ከምዕራብ ጉጂ ዞን የተፈናቀሉ 188 ሺህ 744 ዜጎች ወደ መኖሪያ ቀያቸው ተመለሱ

ከምዕራብ ጉጂ ዞን የተፈናቀሉ 188 ሺህ 744 ዜጎች ወደ መኖሪያ ቀያቸው ተመለሱ

(fanabc)—-አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 23፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከምዕራብ ጉጂ ዞን ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያዎች ከነበሩት 188 ሺህ 744  የሚሆኑት ዜጎች ወደ መኖሪያ ቀያቸው መመለሳቸውን የብሄራዊ አደጋ ስጋት እና ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ በጌዲዮ ዞን የተፈናቀሉ ዜጎችንም ወደ መኖሪያ ቀያቸው የመመለሱ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቋል።

በጌዲዮ ዞን ተፈናቅለው በሰባት መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ከነበሩ ዜጎች ውስጥ ከ223 ሺህ በላይ የሚሆኑትን ወደ ቀድሞ ቀያቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።

በመጠለያ ጣቢያዎቹ ከ600 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎችን ወደ መኖሪያ ቀያቸው ለመመለስ የህዝብ ለህዝብ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው።

ተፈናቃይ ዜጎችን ወደ መኖሪያ ቀያቸው ከመመለስ ባለፈም ከ6 እስከ 8 ወር ድረስ የማቋቋሚያ ድጋፍ እድሚደረግም ተነግሯል።

በይስማው አደራው