ከሰዓታት በፊት በድሬደዋ ረዘም ላለ ጊዜ የጣለው ዝናብ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ጎርፍ አስከትሏል።

ከሰዓታት በፊት በድሬደዋ ረዘም ላለ ጊዜ የጣለው ዝናብ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ጎርፍ አስከትሏል።

(DW Amharic) በድሬዳዋ ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ ጉዳት አደረሰ ከሰዓታት በፊት በድሬደዋ ረዘም ላለ ጊዜ የጣለው ዝናብ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ጎርፍ አስከትሏል። ቁጥሩ በውል አይታውቅ እንጂ የተወሰኑ መኖርያ ቤቶችን ማፍረሱን እና አንዳንድ ንብረቶችንም ማበላሸቱን የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ዲቪዥን ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ባንታለም ግርማ ለዶይቼ ቬለ ገልፀዋል። በጎርፍ ሊወሰድ የነበረ አንድ ሰው ህይወት በፖሊስ መትረፉን አስታውቀዋል።

ጎርፍ ያደረሰውን ጉዳት በተመለከተ የመስተዳድሩ ከፍተኛ ኃላፊዎች ተዘዋውረው እየተመለከቱ መሆናቸውን ከመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ከተማዋን ሁለት ከፍሎ የሚያልፈው የአሸዋ መውረጃም መጠኑ ከፍ ያለ ጎርፍ መጥቶበታል። ለአንድ ሰዓት ያህል የቆየው ዝናብ ጋብ ባለበት ጊዜ የተወሰደ ቪድዮ ተያይዟል። የዶይቼ ቬለ የድሬደዋ ዘጋቢ መሳይ ተክሉ ከሰሞንኛው የአየር ትንበያ ጋር በተገናኘ ዛሬ የጣለው ዝናብ እና ያስከተለው ጎርፍ እንደ ማንቂያ ደውል ሊወሰድ የሚገባው ነው ብሏል። መሳይ እንዳለው ቀደም ሲል ተገንብተው ጉዳት የደረሰባቸው የጎርፍ መከላከያ ግንባታዎችን በአፋጣኝ መጠገን ያስፈልጋል።
(ቪዲዮ፦ መሳይ ተክሉ)