ከአያት ጦር ሃይሎች ያመራ የነበረ ባቡር በተሽከርካሪ ተገጨ!!

ከአያት ጦር ሃይሎች ያመራ የነበረ ባቡር በተሽከርካሪ ተገጨ

A pick up vehicle crashed into a light train in Addis Ababa this morning, causing traffic disruption

ባቡር በተሽከርካሪ ተገጨ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 10 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአያት ወደ ጦር ሃይሎች ያመራ የነበረ የአዲስ አበባ ከተማ ቀላል ባቡር በተሽከርካሪ ግጭት ደርሶበታል።

ባቡሩ ከአያት ተነስቶ ወደ ጦር ሀይሎች በማምራት ላይ እያለ ሰዓሊተ ምህረት አካባቢ ባለው የተሸከርካሪዎች ማቋረጫ ላይ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 – ኤ 25640 በሆነ ቶዮታ ፒካፕ ተሽከርካሪ ተገጭቷል።

በወቅቱ ባቡሩ እየመጣ መሆኑን የተመለከቱ በአካባቢው የሚገኙ የትራፊክ ፖሊሶችና የተሽከርካሪ ማቋረጫ ሰራተኞች ለአሽከርካሪው መኪናውን እንዲያቆም ቢነግሩትም፥ ትዕዛዝ ሳይቀበል ባቡሩን መግጨቱን የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የኮሙዩኒኬሽን ዳሬክተር አቶ ደረጃ ተፈራ ተናግረዋል።

በግጭቱ በሰው ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ያልደረሰ ሲሆን፥ በባቡሩ የውጭ አካል ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሷል።

ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ26 ደቂቃ ጀምሮም ከአያት እስከ ጉርድ ሾላ ያለው መስመር ለ1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ያክል ያለ አገልግሎት ቆይቷል።

የመስመሩ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ እንዳይቋረጥም ከጉርድ ሾላ እስከ ጦር ሃይሎች ያለው በግማሽ ባቡሩ አግልግሎት እንዲሰጥ መደረጉን ነው አቶ ደረጀ ያነሱት።

ከግጭቱ በኋላ አሽከርካሪው የተሽከርካሪው ፍሬን እንዳስቸገረው ገልጿል፤ በግጭቱና በአገልግሎት መቋረጡ የደረሰው ጉዳትም በትራፊክ ፖሊስ ካርታ በማንሳት እየተጣራ ይገኛል።

ከአያት ጦር ሃይሎች ያለው የባቡር መስመር አገልግሎት ከ4 ሰዓት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ገብቷል።

Source: FBC