ከሩሲያ ከእስራኤል ከቱርክ ከኳታር ግብጽ… የሚመጣ የኃይማኖት እርዳታ ለቤትህ ችግር መፍቻ ሳይሆን ጣጣ ነው::

ከሩሲያ ከእስራኤል ከቱርክ ከኳታር ግብጽ… የሚመጣ የኃይማኖት እርዳታ ለቤትህ ችግር መፍቻ ሳይሆን ጣጣ ነው::
ችግሩን አሸክሞ የሚልከው የቤት ስራ የሚሰጥ ሀገር እንዴት ከወንድም ጋር ለተፈጠረ ችግር ፈቺ ሊሆን ይቻላል?
እርስ በእርስ ስንባላ መሳሪያ ይሸጡልሀል:: ቱርክ ሰራሽ…ሩሲያ ሰራሽ…ዒላማቸው ያ ነው::
ስለዚህ ማጎብደዱ ቀርቶ ውስጣዊ መፍትሔ ላይ ይተኮር::
ክርስቲያን እና ሙስሊም በሠላም የሚኖርባት ሀገር እኮ ኢትዮጵያ ናት::

Kassahun Yilma

በነገችን ላይ ሩሲያዊው የሚኒሊክ “ወዶ ገብ ወታደር” (በነ ወዳጆቻችን Bewketu Seyoum አገላለጽ?) አሌክሳንደር ቡላቶቪችን በተመለከተ ፊንፊኔ ያለው የሩሲያ ኢምባሲ አንድ ሁላችንም ልንሳተፍበት የምንችል “ዝክረ ቡላቶቪች” ሲምፖዚየም ለምን አያዘጋጅም? ቡላቶቪች የአጤ ሚኒሊክ የግል ወዳጅ፣ ሲበዛ አድናቂ ብቻም ሳይሆን አምላኪው የነበረ ነው ማለት ይቻላል። እንዲህም ሆኖ፣ ባጤው ዘመን ስለተፈጸሙት ታሪካዊ እውነታዎች ከመዘገቡልን ጸሃፍት አንዱ ነው ቄስ አሌክሳንደር ቡላቶቪች።

Girma Gutema