ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ጋር በተያያዘ ሶስት የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ጋር በተያያዘ ሶስት የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ግለሰቡም ወደ መኖሪያ ቤቱ በተወሰደበት ወቅት ክላሽንኮቭ መሳሪያ በማውጣት በጸጥታ ሃይሎች ላይ ጥቃት ለማድረስ መሞከሩን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ከቤቱም ሁለት ክላሸንኮቭ መሳሪያዎች ተገኝተውበታል፡፡
እነሱ በደረሱበት ሞያዊ ስነምግባ (ethicists) ግድለት የማይለያቸው የጫካ አውሬዎች ናቸው ሁሌ በመግደልና በአመፅ መኖር ስልጣኔና እውቀት የሚመስላቸው ዘላለም የኃልዮሽነት የተጣባቸው ክፉ ተናካሾች ናቸው ስንል ዝም ብለን አይደለም ሕወሃት መቼም የሚሰለጥን ፍጡሩ አይደለም ተስፋ ላልቆረጣችሁ ማስረጃው ይሄውላችሁ

(amharaweb)ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ጋር በተያያዘ ሶስት የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰብ “ታምሚያለሁ” በማለቱ መድኃኒት ለመውሰድ ወደ ቤቱ እንዲሄድ የፈቀዱ ፖሊሶች ናቸው በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡ ግለሰቡም ቤቱ ውስጥ ከገባ በኋላ ለማምለጥ በመሞከሩ  ከጸጥታ ሃይሎች ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ ገብቶ ነበር፡፡

በዚህ  የተጠረጠሩ ሶስት የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ነው የአሶሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ያስታወቀው፡፡

የፖሊስ አባላቱ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰብ ላቀረበውየ”ታምሚያለሁ” ጥያቄ ጉዳዩ ከሚመለከተው የወረዳው አካል ትዕዛዝ ሳያገኙ በራሳቸው ፈቃድ  ወደ መኖሪያ ቤቱበመውሰዳቸው ነው፡፡ ተጠርጣሪውን ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ ሲገባቸው ወደ መኖሪያ ቤቱ መውሰድእንዳልነበረባቸውም ነው የተገለጸው፡፡

ግለሰቡም ወደ መኖሪያ ቤቱ በተወሰደበት ወቅት ክላሽንኮቭ መሳሪያ በማውጣት በጸጥታ ሃይሎች ላይ ጥቃት ለማድረስመሞከሩን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ከቤቱም ሁለት ክላሸንኮቭ መሳሪያዎች ተገኝተውበታል፡፡

ግለሰቡም በጸጥታ ሃይሎች እና በህብረተሰቡ ትብብር ወደ ነበረበት ተመልሷል፡፡  አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በተፈጠረ ግጭት የሶስት ተማሪዎች ሕይዎት ማለፉ ይታወሳል፡፡ ትምህርትም እስካሁን አልተጀመረም፡፡ ሰላማዊ መማር ማስተማሩን ለማስጀመርም ጥረት እየተደረገ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ምንጭ፡- ኢዜአ እና የክልሉ አስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ


በአሶሳ ህዝብ ለህዝብ በማጋጨት ሴራ ተጠርጥሮ ከበርካታ… ፎርጅድ መታወቂያ፣ የባንክ–ቡክ ደብተሮች፣ ብርና የጦር ማሳሪያዎች ጋር በቁፅፅር ስር የዋለው #ገሬ–ወዲ ሴሮ #ከማህደር አሰፋ ጋር ያለው ግንኙነት እስከ ምን ነው?😉


OMN: በአሶሳ ከተማ የተካሄዳ የምክክር መድረክ [NOV 26, 2018]