ከአመታት በፊት ከ አባቴ ጋር ኢቲቪ እያየን ነበር።

ከአመታት በፊት ከ አባቴ ጋር ኢቲቪ እያየን ነበር።
 
የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ” ሴትየዋ ( ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳን ለማለት ነው) በመድረክ ሞቅታ የተናገሩት ከሆነ ብለን ይቅርታ እንዲጠይቁ እድል ብንሰጣቸውም አልተጠቀሙበትም” የሚል አይነት ንግግር እያሰማ ነበር። (ንግግሩ ወ/ሪት ብርቱካን አውሮፓ ተናገሩት የተባለውና ዳግም ለ እስር የተዳረጉበት ነበር።)
ፋዙካ በጣም አዝኖ “ትልቅ ሰው ናት። እንዴት በመድረክ ሞቅታ ተናግራ ከሆነ ይላል?” ሲል ሰማሁት።
ዛሬ ያኔ ወ/ሪት ብርቱካን የተከሰሰችበት አይነት ፖለቲካዊ ክስ ተከፍቶባቸው እስር ቤት የተወረወሩ ተፅኖ ፈጣሪ የፖለቲካ እስረኞች አሉ።
 
የጠቅላይ ሚንስትሩ አካሄድ አይደለም ለሷ አይነት ፖለቲከኛ ለማንም ተራ ሰው ግልፅ ነው።
ጠሜው በምንም ተዕምር ነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲደረግ አይፈልግም። ተቀዋሚዎችን ሰበብ ፈጥሮ እያሰሩ ፍትሃዊ ምርጫ ማድረግ አይቻልም። ሌሎች ሌሎች ሴራዎችም እየተሴሩ ነው። ይህን ወ/ሪት ብርቱካን ጠንቅቃ ታውቃለች።
አሁን ጥያቄው “ወ/ሪት ብርትኳን ሚደቅሳ ይህን ሁሉ ጉድ እያየች እንዳላየ በማለፍ ለኮረኔሉ አክሊል በመድፋት ለንግስናው ህጋዊ ሽፋን በመስጠት የአምባገነን መጠቀሚያ ትሆናለች ወይስ እንደቀድሞው በቆራጥነት ለህሊናዋ ታድራለች ?” የሚል ነው።
አባቴ “ትልቅ ሰው ነች” ያላትን ሴት ትልቅነት የምለካው ይህን ጥያቄ በምትመልስበት መንገድ ነው።
እኔ ለሷ የምመኘው እነ ስዬን ከእስር የለቀቀችበት እና እነ መለስን የተጋፈጠችበት አይነት የሞራልና የህሊና ደረጃ ላይ እንድትሆን ነው።
በዚህ አጭር ዕድሜ አሳዳጆች ሲሳደዱ፤ እስረኞችና የሞት ፍርደኞች ባለስልጣናት ሲሆኑ፤ እንደ በረከት አይነት አይነኬ ባለስልጣናትም ወይኒ ሲወርዱ አይተናል።
ትልቅነት ከእውነት ጋር ቆሞ ለህሊና ማደር ነው።
ነገ ይዞ የሚመጣውን ማን ያውቃል??
ሌላው ከምርጫ በፊት ምርጫ ሊያስፈፅም የሚችል ህጋዊ የሽግግር መንግስት ሊቋቋም ይገባል።
መስከረም 25