የግንቦት 7 አፈ ቀላጤ አቶ ኤፍሬም ማዲቦ ለቢቢሲ በሰጠው መግለጫ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር እንዳልተለያዩ ተናግሯል፡፡

የግንቦት 7 ነገር ! የግንቦት 7 አፈ ቀላጤ አቶ ኤፍሬም ማዲቦ ለቢቢሲ በሰጠው መግለጫ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር እንዳልተለያዩ ተናግሯል፡፡ ይህ ውሸት ብቻም ሳይሆን የቅጥፈትን የመጨረሻውን ደረጃ ያሳያል፡፡ አገር እምራለሁ የሚል ድርጅት በዚህ ደረጃ አገር የሚያውቀውን ፀሐይ የሞቀውን ሀቅ መካዱ ድርጅቱ ነውራቸውን ሺጠው የበሉ ሰዎች መጠራቀሚያ መሆኑን ነው ያመለከተኝ፡፡

ዕውነታው የሚከተለው ነው፡፡ ኤርትራ ውስጥ በ8 ዙር ‹‹ተመርቀዋል›› የተባሉት ወታደሮች ይሁኑ መናፍስት እግዜር ይወቃቸውና ወይ በመስቀል አደባባይ አሊያ ደግሞ በባሕር ዳር ስታዲዮም አንድ ብርጌድ ጦር ብቅ ይላል ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ ግን የሆነውን ሁላችንም ያየነው ነው፡፡

በኤርትራ ሳለ ድርጅቱ 5 ሥራ አስፈጻሚዎች ነበሩት፡፡ እነርሱም አቶ ማዕዛው ጌጡ፣ መንግሥቱ ወልደሥላሴ፣ ኑርጀባ አሠፋና ተስፋሁን ተገኝ ነበሩ፡፡ ከነዚህ ሁሉ ሰዎች (ዘር ከልጓም ይስባለ ብሎ ከዶክተር ብርሃኑ ጋር ከተሠለፈው ኑርጀባ አሠፋ ውጭ የትኛውም ሥራ አስፈጻሚ ከእነ አቶ አፌሬም ጋር የለም፡፡

እነ አቶ ኤፍሬምና ዶክተር ብርሃኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ከገባን ያጋልጡናል ካሏቸው ሰዎች መካከል ጀግናው አርበኛ ተስፋውን ተገኝን አስቀድመው በሴራ አስገድለውታል፤ ምናልባትም የእነ ተስፋሁን ተገኝና የሌሎች ንጹሐን አማሮችን ነፍስ በፍርድ ቤት ይህን የማፍያ ቡድን መክሰስ የጠበቆች ሚና መሆኑን መግለጽ ያስፈልጋል፡፡ አቶ ታሪኩ ግርማንና አርበኛ አሊ ፋንታን ደግሞ አሁንም በኤርትራ እሥር ቤት አስከርችመውባቸው ነው የመጡት፡፡

ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ወታደሮች ከነኤፍሬም ጎን የቆመ የለም፡፡ እንግዲህ ለአቶ ኤፍሬም ድርጅቱ ተለያይቷል የሚባለው በሦስቱ ዲያስፖራ አፈኞች (ዶ/ር ብርሃኑ፣ አቶ ኤፍሬምና አንዳርጋቸው) መካከል ልዩነት ሲፈጠር ነው ማለት ነው፡፡

ሌላው ግን ቢቢሲ BBC News Amharic የመንግሥቱ ወልደሥላሴን አስተያየት ማስፈሩ ካልቀረ የአንደኛውን ወገን ብቻ ርዕስ ማድረጉ ያልጠበቅኩት ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡


Via: Muluken Tesfaw