገድ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይቁም፣
እስር ለኦሮሞ መርዝ ሆኖ አልቀረም፣ እኛ ነፃ ሆነን ተወልደን ነፃ ሆነን ለመኖርም መብታችን መገፈፉ በደል ነው፣ በመሆኑም የኦሮሞ እስረኞችን ከህፃን እስከ አዛውንት ፣ ቄሮና ቀሬን በአስከፊ ሰቆቃ ማንገላታት ይቁም፣ በአስቸኳይ ፍቱልን፣
 
4. በካምፓስ የምንገኘውን የኦሮሞ ተማሪዎች በቀበሌ በመከፋፈል፣ ከትምህርት ገበታ ላይ በማባረር ፣ በማንገላታት እና በማዳከም በጭካኔ አእምሮን ወይም ስነ ልቦናን መጉዳት ይቁም። ጅማ የኦሮሞ ነው፣ ዘራችን አንድ ነው፣ መነሻችን አንድ ነው ፣ የኦሮሞ ተማሪዎችን በቀበሌ መከፋፈል በደል እና ነውር ስለሆነ ይቁምልን!!
 
5.በባለፈው ዓመት የትም/ት ዘመን ከካምፓሶች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የተባረሩ ተማሪዎችን ይቅርታ በመጠየቅ ጥሪ ልታደርጉላቸው ይገባል።
ካምፓሶቻችን ለኢትዮጵያ ልጆች የእውቀት ማዕድ ሆኖ ለኦሮሞ ልጅ የግም ስፍራ መሆን የለበትም። ስለሆነም ካምፓሶች ለፈፀሙት በደል ይቅርታ ጠይቀው ተማሪዎቹን ወደ ካምፓስ እንዲመልሱልን እንጠይቃለን።
 
6. መንግስት በራሱ ማህበራዊ ሚዲያወች እያሰራጨ ወይም እያራገበ የሚገኘው ምርጫ የኦሮሞ ፓርቲ የሆኑት ኦነግ እና ኦብኮ የማይሳተፉ ከሆነ ትርጉም የለውም።
ለኦሮሞ መከታ የሆኑትን የኦሮሞ ፓርቲዎች ወደ ኋላ እየጎተቱ ስለ ምርጫ ማውራት መሃይምነት ነው። ይህ ለአሮሞ አይገባውም። እኛ የምንፈልገው የኦሮሞ ብሔራዊ የሽግግር መንግስት ነው።
 
7. ኦሮሞ ታላቅ ህዝብ ሆኖ ሳለ በሁሉም ቦታ መዋረድ እና መሳቀቅ አይገባውም።
ማሳሰቢያ/ማስጠንቀቂያ
ማንም ሰው የተማሪዎቻችንን ሃሳብ ጥሶ ወደ ትምህርት ቢመለስ የማያዳግም እርምጃ ይወሰድበታል። Daniel Dhaba